Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
May 09th
Home arrow Sections arrow የሰለጠኑ ዳያስፖራዎችን ለአገር ዕድገት
የሰለጠኑ ዳያስፖራዎችን ለአገር ዕድገት Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአውሮፓ አገራትና በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ሙያዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በተገኘ ነፃ የትምህርት ዕድል ወይም በሌላ አጋጣሚ ከአገር ወጥተው ኑሯቸውን እዚያ ካደረጉት ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ ለአገራቸው ፍቅር ያላቸው፣ የሚችሉትን ለማድረግ ዕድሉን ቢያገኙ ወደ ኋላ የማይሉ ናቸው፡፡
በሚሌኒየሙ በዓል በርካታ የዲያስፖራ አባላት ወደ አገራቸው መጥተው ያሉትን ዕድሎችና ሁኔታዎችን አይተው መጥተው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበትን መንገድ ይወስናሉ ተብሎ ተገምቶ ነበር፡፡ ሆኖም ምክንያቱ በውል ባልለየ ሁኔታ የመጡት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራው አባላት ቁጥር የተፈለገውን ያህል አልነበረም፡፡

ባለፈው ሳምንት በዚሁ ገጽ በቀረበው ዜና በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ተመልሰው ቢያንስ በአጭር ጊዜ  ለአገራቸው ዕውቀታቸው ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ለማድረግ ስለተደረጉ ጥረቶችና ስላስመዘገቧቸው ውጤቶች ተዘግቧል፡፡

አራት ሚሊዮን ብር የተመደበለት ተመላሽ ፕሮፌሽናል ኢትዮጵያውያንን በሥራ ለማሰማራት የታለመ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ፕሮግራም ጀምሮ የተለያዩ የዲያስፖራ ተቋማት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የባለሙያ እጥረት ያለባትን አገራቸውን እንዲረዱ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማኅበር (SEED) የዲያስፖራ ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናሎች ኔትወርክ (“ሓ”“፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዎች ማኅበር (ENAHPA) እና ሌሎችም ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ፕሮፌሽናል ኢትዮጵያውያንን ለአገራቸው አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ሲያበረታቱ ቆይተዋል፡፡

ተደጋግሞ እንደሚገለፀው ግን በሰለጠነ የሰው ኃይል ስደት ክፉኛ የተጠቃችው ኢትዮጵያ በእነኝህ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ እንዳትሆን ያደረገው የዲያስፖራ አባላቱን አንድ ላይ በማሰባሰብ ኃላፊነታቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል ድርጅታዊ አወቃቀርና መረጃ አለመኖሩ ነው፡፡

ለምሳሌ የኢትዮጵያውያን ፕሮፌሽናሎች ኔትዎርክ በዲያስፖራ (NEPID) የተሰኘው ተቋም ያወጣው መረጃ እንደሚለው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው፡፡ በዚህ መሠረትም ፣ቪዥን ፎር ዴቨሎፕመንት፣ እና ፣አሜሪካን ኢንተርናሽናል ሄልዝ አሊያንስ፣ የተባሉት ተቋማት ጥምር ውጤት የሆነው ፣የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ በጎ ፈቃደኝነት ፕሮግራም፣ ተመስርቷል፡፡ ይኸው ፕሮግራም ኢትዮጵያውያኑን በኤድስ መከላከያ ፕሮግራሞች ላይ ለማሳተፍ ያለመ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት በወጣው ጽሁፍ ላይ የተገለፀው በካናዳና አካባቢዋ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ላይ የሚሰራ ተቋም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን አንድ ፕሮፌሰር ጠቅሶ እንዳለው ዩኒቨርሲቲው በመምህራን እጥረት ተጎድቷል፡፡ እንደ ፕሮፌሰሩ አገላለጽ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ዶክተሮች ይልቅ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኙት ይበልጣሉ፡፡ በተለይ በህክምናው ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናት ለማለት ይቻላል፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ለምሳሌ በአገሪቱ 2032 ሐኪሞች መኖራቸውን ሲገልጽ አንድ ሐኪም ለ34ሺህ 449 ሰዎች እንደሚያገለግል ይጠቅሳል፡፡ 12ሺህ 610 ነርሶች ሲኖሩ 1 ነርስ ለ5ሺህ 551 ሰዎች ይደርሳል፡፡ 750 ፋርማሲስቶች ሲኖሩ 1 ፋርማሲስት ለ93 ሺህ 333 ሰዎች ይሆናል፡፡ በሆስፒታሎች ደረጃ 119 ሆስፒታሎች ሲኖሩ 1 ሆስፒታል ለ588 ሺህ 235 ሰዎች አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ በተለይ በጤናው ዘርፍ ወደ አገራቸው መጥተው ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የሚገለፀው በለሙያዎች ድጋፍ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ወሳኝ ነው፡፡ አሉ የሚባሉትን የመዋቅር (የአደረጃጀት) እና የመረጃ ችግሮች ለማሻሻል መሥራትም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡

በተለይ በመንግሥት በኩል በዲያስፖራ የሚኖሩ ዜጎቿንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑን አገራቸውን ለመርዳት መሥራት በሚለው ዓላማ ሥር ለማሰባሰብ ጠንካራ ሥራ መስራት ተገቢ ነው፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያኑም የፖለቲካ አመለካከት ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው አገራቸውን ለመርዳት በቁርጠኝነት ሊነሳሱ ይገባል፡፡ አብዛኞቹ አገራቸው በዝቅተኛ ደረጃዎች ላይም ቢሆን በነፃ የትምህርት ዕድል የሰጠቻቸው ናቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ሳይቀር ተምረውበታል፡፡ የግብር ከፋዮቿን ገንዘብ ተጠቅመው የሚፈልጉት ደረጃ ላይ ደርሰውበታል፡፡ ኢትዮጵያውያኑን ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶች የተቀናጁ እንዲሆኑ ማድረግ ደግሞ ውጤቱ አሁን ከሚታየው የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡


በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >