| አሜሪካ የሚላከው የወጪ ንግድ... |
|
|
| Sunday, 02 March 2008 | |
|
አሜሪካ የሚላከው የወጪ ንግድ ገቢ በ30 በመቶ ጨመረ
ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከምትልከው የወጪ ንግድ ገቢ በ2005 ከነበረው 61 ሚሊዮን ዶላር በ2007 ወደ 88 ሚሊዮን ዶላር በማደግ በ30 በመቶ መጨመሩ ተጠቆመ፡፡ የአጎዋ የሁለትዮሽ ንግድ ፕሮግራም ዩ ኤስ ኤይድ (ቮለንተርስ ፎር ኢኮኖሚክ ግሮውዝ አላየንስ ኢትዮጵያ AGOA ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ምርቶች በአጎዋ/አጠቃላይ የሚመረጥ ሥርዓት ሥር መቶ በመቶ በመጨመር 8.9 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ የአሜሪካ ኤምባሲ የካቲት 20 ቀን 2000 ዓ.ም ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ያመለክታል፡፡ አጎዋ (የአፍሪካ ግሮውዝ ኦፖርቹኒቲ አክት) የአሜሪካ መንግሥት ከ6..000 በላይ ምርቶች ከተመረጡ የአፍሪካ አገሮች ከኮታና ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲገቡ የሚያስችል እድል ሲሆን በዚህ የንግድ እድል የኢትዮጵያ የዚህ ዓመት ገቢ ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረው በእጥፍ መጨመሩ ተመልክቷል፡፡ የአጎዋ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ አዲስ አለማየሁ የአሜሪካ ገበያ ከፍተኛ ውድድር ያለበትና ተፈላጊ መሆኑን ገልፀው፣ እድገቱ አሜሪካውያንም ሆኑ ሌሎች ባለሐብቶች በኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ላይ ለመሰማራት ያላቸው ተነሳሽነትና የአገር ውስጥ ላኪዎች አቅም እያደገ መምጣት የፈጠረው ለውጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአጎዋ ፕሮጀክት በአቅርቦት በኩል በቂ ምርት ያለማምረትና ለሚመረቱት ምርቶች ገበያ የማግኘት ችግር የነበረ ቢሆንም ወደ አሜሪካ የተላከው ጠቅላላ የወጪ ንግድ ገቢ ግን እድገት ማሳየቱ ተገል..ል፡፡ በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ በሚያገኙበት ሂደት ላይ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዲያስፖራዎችን ቁጥር በመጨመር በአጎዋ የሚላኩ ምርቶችን ዓይነት እንዲጨመር በቀጣይ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአበባ፣ ለማርና ለቅመማ ቅመም ትኩረት እንደሚሰጥም ተገል..ል፡፡ አጎዋ ፕሮጀክት ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዓለም የሠራተኛ ድርጅት (ILO) ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወደ አሜሪካ የሚላከውን የኢትዮጵያን የልብስና የምርጥ ልብስ ድርሻ ለማሳደግ የቅርብ አጋርነት መመስረቱን በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |