Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow የሴቶችን የወሲብ ፍላጐት ማጣት የሚያስወግድ መድ
የሴቶችን የወሲብ ፍላጐት ማጣት የሚያስወግድ መድ E-mail
Sunday, 06 January 2008
የወሲብ ፍላጐትን በሚያሳጣ ችግር /ሃይፖአክቲቭ ሴክሹአል ዲዛየር ዲስኦርደር/ ለሚሰቃዩ ሴቶች መፍትሄ እንደሚሆን የተነገረለት መድኃኒት በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ተነገረ፡፡ በሚቀጥሉት ወራት ለህመምተኞች እንደሚደርስ የአሶሽየትድ ኘሬስ ዘገባ ገልጿል፡፡

ከአሜሪካውያት ሴቶች አንድ ሦስተኛው በዚሁ በወሲብ  ማጣት በሽታ እንደሚሰቃዩም በዘገባው ተገልጿል፡፡

በቅባት መልክ የተዘጋጀውና ..ሊቢጄል.. የሚል ስያሜ የተሰጠውን መድኃኒት ደህንነትና ውጤታማነት ለመፈተሽ የቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች 99 የአሜሪካ የጤና ተቋማት ጋር ተባብሮ ሠርቷል፡፡

የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ፈቃድ ከተገኘ በኢሊኖይስ የሚገኘው ..ባዮሳንቴ ፋርማሱቲካልስ.. የተሰኘ ተቋም መድኃኒቱን የወሲብ ፍላጐት ማነስ አለብኝ ብላ ለምትል ሴት ሁሉ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

የወሲብ ፍላጐትን ማጣት የዘር ማኩረቻ /ኦቫሪ/ በቀዶ ጥገና ባስወገዱ እንዲሁም ለማረጥ በተቃረቡ ሴቶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ዘገባው ጠቁሟል፡፡
 
ሊቢጄል የተሰኘው ቅባት በሴቶች የላይኛው ክንድ ላይ በመቀባት ጥቅም ላይ ሲውል በቅባቱ ውስጥ ያለው ቴስቴስትሮን በደም ዝውውር ውስጥ በመግባት ጉልበት እንዲያገኙና የወሲብ ፍላጐታቸው እንዲጨምር የሚያደርግ አሠራር መሆኑንም ዘገባው ገልጿል፡፡

 
< Prev