Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Monday
Oct 13th
Home arrow Sections arrow አዲስ አበባ የቷ ነች?
አዲስ አበባ የቷ ነች? E-mail
Sunday, 06 January 2008

ሳይመለስ የቀረ ጥያቄ

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ናት፡፡ በአንድ ወቅት ወታደራዊው መንግሥት የከተማ ቦታና ትርፍ ቤቶችን በወረሰበት በሐምሌ 19 ቀን 1967 ዓ.ም ዋዜማ ላይ አዋጁን ከነተከታይ ውጤቱና የአፈጻጸም ችግሮቹ ለሕዝብ ከማስተዋወቁ በፊት ከአዋጁ አስቀድሞ ባወጣው መግለጫ አዲስ አበባን የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ብቻ ሳይሆን ..የአድኃሪያን የመጨረሻ ምሽግ..ም ብሏት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ  ከተማ  ከተማ መናገሻ ከተማ መዲና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አሁን ደግሞ የተተኪው የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ናት፡፡ የአፍሪካ አህጉር ኒዎዮርክ ወይም ጀኔቫም ይሏታል፡፡

የኢትዮጵያ /መልክዓ   ክፍፍል ባጠቃላይ ግዛቶች ወይም በክፍለ ሀገሮች ተሸንሽኖ በነበረበት ወቅት የ..ተማሩ..ና የኖሩ እንደሚያውቁት አዲስ አበባ የሸዋም ዋና ከተማ ጭምር ነበረች፡፡

ኢትዮጵያ ከምንነጋገርበት የግዛት አስተዳደራዊ ክፍፍል አንጻር ወደ ሀያ አምስት ሀያ ስድስት ያህል የአስተዳደር አካባቢዎችም ራስ ገዝ አካባቢዎች በተከፈለችበት  ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ ከሦስት አመት በላይ ባልዘለቀው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዘመን የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት የወልመራን፣ የሰንዳፋን፣ የሰበታንና የአቃቂን አውራጃዎች እስኪያካትት ድረስ ሰፍቶ ነበር፡፡ አሁንም ድረስ በብዙዎች ነዋሪዎችና ባለጉዳዮች ዘንድ ክልል አስራ አራት እየተባለ መጠራቱን ያልተወው አዲስ አበባ እንደ ሌሎች  አስራ ሦስቱ እንደ ኦሮምያ አማራ ወዘተ የክልል ደረጃና ሥልጣን ያስተዳደርና የፖለቲካ ቦታ ተሰጥቶት ነበር፡፡

አዲስ አበባ ክልል መሆኑ  የፌዴራሉ  ዓ.ም ሕገ መንግሥት ጸድቆ ከዚያው ዓ.ም ከነሐሴ ጀምሮ ..ሙሉ በሙሉ ሥራ  ውሏል.. ከተባለ በኋላ ነው፡፡

የፌዴራሉ መንግሥት ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው የሚለው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 እንደሌሎች ከዚህ በፊት እንደነበሩት ሕገመንግሥታት በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የሕገ መንግሥቱ የ..ርዕሰ ከተማ.. ድንጋጌ፣

1. የፌዴራሉ መንግሥት  ከተማ አዲስ አበባ መሆኑን፣

2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን እንደሚኖረውና ዝርዝሩም በሕግ እንደሚወሰን፣

3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነት ለፌዴራሉ መንግሥት እንደሆነ፣

4. የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሠረት በፌዴራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚወከሉ፣

5. ..የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል.. በማለት ደነገገ፡፡

በሽግግሩ ዘመን በነበረው የዚህ የሽግግር ፖለቲካ የበላይ ሕግ /መተዳደሪያ ቻርተር/ና የክልሎች መስተዳድር ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 7/1984 መሰረት አዲስ አበባን ጨምሮ 14 የነበሩት ክልሎች በሕገ መንግሥቱ እንደ ተወሰነው በ9 ክልሎች ሲካተቱ አዲስ አበባ የሰኔ 30/1989 ዓ.ም ቻርተር እስኪወጣ ድረስ ብዙው ነዋሪ በለመደውና በሚቀናው በክልል አስራ አራት ስም ቀጠለች፡፡ በሕገመንግሥቱ የተወሰነውም ..በዝርዝር ሕግ.. ሳይወሰንና ተፈጻሚነት የሚያገኝበት ሥርዓት ሳያገኝ በዚያው ቀጠለ፡፡ የ1989 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተር፣ ቻርተሩ ራሱ ቻርተሩ የሚፀናበትን ጊዜ ሲደነግግ ይህ ቻርተር ከሰኔ 30 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ብሎ ቢደነግግም፣ ተለምዶ በማይታወቅ አሰራርና ሁኔታ በዚያው ድንጋጌ ስር ከተጠቀሰው ዓረፍተ ነገር በኋላ በቅንፍ በተቀመጠ ዓረፍተ ነገር ../የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ በጠየቀው መሰረት በድጋሚ ጥቅምት 25 ቀን 1990 ዓ.ም ..መርምሮ አጽድቋል/.. የሚል ..ማስታወሻ.. ሰፍሯል፡፡ እንዲያምር ሆኖ ሕጉ የተፈረመው ..አዲስ አበባ ሰኔ 30 ቀን 1989 ዓ.ም.. ስለመሆኑ በሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ፊርማ ተረጋግጧል፡፡

በ1989 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቻርተር እንደተደነገገው አዲስ አበባ ማለት ..የከተማውን ክልልና በመስተዳድሩ ክልል ውስጥ የሚገኙትን 23 የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል..፡፡ የዚሁ ቻርተር አንቀጽ 33ም ከፍ ሲል በትርጉሙ ክፍል ውስጥ እንደተመለከተው ..በዚህ ቻርተር አንቀጽ 2/1/ መሠረት የሚከለለው የአዲስ አበባ ወሰን በከተማው መስተዳድርና በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በጋራ ተለይቶ የወሰን ምልክት ይደረግበታል.. የሚል ድንጋጌውን የያዘው ..በአዲስ አበባ ስለ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ልዩ ጥቅም.. በሚለው ድንጋጌው ርዕስ ስር ነው፡፡

ይህ ድንጋጌ የአዲስ አበባ ወሰን እንደሚወሰን የወሰን ምልክት የሚደረግበትም በመስተዳድሩ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጋራ ተለይቶ መሆኑን በመደንገግ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችም ጭምር አካቷል፡፡ ይህም የርዕሱ ይዘት እንደሚያሳየው ..በአዲስ አበባ ስለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ልዩ  የሚመለከት ነው፡፡

የመጀመሪያው ጉዳይ ከላይ የተገለጸው የአዲስ አበባ ወሰንን የሚመለከተው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ጋር በጋራ መወሰን ያለበት የወሰን መስመርን ሲሆን፣ የተቀሩት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫውን በአዲስ አበባ የማድረግ መብት እንደሚኖረው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለአዲስ አበባ ሕዝብ የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች በመስተዳድሩ አዋሳኝ ለሚኖረው የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ሊደርሱ የሚችሉ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በተመሳሳይ ሁኔታ የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለአዲስ አበባ ሕዝብ ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ጋር የተያያዘ የልማት ስራዎችን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መስራት የሚችለው በቅድሚያ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመመካከርና በመስማማት ይሆናል የሚሉ ድንጋጌዎች ይዟል፡፡

ሕገ መንግሥቱ ነሐሴ 15/1987 ዓ.ም የፌዴራሉን መንግሥት ርዕሰ ከተማ የአዲስ አበባን ጉዳይ አስመልክቶ በአንቀጽ 49/5 ያለው ..ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል.. በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው ቻርተር ቁጥር 87/89 አንቀጽ 33 የተባለውን ያህል ብቻ ከማለቱ በስተቀር ብዙም ሳይፍታታ ጉዳዩ በዚሁ መልክ እስከ 95 ቀጠለ፡፡ ከሁሉም በላይ አዲስ አበባ ማለት የቱ ነው የሚለው ጥያቄ ሳይወሰን የወሰን መስመር ሳያገኝ ዘለቀ፡፡

ከ89/90 ዓ.ም እና እስከ 95 ዓ.ም ድረስ ባለው ወቅት አዲስ አበባን በሚመለከት ስላለው ስለታየው ፖለቲካዊ ጉዳይ ብዙ ማለት ዝርዝሩን ለቅሞ ማሳየት ይቻላል፡፡ በአሁኑ የምወሰነው ግን የአዲስ አበባን አካላዊ መልክዓ ምድራዊ ቦታ ብቻ ስለሆነ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር በአዋጅ ቁጥሩ 361/1995 አማካኝነት የጀመርነውን ጉዳይ እንቀጥል፡፡

..የሕግ አወጣጡን ሥነ ሥርዓት ባልተከተለ አኳኋን የይዘት ለውጥ ተደርጎበት የታተመ በመሆኑ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 311/1995 ተዘርዝሮ በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ በመተካቱ በአዋጅ ቁጥር 311 እና 361 መካከል ያለውንም ልዩነት እንዲሁም የዚህን ትርጉምና እንደምታ ለጊዜው እንተወው፡፡ ስለዚህም አሁን ..ሥራ ላይ ያለውን.. አዲስ ቻርተር እንመልከት፡፡

ይህ ሕግ ..አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ረፐብሊክ መንግሥት ርዕሰ ከተማ እና  ሕብረትና የተለያዩ ዓለማቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ በመሆኑ..... የወጣ መሆኑን በመግቢያው ገልጾ በአንቀጽ 62 የከተማው አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል ግንኙነትን በተመለከተ

1/ የከተማው አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ጋር ፍሪያማ ትብብርን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ይኖረዋል፡፡  

2/ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 /5/ መሰረት የኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም የተጠበቀ ነው፡፡ ዝርዝሩ በከተማው አስተዳደርና በኦሮሚያ ክልል መካከል በሚደረግ ስምምነት ወይም በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሚወጣው ሕግ ይወሰናል ይላል፡፡

አዋጁ የከተማው አስተዳደር ሕጋዊ ሰውነት እንዳለው የከተማው ስም አዲስ አበባ እንደሆነ ወሰንን በተመለከተም ..አሁን ያለው የከተማው ክልል እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማው ወሰን የከተማው አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያደርገው ስምምነት ወይም በፌዴራል መንግሥት ይወሰናል፤ የወሰን ምልክትም ይደረግበታል.. በማለት ይደነግጋል፡፡ የ1989 ዓ.ም ቻርተር በአንቀጽ 33/2 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫውን በአዲስ አበባ የማድረግ መብት ይኖረዋል ከሚለው የቀድሞው ሕግ ድንጋጌ በስተቀር ወሰንን፣ ልዩ ጥቅምን በሚመለከት ያሉት ጉዳዮች ከሞላ ጎደል እንዳለ ቢቀጥሉም በዝርዝር ሕግ ይወሰናል የተባሉት ጉዳዮች ቁርጠኛ እልባት ሳያገኙ አሁንም በእንጥልጥል የቆዩ ጉዳዮች ሆነዋል፡፡ ይህ ክፍተት ሳይሞላ ወይም እልባት ሳያገኝ በመቅረቱ በዚህ መካከል በየጊዜው ለሚፈጠሩ የፖለቲካ ሁኔታዎች ሲጋለጥና ለዥዋዥዌ ዓይነት ጨዋታ ሲዳረግ ቆይቷል፡፡

አዲስ አበባ ዛሬም እንኳንስ ከአዲስ አበባና ከኢትዮጵያ ወደ ኢትዮጵያ በሚተላለፈው የቮይስ ኦፍ አሜሪካ.. የኦሮምኛ ቋንቋ ስርጭት ..ፖሊሲ.. መሰረት የከተማው ስም በአማርኛ  አዲስ አበባ በኦሮምኛ ፊንፊኔ ነው፡፡ በሌላ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ቋንቋ ደግሞ እንደ ተናጋሪው አቋምና የአፍ መፍቻ ቋንቋ ስያሜው/ስሙ አንዴ ፊኒፊኔ አንዴ አዲስ አበባ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ  ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ሊያስከትል የቻለ አቅም ባለው የአቋም ለውጥ የኦሮሚያ ርዕሰ ከተማ ፊኒፊኔ መሆኑ ከቀረ በኋላ የክልሉ ርዕሰ ከተማ አዳማ እንዲሆን ተወስኖ የክልሉ   ቢሮዎችና ጽህፈት  እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኞች ወደ አዳማ እንደ አዲስ መክተም የማይናቅ ችግርና ውዝግብ ካስነሳ ወዲህ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ርዕሰ ከተማ እንደገና አዲስ አበባ እንዲሆን የተወሰነው የምርጫ 97ትን የአዲስ አበባ የምርጫ ውጤትና ከዚያም ተከታትሎ የመጣውን ሁሉ ተከትሎ ነው፡፡

ይህ ጉዳይ በተለይም የአዲስ አበባ ወሰን ሳይወሰን አዲስ አበባም ከዚህ መለስ፣ ከዚያ ወዲህ ነው ተብሎ የወሰን ምልክት ሳይደረግበት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የወጡትና በተከታታይም ስራ ላይ ያሉ ሕጎች ተግባራዊ ሳይደረጉ እነሆ በጠቅላላውና በጅምሩ የሪፐብሊኩን እድሜ ያህል ቆጥረናል፡፡ አዲስ አበባ የትነው የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስካሁን ቆይተናል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ውጤት መሰረት የተቋቋመው የ3ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ፖርቲ የሚመራው መንግሥት ከተመረጠበት የአምስት ዓመት የስራ ዘመን ውስጥ 3ኛውን ዓመት በያዘበት ወቅት አንድ ከዚህ ጋር የተያያዘ የፖሊሲ ወይም የአቅጣጫ ለውጥ የሚመስል ጉዳይ ተደምጧል ብሎ መጠርጠር /መገመት/ ይቻል ይሆን?

የከተማውን ወሰን አለመወሰን የወሰን መስመር ያልተሰመረበት መሆኑ ምልክት ይደረግበታል፣ የተባለው እውን ሳይሆን መቅረቱን የተመለከተ ወይም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሴቶችና በነዋሪዎች ፎረም በታህሳስ ወር ውስጥ በሰጡት መልስ አዲስ አበባ ከሌሎች ክልሎች/ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላት ግንኙነት በተለይም ከዋሽንግተን ዲሲ ተሞክሮና ትምህርት አግኝቶ መቀመርና መታየት ያለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ መለስ ለጥያቄው የሰጡትን ቃል በቃል እጠቅሳለሁ፡፡

በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ዳር ድንበር በአግባቡ አልተለየም የተባለው በዝርዝር መለየት ያለበት ነገር አለ፡፡ በእርግጥ አሁን  አበባ ከተማ እየሰፋ ስለሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ወጣ ብሎ የኦሮሚያ ከተሞች፣ ገጠሮች የአዲስ አበባ አካል እየሆኑ ነው፡፡ ይኸ በኢትዮጵያ ብቻ ያገጠመ ሳይሆን በሌሎችም ከተሞችም የሚያጋጥም ነው፡፡

አንዳንድ ከተማ ውስጥ ሁለት ሦስት አይነት አስተዳደሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ዋሽንግተንን በምንወስድበት ወቅት ዋና ከተማዋ አለ፡፡ ነገር ግን ዋናው ከተማው አልፎ ሄዶ የሁለት የአሜሪካ ክልሎች  ጭምር ይሸፍናል፡፡ ስለዚህ የዋሽንግተን ዋና ከተማ አስተዳደርና የዋሽንግተን ከተማዋ አስተዳደር የየራሳቸው ልዩነት ያላቸው ናቸው፡፡

በዚሁም ላይ የአዲስ አበባን በምናይበት ወቅት እንደዚሁ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችል ነው የሚመስለው፡፡ ከሌሎች አገሮች ልምድ ወስደን በአዲስ  ማዘጋጃ ቤት አስተዳደር ስር ያለውና በኦሮሚያ አስተዳደር ስር ያሉት የከተማው  ተመጣጣኝ፣ ተመሳሳይ በሆነ የአስተዳደር ስርዓት ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ መፍጠር ይኖርብናል፡፡ ዳርድንበሩም በዝርዝር መጨረስ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአስተዳደር ችግሮች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ከክልሉና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር በመሆን የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ግን ከዋሽንግተን ዲሲ እጅግ በጣም የተለየች ናት፡፡ የአሜሪካን ሕገ መንግሥት የቀረጹት የአገሪቷ መስራቾች ማዕከላዊው መንግሥት በ..መናገሻ.. ወይም መቀመጫ ከተማው ወይም ስፍራ ፍፁማዊ ሙሉ ስልጣን ሊኖረው ይገባል ብለው የዚህንንም ምትክ የለሽና እጅግ በጣም ወሳኝ፣ አስፈላጊነት ተገንዝበው በሕገመንግሥቱ አንቀጽ አንድ ክፍል ስምንት ድንጋጌ ቁጥር 17 ላይ ለኮንግሬስ የሰጡት ስልጣን ተቀምጧል፡፡ በዚህ መሰረት የአሜሪካ የተወሰኑ ክልሎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሳልፈው በሚሰጡት በየትኛውም፣ አንዱ ወይም ሌላው ክልል ግዛት ውጭ በሆነ ቦታ የፌዴራሉ መንግሥት ርዕሰ ከተማውን እንዲያቋቁም ወሰኑ፡፡

የትኛው ቦታ የአገሪቱ ርዕሰ ከተማ ይሆናል፣ በማዕከላዊው መንግሥት መቀመጫ የቱ ይሁን፣ የሚባለው ጥያቄ ከፍ ያለ ሞገደኛ ሙግትና ክርክር ውስጥ ያስገባው  እኔ እቀድም እኔ እቀድም ብለው በመቀናናታቸው ነው፡፡ ፊላዴልፊያ፣ ኒውዮርክ፣ ትሪንተን፣ በልቲሞር እና ሌሎች ከተሞች ወደር በሌለው የቅናት እልክ ውስጥ ገብተው እኔ ልሁን እኔ ልሁን ብለው ተፎካከሩ ማናቸውም አልተመረጡም፡፡ አሁን ዋሽንግተን የሆነው ቦታ የተገኘው የሜሪላንድና  ከሰጡት መሬት የተወሰደው ኮንግረስም በ1791 .ም በጀ ብሎ የተቀበለው ስለዚህም የሜርላንድም፣ የቨርጂንያም ግዛት አካል መሆኑ የቀረው ቦታ ነው፡፡ ዋሽንግተን የሚገኘው እንደ አዲስ አበባ ወይም ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49/5/ እንደወሰነው በሜሪላንድ ወይም በቨርጂንያ ክልል ውስጥ በጭራሽ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ሜሪላንድና ቨርጂንያ የተባሉ የአሜሪካ ስቴቶች /ክልሎች/ ከ1791 ጀምሮ ዋሽንግተን የሆነውን ከአስር ስኩዌር ማይል እንደማይበልጥ ሆኖ አስቀድሞ የተወሰነውን መሬት ከግዛታቸው ቆርሰው አዋጥተው ሰጥተዋል፡፡ ስለዚህም የሜሪላንድም የቨርጂኒያም የግዛት ክልል መሆኑ ቀርቷል፡፡ የሜሪላንድ ወይም የቨርጂኒያ ልዩ ጥቅም በዋሽንግተን የሚባል ነገር የአሜሪካ ሕገ መንግሥት አያውቅም፡፡

ከዋሽንግተን መማር የቻለች አፍሪካዊት ከተማ እንጥራ ከተባለ የናይጄሪያ አቡጃ ነች፡፡ በ1976 ዓ.ም /በአውሮፖውያን ዘመን አቆጣጠር/ ከፌብርዋሪ 4 ቀን ጀምሮ በፀናው/ የፌዴራሉ ርዕሰ ከተማ ግዛት   አቡጃ የተቋቋመችው ቦታው የተወሰደባቸው ክልሎች አካልና ባለቤትነት መሆኑ እንዲቀር ተደርጎ ነው፡፡

ከዋሽንግተንም ሆነ ከአቡጃ መማር ሳያስፈልግ የአዲስ አበባን የወሰን መስመር ማካለል ግን ችግር ያለበት ይህን ያህል ዘመን መውሰድ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ ዋሽንግተን ዲሲ እና አቡጃ የፌዴራል መንግሥት አገሮች ርዕሰ ከተሞች በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን  ቴሪቶሪ.. በመሆናቸው ሊሰጡት የሚችሉት ተሞክሮ ደግሞ ሕገ መንግሥቱን ከማሻሻል ወዲህ ማዶ የሚፈጸም አይደለም፡፡ ሕገ መንግሥቱ ዝርዝሩ እስከ አሁን ድረስ ይፋ ሆኖ ባልተነገረና ምክንያቱም ምን እንደሆነ ባልታወቀ መነሻ ..አዲስ አበባ በኦሮምያ ክልል መሃል የሚገኝ በመሆኑ..... በማለቱ ይህ አልባት ሳያገኝ ከዋሽንግተንም ሆነ ከአቡጃ ትምህርት ማግኘት አዲስ አበባን እንደ ዋሽንግተንም ሆነ እንደ አቡጃ የፌዴራል ቴሪቶሪ ማድረግ አይቻልም፡፡

ከዚህ ቀደም ሲል በታየው 1997 ዓ.ም ልምድ መሰረት ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ብዙ አስቸጋሪ አለመሆኑን አይተናል፡፡ የሕገ መንግሥቱን የሕዝብና የቤት ቆጠራ አንቀጽ ማሻሻል የተቻለበት አካሄድ የሚያኮራ ሕገ መንግሥታዊ ..ጥሪት.. ባይሆንም ከዚህ ይልቅ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው ለሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49  ቁጥር 5 /አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል ይገኛል/ ድንጋጌ መነሻ የሆነውን ፖለቲካዊ አቋም የመለወጡ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ አዲስ አበባን ምርጫው ካስከተለው የምርጫው ውጤት እንድትዘፈቅበት ካደረገው ጊዚያዊና አቶ  በዚሁ ፎረም ላይ ከገለጹት ..የቀውስ አስተዳደር.. ብቻ ሳይሆን ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 /5/ በውጤትነት ካስከተለው ቀውስ ውስጥ ለማውጣት እውነትም ከዋሽንግተንና ከአቡጃ ለመማር መጀመሪያ ዋሽንግተንና አቡጃ ከአዲስ አበባ አኳያ ወይም ዋሽንግተንና አዲስ አበባ ወይም አቡጃና አዲስ አበባ ምንና ምን ናቸው ብሎ መጠየቅና በውል ምላሹንም ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

አቶ መለስ ..... ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ያጋጠመ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም የሚያጋጥም ነው፡፡.. ያሉት ..በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት ሦስት ዓይነት አስተዳደሮች ሊኖሩ ይችላሉ.. ብለው የተናገሩት እንደ ምሳሌም ዋሽንግተንን ያነሱበት መልስና ማብራሪያ እንኳንስ ትክክለኛነቱና እውነትነቱ የምናውቃቸው የአቶ መለስ ስለመሆኑም የሚያጠራጥር ነው፡፡ ግን የአቶ መለስ መልስ ወደድንም ጠላንም ይኸው ነው፡፡ የአቶ መለስ ቃልና መልስ ነው፡፡ ከዚህ ግን መፍትሄ አናገኝም፡፡ የአዲስ አበባን የከተማ ወሰን ከማካለል አኳያም ሆነ የአዲስ አበባን ፖለቲካዊ ስልጣን በቅጡ ከመወሰን አንጻር አዲስ አበባ የት ነች? አዲስ አበባ የት ነች? የሚለው ጥያቄ ቀውስ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀረው እኛም ይህንን ጥያቄ ሳናባራ የምንጠይቀው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡   

አቤል ከስድስት ኪሎ

 
< Prev