Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ሽያጭ አዘጋጀ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕህፍት ዝግጅት ተቋም የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ሽያጭ ከመጋቢት መባቻ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እንደሚያዘጋጅ አስታወቀ፡፡ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ዓለማቀፍ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ሽያጭ (ቡክ ፌር) እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡

 

በዩኒቨርሲቲው የመጻሕፍት ዝግጅት ተቋም ዳይሬክተር ኘሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ በሰጡት መግለጫ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ዐውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት ማዕከልና ሌሎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ አሳታሚዎች በቅርብ ያሳተሟቸው መጻሕፍት ለእይታ የሚቀርቡበት፣ ደራስያን፣ መጻሕፍት አሳታሚዎች፣ አታሚዎች፣ የመጻሕፍት ሽያጭ መደብሮች፣ የቤተ መጻሕፍት ሠራተኞች ተማሪዎችና ኅብረተሰቡ የሚገናኝበት መድረክና ትልቅ የመጻሕፍት ግብይት የሚደረግበት ዝግጅት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከመጋቢት 1 እስከ 7 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (6 ኪሎ) በሚኖረው ዝግጅት የዘመኑ ደራስያን ከመጻሕፍቶቻቸው የሚያነቡበት፣ አንጋፋ ደራስያን የሕይወት ገጠመኞቻቸውን የሚያጋሩበት እንደሚሆን ያወሱት ዳይሬክተሩ፣ በመጻሕፍት ሕትመትና ሥርጭት፣ በንባብ ባህል ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት የውይይት መርሐ ግብር እንደሚኖር አስረድተዋል፡፡ በ1960 ዓ.ም. የተመሠረተውና ያልታተሙ ጽሑፎችን ተቀብሎ ለትምህርትና ለልዩ ልዩ ጥናት ጠቃሚነታቸውን በመመዘን የመማሪያና የማጣቀሻ መጻሕፍትን፣ የምርምር ሥራ ውጤቶችንና የተለያዩ የታሪክ፣ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የያዙ ጽሑፎችን በማሳተም በርካታ መጻሕፍትን ለሥርጭትና ለግብይት ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡

የቆዩና ፈርጥ የተባሉ ጽሑፎች ከወራሾቻቸው ጋር በመስማማት በማሳተም ላይ የሚገኘው ተቋም በአገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለውን የመማሪያና የማጣቀሻ መጻሕፍት እጥረትና ክፍተት ለማሟላት እየሠራ ይገኛል፡፡

በታላላቅ የአውሮፓና የአፍሪካ ከተሞች በየጊዜው የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ሽያጭ (ቡክ ፌር) የሚካሄድ በመሆኑ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ለወደፊት ዓለም አቀፍ በሆነ ይዘት በየዓመቱ በቋሚነት ለማካሄድ ዝግጅት መኖሩን ኘሮፌሰር ማስረሻ ጠቁመዋል፡፡

በሔኖክ ያሬድ

 
< Prev   Next >