| የሳሙና ዋጋ ጭማሪ በነዋሪዎች ላይ ጫና ፈጠረ |
|
|
| Sunday, 02 March 2008 | |
|
በሳሙና የችርቻሮ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ በኑሯአቸው ላይ ጫና እንደፈጠረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ የሳሙና ፋብሪካዎች በበኩላቸው በጥሬ እቃ መወደድ ምክንያት የተወሰነ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
ከታህሳስ ወር ጀምሮ በአማካኝ ከአንድ ብር እስከ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ይሸጥ የነበረው የልብስ ሳሙና በአሁኑ ወቅት ከአራት ብር እስከ አምስት ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ፣ መንግሥት በሳሙናና በሌሎች ሸቀጦች ላይ ከነፃ ገበያው የውድድር መርህ ውጪ ጭማሪ በማድረግ አላግባብ ለመበልፀግ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችን ሊቆጣጠርና ለችግሩ መፍትሄ ሊያፈላልግ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ (ዋኢማ) ኩባንያው 245ሺህ የቁም እንስሳት ለዓለም ገበያ ሊያቀርብ ነው በተያዘው የበጀት ዓመት 245ሺህ የተለያዩ የቁም እንስሳትን ለዓለም ገበያ እንደሚያቀርብ ኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ የተሰማራው ሻግ ኩባንያ አስታወቀ፡፡ ኩባንያው እስካሁን 64ሺህ የቁም እንስሳትን ለዓለም ገበያ ማቅረቡንም አመልክቷል፡፡ ሻግ በመባል የሚታወቀው ኩባንያ 200ሺህ በጐችን፣ 30ሺህ በሬዎችንና 15ሺህ ግመሎችን ወደ ግብፅ እንደሚልክ፣ ከሚላኩት የቁም አንስሳት በግምት 20 ሚሊዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፆ፣ ኩባንያው ባለፉት ሰባት ወራት 50ሺህ በጐችን ስምንት ሺህ በሬዎችንና ስድስት ሺህ ግመሎችን ለውጭ ገበያ ማቅረቡን፣ በቀሪዎቹ አምስት ወራት 179ሺህ የቁም እንስሳት እንደሚላኩና በሙስሊሞች የረመዳን ፆም ዋጋ ስለሚጨምር እቅዱ እንደሚያሳካ ገል..ል፡፡ (ኢዜአ) ለ173ሺ ሰዎች የትራኮማ በሽታ ሕክምና ተሰጠ በጐንደር ዙሪያ ወረዳ በካርተር ማዕከል ድጋፍ ለ173ሺህ ሰዎች የዓይን ትራኮማ በሽታ በመከላከያ መድሃኒት እደላና የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምና መስጠቱን የወረዳው የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በዓይናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ከአራት ሺህ በላይ የዓይን ህሙማን በቀዶ ህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት የዓይን ቆብ ቀዶ ክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን፣ ለሌሎች የዓይን ህሙማን በቅባትና በፈሳሽ መልክ የተዘጋጁ መድሀኒቶችን በየአቅራቢያቸው በተቋቋሙ የህክምና መስጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ (ኢዜአ) ለሲቪል ማህበራት የፀረ ሙስና ሥልጠና እየተሰጠ ነው የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የአገልግሎት አድማሳቸው ሰፊ ከሆኑ 17 የሲቪል ማህበራት ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ሥልጠናው በሙስና ፅንሰ ሐሳብ፣ በሙስና መከላከያ ስትራቴጂዎችና ስልቶች፣ በሙስና ወንጀሎች፣ በሥነ ምግባር መርሆዎች፣ በመከላከያ ስልቶችና በአሠራር ሥርዓት ጥናት ላይ ያተኮረ መሆኑን፣ ሥልጠናዎቹ በአንድ መስሪያ ቤት ለሚገኙ በርካታ ሠራተኞች በአንድ ጊዘ የሚሠጡ ሳይሆኑ፣ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች መሆናቸውን ገል..ል፡፡ (አዲስ ዘመን) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |