Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ተመድ በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ...
ተመድ በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ... Print E-mail
Wednesday, 05 March 2008
ተመድ በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ እንደሚከሰት አስታወቀ
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ በቦረና አካባቢ ከፍተኛ ድርቅ እንደሚከሰት ማስታወቁን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡
ተመድ ባለፈው አርብ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ባለፉት ህዳርና ታህሳስ ወራት ዝቅተኛ የዝናብ መጠን መመዝገቡ በአካባቢው ድርቅ እንደሚከሰት አመላካች መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተመድ የሰብአዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት በአካባቢው በተከሰተው በዝናብ እጥረት ምክንያት በሽታ መከሰቱንና የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡

በአካባቢው የተሰማራው የጥናት ቡድን በአካባቢው የቀንድ ከብቶች ላይ የሚታየው ዝቅተኛ የጤንነት ደረጃና የሞት አደጋ እንዲሁም ሰዎችን እያጠቃ ያለው ድንገተኛ በሽታ፤ ከዝናብ እጥረት ጋር ተዳምሮ የአካባቢውን ሁኔታ አሳሳቢ ያደረገው መሆኑን ገልጿል፡፡

በተመድ መግለጫ መሠረት በአካባቢው አራት ሺ ስድስት መቶ ስልሳ የቀንድ ከብቶች በያዝነው ወር ውስጥ መሞታቸው ታውቋል፡፡

የቦረና አካባቢ የአስተዳደር ተጠሪዎች በአካባቢው በተከሰተው ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ምክንያት የከብቶች ጤንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና የከብቶች በሽታ በአካባቢው በስፋት መከሰቱን ገልፀዋል፡፡

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በአካባቢው የሚታየው ሁኔታ ከፍተኛ ሰብአዊ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል በመጠቆም መንግሥትና የእርዳታ ድርጅቶች ጣልቃ በመግባት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >