Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የጡት ካንሰር ሞት ከነጮቹ ይልቅ...
የጡት ካንሰር ሞት ከነጮቹ ይልቅ... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
የጡት ካንሰር ሞት ከነጮቹ ይልቅ በጥቁሮቹ እየበዛ ነው

ከአሜሪካ ካንሰር ሶሳይቲ በቅርቡ የወጣ ጥናት እንደሚያመለክተው ከጡት ካንሰር ጋር በተያያዘ የሚሞቱ የነጭ ሴቶች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን የጥቁሮቹ ግን እየጨመረ ወይም ቀድሞ ከነበረው እኩል በሆነ ሁኔታ እየቀጠለ ነው፡፡
ከጡት ካንሰር ጋር በተያያዘ የሚሞቱት የአፍሪካ አሜሪካውያን ሴቶች ጥናት ከተካሄደባቸው 37 ግዛቶች ቀንሶ የታየው በአስራ አንዱ ብቻ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1990 ጀምሮ የነጭ እንዲሁም ከ1991 ወዲህ ደግሞ የጥቁቆቹን ጨምሮ በጡት ካንሰር የመሞቱ ሁኔታ እየቀነሰ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በአፍሪካ አሜሪካውያን ጥቁር ሴቶች ላይ የመቀነስ ሂደቱ አዝጋሚ ሆኖ ታይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በጡት ካንሰር የሚሞቱ የሴቶች ቁጥር በጥቁርና በነጮቹ መሃል ልዩነት እያመጣ ሄዷል፡፡

በነጭና በጥቁር ሴቶች መሃል በጡት ካንሰር ምክንያት መሞት በ1991 ከነበረው የ18 በመቶ ልዩነት በ2004 36 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ የሴቶች በጡት ካንሰር የመሞት አጋጣሚ የቀነሰ ቢሆንም በጥቁር ሴቶች ላይ ለውጥ አለማምጣቱ ወይም እየጨመረ መሄዱ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡

በነጮቹና በጥቁሮቹ መካከል ልዩነቱን ሊያመጣ የቻለው ቅድመ ምርመራ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ አለመኖር፣ ስለ ካንሰር ያለው የግንዛቤ ልዩነትና አገልግሎቱን በአግባቡ የማያገኙ መሆናቸው ነው፡፡

የአሜሪካ ካንሰር ሶሳይቲ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ኦቲስ ብራውሊንን ጠቅሶ ጆርናል ኦፍ ካንሰር ኮውዝስ ኤንድ ኮንትሮል እንደዘገበው አዲሱ ጥናት ልዩነቱን ለማጥበብም ሆነ ችግሩን ለመፍታት ፍንጭ ያሳየ ነው፡፡ ማንኛቸውም ሴቾች የዘር፣ የገቢ መጠንና የሚኖሩበት ቦታ ሳይገድባቸው የህክምናው ተጠቃሚ መሆን አለባቸው፡፡
 
< Prev   Next >