Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ከጉርጥ ቆዳ የስኳር በሽታ መድሃኒት ሊሰራ ነው
ከጉርጥ ቆዳ የስኳር በሽታ መድሃኒት ሊሰራ ነው Print E-mail
Wednesday, 05 March 2008
በደቡብ አሜሪካ ከምትገኝ አንዲት የጉርጥ ዝርያ ቆዳ የሚመነጨው ፈሳሽ ለሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ (type 2 diabetes) መድሃኒትነት እንደሚያገለግል አጥኚዎች ገልፀዋል፡፡
የተጠቀሰችው የጉርጥ ዝርያ በታዮፖልነት እድሜዋ (tadpole stage) 27 ሴሜ ርዝመት ሲኖራት ሙሉ አካል ሲኖራት የርዝመት መጠኗ ወደ 4ሴሜ  ዝቅ ይላል፡፡ የጉርጦቹ ርዝመት እንዲቀንስ ለማድረግ ከቆዳቸው የሚወጣው ፈሳሽም በአካላቸው ውስጥ አንሱሊን እንዲመነጭ ለማነቃቃት እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡

ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት መድሃኒቱን መስራት ከተቻለ እየተስፋፋ ያለውንና በርካታ ሰዎችን የሚያሰቃየውን በሁለተኛው አይነት የስኳር አይነት ማከም ይቻላል፡፡ በእንግሊዝ ብቻ ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የሁለተኛው አይነት ስኳር በሽታ ተጠቂዎች ናቸው፡፡

ሁለተኛው አይነት ስኳር ከመጠን በላይ ከሆነ ውፍረት ጋር ይያያዛል፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት በሽታውን የሚያስከትለው ሰውነት አንሱሊን እንዲያመርት እንቅፋት ሲሆን ወይም የሚመረተው ኢንሱሊን በትክክል ሥራ ላይ እንዳይውል ሲያደርግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የጉሉኮስ መጠን በአግባቡ እንዳይቆጣጠሩ ያደርጋቸዋል፡፡

ከላይ ከተጠቀሰችው የጉርጥ ዝርያ ቆዳ የሚመነጨው ፈሳሽ “ፒሱዲን -2” በመባል የሚታወቅ ሲሆን የርዝመት መጠን ከመቀነስ ባሻገር ቆዳዋን ከኢንፌክሽን እንደሚከላከልላት ሳይንቲስቶች አስረድተዋል፡፡ በላቦራቶሪ ውስጥ በተደረገው ተጨማሪ ጥናትም የቆሽት ሴሎችን በማነቃቃት ኢንሱሊን እንዲመነጭ ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህንን ሲያደርግ በቆሽት ሴሎች ላይ ምንም የመመረዝ ችግር እንደማይፈጥርም ታውቋል፡፡

በአልስታር ዩኒቨርሲቲ የባዮ ሜዲካል መምህርና ጥናቱን ያካሄዱት ሳይንቲስቶች መሪ የሆኑት ዶ/ር ያሲር አብደል ዋሃብ እንዳሉት አጥቢያን ከሆኑ (በየብስና በውሃ ውስጥ መኖር የሚችሉ) እንስሳት ላይ ትኩረት አድርጎ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከቆዳቸው የሚመነጨው ፈሳሽ በአብዛኛው ባዮ አክቲቭ የሆኑ ሞሎኪውሎች አሏቸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ በፊት ለስኳር በሽታ መድሃኒት የተገኘ ሲሆን በደቡብ ምዕራብ አሜሪካና ሰሜናዊ ሜክሲኮ ከሚገኝ የእንሽላሊት ዝርያ ምራቅ ሆርሞን የተገኘ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ቻይና ከባቢ አየር በካዮችን ልታጠና ነው

ቻይና አገሯ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ ከባቢ  የሚበክሉ ተቋማት ላይ ጥናት ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች፡፡
 
አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የተለያዩ ፋብሪካዎች፣ የእርሻ እንቅስቃሴዎችና ሌሎችም ለከባቢ አየር ብክለት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ተብለው የሚታሰቡ ላይ ምን ያህልና በምን ደረጃ አየርን እንደሚበክሉ ጥናት ይደረግባቸዋል፡፡

የቻይና መንግሥት ይህንን ፕሮጀክት ሥራ ላይ ለማዋል ሲወስን ያሳሰበውን ነገር ከኩባንያዎቹ ትክክለኛ ዳታ ማግኘት ከባድ እንደሚሆን ነው፡፡ በሚቀጥለው አመት ለህትመት ለሚበቃው ይኸው ጥናት በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች መረጃዎችን ለቻይና ፖሊውሾን ሶርስ ሴንሰስ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሃላፊ ዋንግ ዩኪንግ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የጥናቱ ዋና አላማ የቻይና የአየር ብክለት ችግር ምን ላይ እንደሆነ ጥርት ያለ ስዕል ማግኘት መቻል ነው፡፡ መንግሥት የተገኘውን መረጃ በመጠቀም አዳዲስ ፖሊሲዎችን እንዲያረቅ ያስችለዋል ብለዋል፡፡ ትክክለኛ መረጃ የማይሰጡ ኩባንያዎችም ይቀጣሉ፡፡ ቻይና ውስጥ ከከባቢ አየር መበከል ጋር ይያያዛሉ የሚባሉ 15ሺህ ኩባንያዎች አሉ፡፡

ቫይታሚን ኢ አብዝቶ መውሰድ ለሳምባ ካንሰር ያጋልጣል

የቫይታሚን ኢ ክኒኖችን ከተፈቀደው መጠን በላይ መውሰድ በሳንባ ካንሰር የመያዝ እድልን እንደሚጨምር ጥናት ያደረጉ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡

በአሜሪካ በሚኖሩ 77ሺህ ሰዎች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው 400 ሚሊ ግራም የቫይታሚን ሲ ክኒን በቀን የሚወስዱ ሰዎች በሳምባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው 28 በመቶ ደርሷል፡፡ በተለይ በሚያጨሱ ሰዎች ላይ አደጋው ይጨምራል ተብሏል፡፡

ኤክስፐርቶች እንዳሉት ሰዎች በክኒን መልክ የተቀመሙ ቫይታሚኖችን ከመውሰድ ይልቅ ከቅጠላቅጠልና አትክልቶች ቢያገኙ ይመረጣል፡፡ ከኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ቲም ቤርስም በበኩላቸው “ከጤናማና ከተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊ ኒውትራንቶችንና ሚኒራሎችን በቀጥታ ማግኘት በካንሰር ከመያዝ አደጋ ያድናል” ብለዋል፡፡

አጥኝዎቹ እድሜያቸው ከ50 እስከ 76 ያሉ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ለአራት ዓመታት ክትትል አድርገዋል፡፡ ሰዎቹ በየቀኑ ቫይታሚን ሲ፣ ፎሊክ አሲድና ቫይታሚን  ያላቸው ክኒኖችን ይወስዳሉ፡፡ በተደረገው ክትትልም በአራት ዓመት ውስጥ 52 ያህል ሰዎች በሳምባ ካንሰር ተይዘዋል፡፡

በተለይ የሚያጨሱና ከሚያጨሱ ሰዎች ጋር የሚኖሩት በበሽታው የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ታይቷል፡፡ ለካንሰር የተጋለጡት ግን ቫይታሚን ሲም ሆነ ፎሊክ አሲድ የወሰዱትን ሳይሆን ቫይታሚን ኢ የወሰዱት ብቻ ናቸው፡፡

ቫይታሚን ኢ በተለይ ለአጫሾች የሚታዘዝ ቢሆንም በተቃራኒው አጫሾች የቫይታሚን ኢ ኪኒን ከወሰዱ ደግሞ በሳምባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡

ድብርትን በደም ምርመራ ማወቅ ተቻለ

የስሜት መዛባትን (Mood disorder) በደም ምርመራ እንደሚታወቅ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡ በደም ውስጥ የተለያዩ ኬሚካሎች መገኘት የስሜት መዛባት ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ደረጃ ድብርት ያጋጠመውን ሰው ለመለየት የሚያስችል የላቦራቶሪ ምርመራ የለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በሽተኛው ከሚነግረው በመነሳት የጤና ባለሙያው የሰውየውን የስሜት መዘበራረቅና አለመዘበራረቅ ይገምታል፡፡

አሜሪካ ድረ ገጽ ላይ ሽብርተኞችን ትፈልጋለች

የአሜሪካ መንግሥት በድረ ገጾች ላይ አሸባሪዎችን ለማወቅ የሚያስችል ፕሮጀክት መዘርጋቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሬይናርድ በተባለ ስውር ስም የተሰየመው ፕሮጀክት በኦን ላየን ወርልድ የሽብርተኝነት ባህሪይ ያላቸውን ግለሰቦችና አሸባሪዎችን ለማደን ይረዳል፡፡ ይህ ድረ ገጽ በኢንተርኔት አሸባሪዎችን ለሚያድኑ የደህንነት ባለሥልጣኖች ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ሽብርተኞችን  በማደን ላይ ባሉ የተለያዩ ተቋማት ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን ስለሬንያርድ ፕሮጀክት ዝርዝር መረጃ በአሜሪካ ደህንነት ባለሥልጣናት በአሜሪካ ኮንግረስ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
 
< Prev   Next >