Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ኢሕአዴግ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን...
ኢሕአዴግ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን... Print E-mail
Wednesday, 05 March 2008
Image
አቶ ኩማ ደመቅሳ
Image
ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
ኢሕአዴግ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን በዕጩነት አቀረበ


በመጪው ሚያዚያ ወር በሚካሄደው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ኢሕአዴግ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን በዕጩነት ማቅረቡን ይፋ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ኮሚቴ "ህዳሴ" በሚል ስም በሚያሳትመው ጋዜጣ ላይ ይፋ እንዳደረገው ለተወካዮች ም/ቤት ማሟያ ምርጫ ካቀረባቸው 14 ዕጩዎች መካከል የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ይገኙበታል፡፡ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ቤት ካቀረባቸው 138 ዕጩዎች መካከል የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ መላኩ ፈንታ፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስምዖን መቻሌ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪ ለተወካዮች ም/ቤት ማሟያ ምርጫ የሐገር ፍቅር ቲአትር ቤት ሥራ አስኪያጅ አርቲስት መንበረ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃራ ኃ/ማርያም፣ ሠዓሊ ግርማ አገኘሁ እንግዳ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንበረ ፓትርያርክ የሕግ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኮንን በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

አቶ ደስታ ኃ/ማርያም የአዲስ አበባ ምርጫ አስተባባሪ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ለተወካዮች ም/ቤት ማሟያ ምርጫ የሚካሄድባቸው 14 መቀመጫዎች ኢሕአዴግ 14 ዕጩዎችን ሲያቀርብ፣ ተቃዋሚዎች በድምሩ 108 ዕጩዎችን አቅርበዋል፡፡

በተመሣሣይ ሁኔታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካሉት 138 መቀመጫዎች ኢሕአዴግ 138 ዕጩዎችን ሲያቀርብ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድምሩ 327 ዕጩዎችን ማቅረባቸውን አቶ ደስታ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ኢሕአዴግ ወደ 2ሺ 970 ዕጩዎችን ያቀረበ መሆኑን፣ ተቃዋሚዎች እና ግል ተወዳዳሪዎች በድምሩ ከ90 የማይበልጥ ዕጩዎችን ማቅረባቸውን በዚህም ምክንያት ክ/ከተሞች ላይ ውድድሩ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >