Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የናዝሬት አሰላ መንገድ ከታቀደለት...
የናዝሬት አሰላ መንገድ ከታቀደለት... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
Imageየናዝሬት አሰላ መንገድ ከታቀደለት ጊዜ በፊት ተጠናቀቀ

ከናዝሬት አሰላ ያለው የ79 ኪሎ ማትር የአስፋልት መንገድ ተመረቀ፡፡ የምረቃ ስርዓቱ በተከናወነበት ባለፈው ሐመስ ግንባታውን ያካሄደው የቻይናው ሲኖ ኮርፖሬሽን ተወካይ እንደገለፁት፣ መንገዱ ከታቀደለት ጊዜ በፊት በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል፡፡ ለመንገዱ ሥራ ለሚውሉ የኮንስትራክሽን እቃዎች 1ዐዐ ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጋቸውና 13ዐዐ ያህል ሠራተኞችንም በመቅጠር ሥራው ቶሎ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡ በቀጣይ ከአሰላ ዶለላ ያለውንም መንገድ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚገነቡ አስረድተዋል፡፡
የናዝሬት አሠላ መንገድ ይጠናቀቃል ተብሎ ስምምነት ላይ የተደረሰው በፌብሪዋሪ 2ዐዐ8 ሲሆን ነገር ግን ከእቅዱ በፊት ዲሴምበር 2ዐዐ7 ማጠናቀቁ መቻሉን የኩባንያው የሥራ ሃላፊዎች ገልፀዋል፡፡ በመንገዱ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የቻይና የኮንስትራክሽን ሚ/ር ዋንግ ጉአቶ በበኩላቸው ይህንን መንገድ ለገነባውም ሆነ ለሌሎች የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩትን ሥራ ውጤታማ እንዲሆን መንግሥታቸው አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡

የናዝሬት አሰላ መንገድ ከመሠራቱ በፊት አስቸጋሪ እንደነበር የጠቆሙት በምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ተወካይ በበኩላቸው “ቀድሞ ከአሰላ ናዝሬት ለመምጣት አራት ሰዓት ይፈጅብን ነበር፡፡ አሁን ግን ወደ አንድ ሰዓት ዝቅ እንዲል አድርጐልናል” ብለዋል፡፡

የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አርከበ እቁባይ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በቻይና መንግሥታት መካከል በተደረሰ ስምምነት በርካታ የቻይና ኩባንያዎች በአገር ውስጥ እየተንቀሳቀሱና ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ አካባቢ ያለውን የሰብል ምርት በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማጓጓዝ ይህ መንገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የጠቆሙት አቶ አርከበ፣ የቻይናው ኩባንያ ይህንን መንገድ ለመሥራት ያሳየውን ብቃት አድንቀውታል፡፡  የናዝሬት አዋሳ መንገድ ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀ መሆኑንም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዚአድ ወ/ገብርኤል የገለፁ ሲሆን መንገዱም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >