| አባይን ለመጠቀም በቅድሚያ አቅምን ማጠናከር |
|
|
| Wednesday, 05 March 2008 | |
|
ጥቁር አባይ (ናይል) 1ሺህ 370 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ አባይንም ሆነ ሌሎች ወንዞቻችንን በአግባቡ ለመጠቀም ዘለቄታ ያለው ስትራቴጂ መቅረጽና የአሰራር ቅደም ተከተል ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 23 ቀን 2000 እትም "እኔ የምለው" ገጽ "መገደብ ያለበት አባይ ብቻ ሳይሆን ሃብታችንም ነው" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሁፍ ይህንን እንዳነሳ አስገድዶኛል፡፡
የጊዜና የአቅም ጉዳይ እስካልሆነ ድረስ አባይን መጠቀም የግድና አይቀሬ ነው፡፡ ይህንንም ስናስብ የገናሌ፣ የተከዜ፣ የአዋሽ፣ የዋቢሸበሌ ወዘተ. ወንዞቻችንም ውኃ መጠቀም እንደሚኖርብን መዘንጋት የለብንም፡፡ ከዚህ አኳያ አባይን ከመገደባችን ወይም ለመጠቀም ከመንቀሳቀሳችን በፊት ሌሎች ወንዞቻችን ለመጠቀም ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ ምክንያቱም ከአባይ ይልቅ ሌሎች ወንዞቻችን ለልማት ምቹ ናቸው፡፡ ለልማት ተስማሚ የሆነ ወንዝ ደግሞ ለፈጣን ልማት እውን መሆን ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡ አባይን ለመጠቀም መጀመሪያ አቅምን በሁለንተናዊ መልኩ ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ለማምጣት ረዘም ያሉ ዓመታትን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ግን መንግሥት በአባይ ላይ እያካሄደ ያለውን የዲፕሎማሲ ሥራ በከፍተኛ ደረጃ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ይህም ነገ አባይን ለመጠቀም ለሚፈልጉ ልጆቻችን እሴትና መሠረት መጣል ይሆናል፡፡ (ዘውገ ተሰማ፣ ከጉርድ ሾላ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |