Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow በታሰሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ...
በታሰሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ... Print E-mail
Wednesday, 05 March 2008
በታሰሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ኃላፊዎች ምትክ ተሾሙ

ከብሄራዊ ባንክ በተጭበረበረ ወርቅ ተጠርጥረው ከታሰሩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካከል በአምስቱ ኃላፊዎች ምትክ ሌሎች ሃላፊዎች መሾማቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለፁ፡፡
እንደ ምንጮቻችን ገለፃ፣ ከህዳር 24 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙት የገንዘብ መረጣና ቆጠራ ዋና ክፍል ሃላፊ የነበሩት አቶ መሸሻ ዳዲ ወደ የትረዠሪ (ኢሹ) ዋና ክፍል ሀላፊ፣ የገንዘብ ቤት ዋና ክፍል ተጠባባቂ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወ/ጊዮርጊስ ነጋሳ የገንዘብ መረጣና ቆጠራ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ዋና ከፋይ (Senior Teller) የነበሩት እልፍነሽ ክፍሉ፣ የገንዘብ ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ፣ በገንዘብ መረጣና ቆጠራ ክፍል የቡድን መሪ የነበሩት አቶ ግርማ መንግሥቱ የትሬዠር ተጠባባቂ ዋና ክፍልና በሪዘርቭ ማኔጅመንት ዋና ክፍል ሀላፊ የነበሩት አቶ አበበ ሰንበቴ የከረንሲ ማኔጅመንት መምሪያ ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተሹመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተጭበረበረው ወርቅ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት፣ አቶ አህመድ ሰዒድ (የውጭ ምንዛሪና ስታትስቲክስ) ሞኒተሪንግ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ..፣ አቶ አለማየሁ ካሳሁን (የገንዘብ ቤት ምክትል ዋና ክፍል ኃላፊ..፣ አቶ ፍቃዱ ሉሉ (የገንዘብ መረጣና ቆጠራ ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ..፣ አቶ ጨምዴሳ ሂርጳ (የትሬዠር ዋና ክፍል ምክትል ተጠባባቂ..፣ አቶ ፍቃዱ ዳፋ (በከረንሲ ማኔጅመንት የውስጥ ቁጥጥር ሠራተኛ..፣ አቶ ዋሱ አደም (የከረንሲ ማኔጅመንት ሥራ አስኪያጅ) እና አቶ ተክለሀና ዘለቀ (የትሬዥር ዋና ክፍል ኃላፊ) መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በታምሩ ጽጌ
 
< Prev   Next >