Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ምርጫ ኼኛ
ምርጫ ኼኛ E-mail
Sunday, 06 January 2008
ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስተኛው ሚሌንየም ገና በተጀመረበት አዲስ ሚሌንየም፣ አዲስ ምዕተ ዓመት እንዲሁም አዲስ (አንድ) አስር ዓመት የሚጀምረው ዜሮ አንድ ላይ እንጂ ዜሮ አንድ ላይ እንጂ ዜሮ ዜሮ አይደለም ብለው የሚከራከሩት እንደሚሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ሚሌንየም ዋዜማ ላይ በምንገኝበት ወቅት መላው ዓለም የሦስተኛውን ሺህ ዓመት ስምንተኛ ዓመት ተቀብሎ የመባቻውን ሳምንት እያከበረ ያሳለፈውን የ2002 ዓመት እየገመገመ ማክሰኞ የተያዘውን የ2008 ምኞትና እቅድ እየገለጸ ነው፡፡

የመባቻውን ሳምንት እያከበረ ያሳለፈውን የ2002 ዓመት እየገመገመ ማክሰኞ የተያዘውን የ2008 ምኞትና እቅድ እየገለጸ ነው፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙና ከሚገኙበት ዋና መቀመጫቸውና ጠቅላይ መምሪያቸው ሆነው አውታራቸውንም በዓለም ዙሪያ ዘርግተው መልሰው በዓለም ዳር እስከዳር የሚሰጡና የሚደመጡ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን የሰሞኖቹና የመሰንበቻቸው የሀሳብ ልዩ ፕሮግራም ዓላማ ባሳለፍነው ዓመት የሚል መጭውን አንድ ዓመት አርቆ የሚተነብይ ወይም እተንብያለሁ.. የሚል ነው፡፡

ያም ሆኖ ግን ወይም በዚሁ ምክንያት የአሁኑ ያለንበት ሳምንትና የእለት የየቀኑ ዕለታዊ ትኩስ ዜናዎች ጋዜጦች በሬዲዮና በቴሌቪዥን የተዘጋው ኩነት የመጪው ሂደትና አቅጣጫ የትንቢት መነሻ የትንበያው መጠቆሚያ መሆኑ አልቀረም፡፡ መላው ዓለም አዲሱን 2008 የተቀበለው ከአሮጌው ዓመት የመሰናበቻ ሳምንት ጀምሮ የመገናኛ ብዙሃንን የግንባር ቀደም ቦታ የያዙትን ሌሎችን መደበኛ አርዕስተ ዜናዎች ከሞላ ጎደል ከደረጃቸው እንዲወርዱ ያደረጉትን የፖኪስታን እና የኬንያ ዜናዎችን አንግቦ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የቀድሞው የፓኪስታን የሁለት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር በወቅቱ የፓኪስታን ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ መገደል የ2008 የመጀመሪያው ወር በገባ በስምንተኛው ቀን ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ምርጫ እጣ ፋንታ አንዱ ታላቅ አብይ ዜና ነው፡፡
ሌላው ከዚያው ከፓኪስታን ሁኔታ ጋር ተፎካካሪ ሆኖ መላውን ዓለም በማነጋገር ላይ ያለው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነው፡፡

የዓለም የመገናኛ ብዙሃን አንድን በዓለም የተከሰተ ድርጊት የዜና ፋይዳ አለው የሚሉት ስለዚህም ዜና የሚያደርጉበት ብሎም ዜና ብለው ከጠሩት ጋር አወዳድረው ደረጃ የሚሰጡበት አሰራር ራሱ አይታማም የሚባል አይደለም፡፡ ይልቁንም አንዱ የሃሜቱ መገለጫ ይህ ራሱ የዜና ርዕስ ሆኖ የዜና ፋይዳ አግኝቶ የሚወራና የሚዘገብ አለመሆኑ ነው፡፡ አንዳንዴና አንዳንድ ቦታ የመገናኛ ብዙሃን ራሳቸውና ዜናቸው የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስበው ቢገኙ የዜና ፋይዳ አግኝተው ሊዘገቡ የማይችሉ ቢሆንም ይህ ግን መደበኛውና የተለመደው አሰራር አይደለም፡፡

የኬንያ ምርጫ ከፓኪስታን የቡቶ ግድያ ጋር እየተፎካከረ የዓለምን የመገናኛ ብዙሃን አጨናንቆ በሰነበተበት በተለይም በሳምንቱና በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተቻለንን የተመቸንን ያህል የተለያዩ ሬዲዮና ቴሌቪዥኖችን ተከታትለናል፡፡ የኬንያ ምርጫ ጉዳይ ይህን ያህል ከፍ ያለ ተፎካካሪና የጎላ ቦታ የያዘው በሌላም ጊዜ ከሚታወቀው መደበኛ ምክንያት በተጨማሪ በተለይም ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ ስልጣን ላይ ካለውና ለሁለተኛ የፕሬዚዳንትነት የሥልጣን ዘመን ከሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክሮ ፕሬዚዳንት ሆኖ የመመረጥ እድል አለው የሚባል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና እጩ ተፎካካሪ በመኖሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ይበልጥ ግን ጉዳዩ የአለምን ትኩረት እንዲስብ ያደረገው አሮጌው አመት ከመሰናበቱ ከአራት ቀን በፊት በሰላም የተካሄደው ምርጫ በተለይም የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት በሚነገርበት ወቅት በታየው ስለመታየቱም ብዙዎች ታዛቢዎች ባረጋገጡት የምርጫ ሂደት እንከንና ችግር የተነሳ የተቀሰቀሰው ሁከት፣ ሁከቱም ያስከተለው ጥፋትና ሞት ምክንያት ሆኖ ነው፡፡

የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ኬንያንና የኬንያን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዜናቸውና የዘገባቸው መግቢያና ዋነኛው ርዕሰ ጉዳይ አድርገው በሚያስተጋቡበት ምዕርባውያን መንግሥታት ጉዳዩ ያሳሰባቸው እንደሆነ እየገለጹ ባለበት ወቅት የተደመጠው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዓለም እንዴት ሰነበተች ሳምንታዊ ፕሮግራም የኬንያ ምርጫ ያለ አንዳች እንከን መጠናቀቁን ፕሬዚዳንት ሞዋይ ኪባኪ የምርጫው አሸናፊ ሆነው ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አሰማን፡፡ በቀጥታ ስርጭት በማይተላለፍ ምናልባትም ከውጭ ሆነን እንደምናስበውና እንደምንገምተው ከሚተላለፍበት ቀን ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ ሪከርድ ተደርጎ ሰዓቱንና ቀኑን ጠብቆ በሚተላለፍ ፕሮግራም የኬንያው ምርጫ ያለአንዳች እንከን ተጠናቀቀ ብሎ መዘጋጀትና መዘገብ የሚገርም ቢሆንም ከሁሉም በላይ የሚደንቀው ግን ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሳምንታዊ ዘገባ በሚተላለፍበት ወቅት የኬንያ በተለይም የዋና ዋና ከተማና የአገሪቱ ከተሞች ምድር በርካታ እንደ ቁና ይንቀረቀብ የነበረ መሆኑ በያቅጣጫው ይሰማ የዓለምም ዜና ይኸው መሆኑ ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና ተዘጋጅቶ ተቀምጦ ሰዓቱ ሲደርስ የተላለፈው ከአሜሪካ መንግሥት ለኪባኪ የተላከው የእንኳን ደስ ያለዎት የደስታ መግለጫ መልዕክትም በራሱ በአሜሪካ መንግሥት መልሶ ተሳበ፡፡

የአሜሪካ አስተዳደር እና ስቴት ዲፓርትመንት ጉዳዩ በእጅጉ የሚያሳስበው መሆኑን ገለፀ፡፡ በዚህ በተመሳሳይ ወቅት በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚሄደው የኬንያ ምርጫ ሁከትና ፖለቲካ ውስጥ ያንኑ ያህል የሞተው ሰው ቁጥር ሪከርድ እየሰበረ መሄዱ በሚታይበት ሰዓት የኬንያ የምርጫ ኮሚሲዮን የውጤት መግለጫ ጭምር በቀጥታዊ በሕይወት እንመለከትና እንከታተል ነበር፡፡

የምርጫ ከሚሲዮኑ ውጤት ሊገለጽ በተያዘውና በተዘጋጀው ቦታ የኮሚዮሲኑ ሊቀመንበር መግለጫ ተጀምሮ ሲቋረጥ እንደገና ሲቀጥል በዚህ መካከል የተቃዋሚው ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ መግለጫ ሲሰጡ የምርጫ ኮሚሲዮኑ የቆጠራ ውጤት አስተዋቂ ባለስልጣኖች መካከል አንዳንዶቹ በእጃቸው የያዙትን የመጭበርበር ማስረጃ ሰነድ እያሳዩና የኮሚሲዮኑን ውሳኔ ሲቀውጡ አይተናል፡፡ ስምተናል፡፡

በዚህ ብቻ ሳያበቃ ፕሬዚዳንት ሞዋይ ኪባኪ ፕሬዚዳንት ሆነው በጥድፊያ ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ በሌላ ወገን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ አዲንጋ ለብቻቸውና በተለይ ራሱን የቻለ የቃለ መሀላ አፈጻጸም ስርዓት የሚካሄድ መሆኑን ሲገልጹ ሰምተናል፡፡ የኬንያ መንግሥት አነጣጥረህ ተኩሰህ ግደል ብሎ ለአገሪቷ የፀጥታ አስከባሪ ኃይል ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመስጠቱ ይኸው መንግሥት በቀጥታ ስርጭት ያላቸውን የመገናኛ ብዙሃንን እንዲያስተላልፍ ስለማገዱ የሰማነው ኢትዮጵያ ውስጥ ..ዲሺ.. የሌለው ሰው የኬንያ ምርጫ ያለአንዳች እንከን ተጠናቀቀ ተብሎ እየተነገረው እያለ ነው፡፡ ..ያለአንዳች እንከን.. በተጠናቀቀው ምርጫ ምክንያት እስከ ማክሰኞ ድረስ ከሁለት መቶ ያላነሱ ዜጎች አብዛኞቹ በፖሊስ ተገድለዋል፡፡ ፖሊስ እንደምን አድርጎ እንደሚደበድብ በሌላ አነጋገር የፖሊስን የሰብዓዊ መብት አያያዝን በቴሌቪዥን አይተናል፡፡

በዓለም እንዴት ሰነበተች የሰማነውን ..የኬንያ ምርጫ ያለአንዳች እንከን ተጠናቀቀ.. ዘገባ በእቅድ ፖለቲካዊ ክፍት ይዞ የተሰራጨ ነው ብዬ አላምንም፡፡ አልጠረጥርምም፡፡ ሙያዊ ብቃትንና ድርጅታዊ አቅምን ግን ያጋልጣል፡፡ ከእንዲህ ያለ ፖለቲካዊ ትኩሳቱ ከሩቁ ከሚፋጁ ጋር የተያያዘ ሲሆን ደግሞ እምነትን ይበልጥ ያሳጣል፡፡ የኢትዮጵያን የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ማመን ቀብሮ ነው የሚለውን ከተናገረ የቆየ አባባል ይበልጥ ያጠናክራል፡፡

አዲስ አበቤዎች ከተጨባጭ ተሞክሮ አግኝተው ይህንኑ አዳብረው በፈጠሩት አንድ ቀልድ ውስጥ የሚኖሩ አንዲት እናት የሆኑትንና አሉ የተባሉትን ባጭሩ ላጫውታችሁ፡፡ ሴትዮዋ የአውሮፓ ህብረት ዩሮን የመገበያያ ገንዘቡ ከማድረጉ በፊት በነበረው ጊዜ ውስጥ ጣሊያን የምትኖር ልጃቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ገንዘብ የላከችላቸው መሆኑን ስልክ ደውላ ትነግራቸዋለች፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መላኳን ገልጻ ሰኞ ወደ ባንክ ሄደው ገንዘቡን እንዲያወጡ ትነግራቸውና በጸሎታቸው እንዳይረሷት ጠብ የማይለው ምርቃታቸውም እንዳይለያት አሳስባ ትሰናበታቸዋለች፡፡ ሴትዮዋም ሰኞ እስኪደርስ ድረስ እረፍት አላደረጉም፡፡ እንቅልፍም አልወሰዳቸውም፡፡ ተበድረው ተለቅተው ወዳጅ ዘመድ ሰብስበው ለእድር ለማህበር ተናግረው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ልጃቸው እንደላከችላቸው ገልፀው በተበደሩትም እንደ አቅማቸው ከፍ ያለ ድግስ አድርገው አካባቢያቸውን ሰው ሁሉ አብልተው አጠጥተው እሳቸውም በፋንታቸው ወዳጅ ዘመድ በፀሎት እንዳይረሳት ይማጠናሉ፣ ይለምናሉ፡፡ ቀኑ ደርሶ ባንክ ይሄዳሉ፡፡ ባንኩ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የጣሊያን ሊሬ የተላከላቸው መሆኑን ገልጸው ምንዛሬውን አስረድቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ያወጡትን የጥቂት መቶ ብሮች ብድር እንኳን የማይሸፍን ብር ቆጥሮ ይሰጣቸዋል፡፡ እርር ድብን ብለው አፍረው ሰው ማየት ፈርተው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ይህ በሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከእለታት አንድ ቀን እንደልማዳቸው ጣሊያንን ሊሬን ሲረግሙ የቴሌቪዥኑ ዜና ..ጣሊያን ውስጥ በደረሰ የባቡር አደጋ ሦስት መቶ ሰዎች ሞቱ፣ ከዚያ በላይ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰ.. ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ኤጭ ይሉና ይህን ጊዜ የሆነ ሰው ወድቆ ትንሽ ቆስል ደርሶበት ይሆናል፡፡ የጣሊያኖችንም የቴሌቪዥኑንም ነገር ማመን ቀብሮ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የተሳሳትኩት ይበቃኛል አሉ ይባላል፡፡

የምርጫው ጉዳይ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የተለየ ነው፡፡ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ የኬንያ ምርጫና ሁከት ከኛ ምርጫ 97 ጋር በእኛ ምርጫ ውስጥ በዚያው መነፅር በኩል የሚታይ መሆኑ ነው፡፡ ሰው ብዙ ነገር እያዛመደ ያስታውሳል የተለያዩ ነገሮችን እያነጣጠረ እያመሳሰለ ያዛምዳል፡፡ ለአዲስ የማሟያና የወረዳና የቀበሌ ምርጫ ቀጠሮና አጀንዳ ፊት ለፊት ያለበት ሕዝብ ከምርጫ 97 በኋላ ከደረሰበት ቁስል አልዳነም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው የአንድ ወቅት (የቅንጅት መሪዎችን በይቅርታ መፈታት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ) ካምናው እንደገለጽኩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በህዝቡ ..ሶፍትዌር.. ውስጥ አሁንም ገና እርም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያሉት ሕዝቡ በሰላማዊ ተቃውሞና በመንገድ ላይ ነውጥ መካከል ያለውን ልዩነት እስኪረዳው ድረስ ጊዜ መውሰዱ የማይቀር ነው የሚል ነው፡፡ በህዝቡ በኩል ደግሞ መንግሥት በነዚህ ሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ራሱ እስኪረዳ እንደፈለገውና የፈለገውን ይኸ ነውጥ ነው፣ ይኸ ዴሞክራሲ ነው ማለቱንና መደባለቁን እስከቀጠለ ድረስ ..መፍትሄው.. አርፎ መቀመጥ ነው ባይ ነው፡፡

የኬንያ ትኩስ ዜናና ዘገባ ከዚህ በላይ ብዙ ነገር እንደገና እንድንገመግም ያደርገናል፡፡ በምርጫው ሂደት ውስጥ ያየናቸውን ሰፊና ዝርዝር ..እንከኖች.. ያስታውሱናል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ምክንያት አዲስ አበባን የሚያክል የአገር መዲና ብቻ ሳይሆን አሁንም ድሬዳዋና አዋሳ በጊዜያዊ አስተዳደር የሚተዳደሩበትን ምክንያት መለስ ብለን እንድናይ ይገፋናል፡፡ በአዲስ አበባም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ፓርላማ ያለመግባትን ውሳኔ መርጠው የወሰዱት የቅንጅት ፓርቲ መሪዎች ስህተት ቀስ እያለ እየገባን ሲመጣ ይታየናል፡፡ አዳሜ (በኢትዮጵያ ህዝብ አምሳል) ኢህአዴግን ጠልቶ የሰጠው ድምፅ ለቅንጅት ፍቅር አለመሆኑ ቀስ እያለ እየገባን መጥቷል፡፡ አሁን የቅንጅትን መሰነጣጠቅ መፈረካከስ እያየንም እንኳንም አጠቃላዩን ምርጫ ቅንጅት አላሸነፈም ወይም አሸነፈ አልተባለም፡፡ እውነትም እግዜር ይወደናል፡፡ ሳይደግስ አይጣላም ማለት እውነት ነው ማለት ጀምረናል፡፡


ፍፁም ዘገብርኤል

 

 
< Prev   Next >