Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow በካሜሩን በተነሳ አመፅ አሥራ ሰባት ሰዎች ተገደሉ<
በካሜሩን በተነሳ አመፅ አሥራ ሰባት ሰዎች ተገደሉ< Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
በካሜሩን የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ አሥራ ሰባት ሰዎች በፖሊስ መገደላቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
የካሜሩን ኘሬዚዳንት ፓል፡ቢያ የሀገሪቱ የተቃዋሚ ኃይሎች በአመፁ ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው በሀገሪቱ የተከሰተው የኑሮ ውድነት በተለይ በምግብና በነዳጅ ላይ የተከሰተው የዋጋ ንረት አመፅ መቀስቀሱን ገልፀዋል፡፡

ኘሬዚደንቱ አመፁን ለማስቆም የፖሊስ ኃይል መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው መንግሥት አላስፈላጊ ኃይል በመጠቀሙ የሟቾች ቁጥር ከፍ ማለቱን ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ ከተሞች በኑሮ ውድነት ምክንያት የተቀሰቀሰው አመፅ ወደ ፖለቲካዊ ተቃውሞ እያመራ መሆኑ ዘገባው ያመለክታል፡፡

የእስራኤል የጦር ኃይል በጋዛ ጥቃት ሰነዘረ

የእስራኤል የጦር ኃይል በጋዛ በከፈተው ጥቃት በትንሹ ሠላሳ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የአሶሲየትድ ኘሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡

በዘገባው መሠረት የእስራኤል የጦር ኃይል ባለፈው ረቡዕና ሀሙስ የከፈተው ጥቃት በአየር ኃይልና በከባድ የጦር መሳሪያ የታገዘ ነበር፡፡ የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ ጥቃቱ በቅርቡ በደቡባዊ እስራኤል ለደረሰው የሮኬት ጥቃት ምላሽ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዘገባው መሠረት በጋዛ በደረሰው ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገልጿል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሁድ ኦልመርት “ፍልስጤማውያን በሰላማዊ እስራኤላውያን ላይ የሚያደርሱትን የሮኬት ጥቃት ካላቆሙ የሰላም ስምምነት አይታሰብም” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ “የፍልስጤማውያን ሕልውና በእስራኤል ውሳኔ ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም፡፡ እስራኤል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የምታደርሰው ጥቃት ሊወገዝ ይገባል” በማለት በመካከለኛው ምስራቅ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አባል የሆኑት ሀና አሺርዊ የእስራኤልን ድርጊት ኮንነዋል፡፡

ኩባ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ህግጋትን ፈረመች

ኩባ ሁለት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ህግጋትን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር ተፈራረመች፡፡ ስምምነቱ አዲሱ ኘሬዚዳንት ራውል ካስትሮ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የተደረገ ከፍተኛ ለውጥ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ኩባ የፈረመችው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድንጋጌ በሀገሪቱ ያለውን የሰብአዊ መብት አፈና እንደሚፈታ ተጠቁሟል፡፡ የኩባ ኘሬዚዳንታዊ ለውጥ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ነፃነት እንዲሁም የሰብአዊ መብት አከባበር እንደማያሻሽል ተጠቁሟል፡፡

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊኘ ፔርዝ ሮኩ የኩባ ህዝብ በሀገሪቱ እ.ኤ.አ በ1959 በተደረገው አብዮት ሰብአዊ መብቱን ያገኘ መሆኑን ጠቁመው፤ ከተመድ ጋር የተደረገው ስምምነት የዓለም አቀፉን ውሳኔ መደበኛ በሆነ መልኩ በሀገሪቱ ህግ ውስጥ ለማካተት የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >