|
የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መንደር
|
|
|
|
Wednesday, 05 March 2008 |
 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መንደር ይህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መንደር (Ethiopian Millennium Village) የሚያሳይ ዲዛይን ሲሆን በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ በሐያት ሆስፒታል ፊት ለፊት በ160ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ይገነባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ቪሌጅ አድቬንቸር ከተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም መታሰቢያ በሚያስገነባው በዚሁ መንደር የየብሔር ብሔረሰቡ ባህል፣ እሴት፣ ቋንቋ፣ አኗኗር እና ልማት ያንፀባርቃል ተብሏል፡፡ ግንባታውም በ50 ሚሊዮን ብር ወጪ ይከናወናል ተብሎ እንደሚገመት የኢትዮጵያ ቪሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሙራድ መሐመድ ገልፀዋል፡፡ በመንደሩ ግንባታ ጉዳይ የሚመክር ስብሰባም ነገ በሸራተን ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
|