| ግዮን ሆቴልን በሽርክና ለመግዛት... |
|
|
| Wednesday, 05 March 2008 | |
|
ግዮን ሆቴልን በሽርክና ለመግዛት ጥያቄ እየቀረበ ነው የግዮን ሆቴልን በሽርክና ለማስተዳደር የደቡብ አፍሪካ የህንድና የኩዌት ኩባንያዎች ጥያቄ ማቅረባቸው ታወቀ፡፡ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶቸ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ አስራ ሶስት የልማት ድርጅቶችን ለመሸጥ ጨረታ አወጣ፡፡
የኤጀንሲው አጋር ፍለጋ ዳይሬክቶሬት ክፍል ኃላፊ አቶ ዳንኤል በንቲ ከተጠቀሱት አገራት የመጡ ኩባንያዎች ጥያቄውን እንዳቀረቡ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ኤጀንሲው ኩባንያዎቹ ፕሮፖዛል አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መጠየቁን አስታውቋል፡፡ በሌላ ተመሳሳይ ዜና ኤጀንሲው 13 የልማት ድርጅቶችን በጨረታ እንደሚሸጥ ይፋ አድርጓል፡፡ ኤጀንሲው ባወጣው ጨረታ እንዳስታወቀው የልማት ድርጅቶቹ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የሚገኙ ሲሆን ኤጀንሲው የተጠቀሰትን ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በመግዛት ለመምራትና ለማስፋፋት ፈቃደኛ ለሆኑና አቅም ላላቸው ባለሃብቶች ወይም ድርጅቶች ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ድርጅቶቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ባለሃብቶች ወይም ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶችን ለመውሰድ አስፈላጊውን ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ ኤጀንሲው ከጥር 19 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ማስተናገድ እንደጀመረና ጨረታው መጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም እንደሚከፈት ገልጿል፡፡ ጨረታ የወጣባቸው ድርጅቶች ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ቁጥር 1 ድሬዳዋ፣ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ቁጥር 2 /ካራማራ/ ድሬዳዋ፣ ሐረር ራስ ሆቴል ሐረር፣ ባሌ ጎባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎባ፣ ኮልፌ የቤት ዕቃዎች ፋብሪካ አዲስ አበባ፣ ኢትዮ-ፕላስቲክ አክስዮን ማኅበር አዲስ አበባ፣ የሸክላ ምርቶች አክስዮን ማኅበር አዲስ አበባ፣ ዓባይ ቴክኒክና ንግድ አክስዮን ማኅበር አዲስ አበባ፣ አዲስ መለዋወጫ ዕቃዎች አስመጪና አከፋፋይ አ.ማ አዲስ አበባ፣ የካቲት ወረቀት ፋብሪካ አዲስ አበባ፣ አዲስ አበባ ፎምና ፕላስቲክ አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ኮምፔንሳቶ ፋብሪካ አዲስ አበባ፣ ኮንስትራክሽንና የቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንተርፕራይዝ አዲስ አበባ፡፡ ናቸው፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |