Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ኒያላ ኢንሹራንስ የገዛውን ህንፃ...
ኒያላ ኢንሹራንስ የገዛውን ህንፃ... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
Imageኒያላ ኢንሹራንስ የገዛውን ህንፃ እንዲመልስ ተፈረደበት

ኒያላ ኢንሹራንስ ከሰባት ዓመት በፊት ገዝቶት የነበረውን ሆማ ህንፃ ለባለቤቱ እንዲመልስ ተፈረደበት፡፡
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀጥተኛ ክስ 8ኛ ችሎት ትናንት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ኒያላ ኢንሹራንስ በ1994 ዓ.ም በ6.5 ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆማ ህንፃን ለባለቤቱ እንዲመልስና የሆማ ህንፃ ባለቤት ደግሞ የወሰዱትን ብር ለኒያላ ኢንሹራንስ እንዲመልሱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ ከስድስት ዓመት በፊት የገዛውን ህንፃ እንዲመልስ የተፈረደበት የግዥ ስምምነቱ በመንደር ውል ብቻ የተፈፀመ ውልና ማስረጃ ያላፀደቀው በመሆኑ ነው፡፡

ይህ ውሳኔ የተላለፈው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ስልጣን ባለው አካል ፊት ወይም በፍርድ ቤት ፊት መደረግ አለበት በሚለው አንቀጽ 1723 መሰረት መሆኑ ታውቋል፡፡

በመንደር ውል መሰረት የህንፃ ግዥውን የፈፀመው ኒያላ ኢንሹራንስ የህንፃው ባለቤት በውልና ማስረጃ ተገድደው እንዲፈርሙ ያ ካልሆነ ደግሞ ብሩን እንዲመልሱ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ሲሆን የህንፃው ባለቤት በበኩላቸው አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው እንደ ውሉ እንዲፈጽም የሚገደደው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ ተገድደው ውል ለመዋዋልም ሆነ ስም ለማዛወር አንገደድም የሚለውን መከራከሪያ አቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኒያላ ኢንሹራንስ አምስት አመት ሙሉ ህንፃውን በነፃ ሲጠቀም መቆየቱን ገልፀው ህንፃው ቢከራይ ኖሮ 7.2 ሚሊዮን ብር ሊያስገኝ እንደሚችል በማብራራት ከኪራይ ይገኝ የነበረው ይህ ገንዘብ በኒያላ ኢንሹራንስ እንዲከፈላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

የሁለቱንም ወገኖች መከራከሪያ ያደመጠው ፍርድ ቤትም ኒያላ ኢንሹራንስ አሁን የሚጠቀምበትን ህንፃ ለባለቤቱ እንዲመልስ፣ የህንፃው ባለቤት 6.5 ሚሊዮን ብሩን ለኒያላ ኢንሹራንስ እንዲመልስና የጠበቃ ውልም እንዲቻቻሉ ወስኗል፡፡  

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >