Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow "ሃርድ ካንዲ"
"ሃርድ ካንዲ" Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
Imageየማዶና አዲሱና "ለዋርነ ብሮስ" ካምፓኒ የመጨረሻ የሆነው የማዶና አልበም ስም "ሃርድ ካንዲ" በማለት የተሰየመ ሲሆን እ.ኤ.አ ኤፕሪል 28 በአውሮፓ እንዲሁም በማግስቱ በሰሜን አሜሪካ ይለቀቃል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ከ2005 በኋላ ለኮከቧ አቀንቃኝ ማዶና "ሃርድ ካንዲ" የመጀመሪያዋ አልበም ይሆናል፡፡

ማዶና ላለፉት 26 ዓመታት አብራ ትሰራ ከነበረችው የሪኮርድ ካምፓኒ "ዋርነር ብሮስ" የነበራትንም ስምምነት ከአዲሱ አልበሟ በኋላ የምታቋርጥ በመሆኑ በምትኩ የኮንሰርት አስተዋዋቂ ከሆነው "ላይቭ ኔሽን" ጋር የአስር ዓመት የቅጂ ስምምነት አድርጋለች፡፡

ማዶና ከ"ላይቭ ኔሽን" ጋር ያደረገችው ስምምነት ከሁሉም ዘፈኖቿ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ አልበሞችን፣ ዲቪዲ፣ የጉዞዋንና ፊልሞችን ያጠቃልላል፡፡

ታዋቂ ኮከብ ከሆኑ አቀንቃኞች እንዲህ አይነቱን ስምምነት በማድረግ ማዶና የመጀመሪያዋ መሆኗን ቢቢሲ ገልጿል፡፡

በ2007 ማብቂያ ላይ የማዶና አዲስ አልበም "ላይኮራይስ" እንዲባል ሃሳብ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም አሳታሚው "ዋርነር ብሮስ" ስሙንና የሚለቀቅበትን ቀን ተቃውሞ ነበር፡፡

የኮከቧ አቀንቃኝ ማዶና አልበም በኒውዮርክ በ"ሮክ ኤንድ ሮል ሆል" በተያዘው ወር ይተዋወቃል፡፡ በአልበሟ ተባባሪ የሆነው ጀስቲን ቲምበርሌክ አስተዋዋቂ የሚሆን ሲሆን ሌሎች ተባበሪዎቿ ደግሞ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
 
< Prev   Next >