Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ኮሚሽኑ ኢ-ፍትሃዊ ለሆኑ የንግድ...
ኮሚሽኑ ኢ-ፍትሃዊ ለሆኑ የንግድ... Print E-mail
Wednesday, 05 March 2008
ኮሚሽኑ ኢ-ፍትሃዊ ለሆኑ የንግድ ውድድሮች መፍትሄ የመስጠት አቅም የለውም

የኢትዮጵያ ንግድ አሠራር አጣሪ ኮሚሽን የንግድ ውድድር ህግን ለማስፈፀም የተቋቋመ ቢሆንም በእቃና አገልግሎት ላይ የሚነሱ የዋጋ መናር ችግሮችንና ፍትሃዊ ያልሆኑ የንግድ ወድድሮችን በራሱ አነሳሽነት አጣርቶ መፍትሄ የመስጠት አቅምና ሥልጣን እንደሌለው ተጠቆመ፡፡
 
የኢትዮጵያ የንግድ አሠራር አጣሪ ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ ሐርቃ ሐሮዬ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችንና ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ በስምምነት ዋጋ የመጨመር ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋመው ኮሚሽን አቋም ጠንካራ ባለመሆኑ በራሱ ክስ መስርቶ መፍትሄ የመስጠት አቅምና ሥልጣን የለውም፡፡

የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጳጉሜ 1996 ዓ.ም. ጀምሮ ከቀረቡት ክሶች መካከል 3ዐዎቹ  ውሳኔ ሲያገኙ ከቀረቡት ክሶች አብዛኛዎቹ በብይን መታለፋቸውንና መዘጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህ ዓመት ከታዩት ክሶች 7ቱ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በድጋሚ እንዲታዩ መመለሳቸውን ለዚህም በዋናነት የተጣለው ቅጣት አነስተኛ በመሆኑ እንደሆነ አቶ ሐርቃ ተናግረዋል፡፡

በንግድ አሠራር አዋጅ አንቀፅ 6/10/11 የተከለከሉ የንግድ ውድድር አይነቶች እንዳሉና አንድ ተከሳሽ ሕገ ወጥ የንግድ ውድድር ካካሄደ ከዓመት ገቢው አንድ አስረኛ ድረስ ሊቀጣ እንደሚችል በሕጉ መቀመጡንም ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ሠዓት በምርት ግብአት ላይ የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በስምምነት ዋጋ የመጨመር ሂደትን በውድድር ሕግ የተከለከለና የሚያስቀጣ ቢሆንም ከግለሰቡም ሆነ ከሸማቾች ማህበር የቀረበ ክስ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ ውሳኔ ካገኙ ክሶች በአብዛኛው በንግድ ስያሜና የንግድ ምልክት፣ ፍትሃዊ ያልሆነ ውድድር የተነሱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽኑ አሁን ባለበት አቅሙ ጠንካራ እንዳልሆነ በጀትና በቂ የሰው ኃይል እንደሌለው ያሉትም በቂ ስልጠናና የሥራ ልምድ እንደሌላቸው፣ የራሱ ቢሮ እንደሌለው የገለፁት አቶ ሐርቃ በበላይነት የሚመሩት አባላቱ መደበኛ አገልግሎት የማይሰጡ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አባላቱ የራሳቸው መደበኛ ሥራ እያለባቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በነፃ ገበያ ውስጥ ፍትሃዊ ያልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር ኃላፊነትና አቅም ያለው ኮሚሽን በነጋዴው ላይ ያሉትን ፍትሃዊ የንግድ እንቅስቃሴዎች የማስተካከል አቅም ለመፍጠር የሚያስችለውን አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በንግድና ኢንዱስትሪና በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተወሰነ ሥራ እንደተሠራ የገለፁት አቶ ሐርቃ አደረጃጀቱንና የውስጥ አቋሙን ለማሻሻል ሠፊ ሥራ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አህመድ ቱሳ የሚመራ ግብረ ኃይል ከተለያዩ መስሪያ ቤት በተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ሕጉን የማሻሻል ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ሕጉ ለካቢኔ ከመቅረቡ በፊት እስከ ሚቀጥለው ወር ቀርቦ የሚመለከታቸው አካላት አስተያየት የሚሰጡበት መድረክ እንደሚመቻችም ተናግረዋል፡፡

ሕጉ ሲሻሻል ኮሚሽኑ ክስ ሳይጠብቅ በራሱ አነሳሽነት ፍትሃዊ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም ለመገንባት እንደሚችልም ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >