| የሐብሊን ውዝግብ ለመፍታት... |
|
|
| Sunday, 09 March 2008 | |
|
የሐብሊን ውዝግብ ለመፍታት በሽምግልና እየተሞከረ ነው
በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) ፓርቲ አባላት መካከል የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት በሽምግልና ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንዳንድ የፓርቲው አባላት ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ እንዲሁም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት የሐረሪ ብሔረሰብ አባላትና የፓርቲው ደጋፊዎች ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም የፓርቲው የአዲስ አበባ አካባቢ አባላትና በሐረሪ ክልል የሚገኙ የፓርቲው አባላት ሰሞኑን በሐረሪ ከተማ ውይይት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል፡፡ የፓርቲውን ውዝግብ ለመፍታት ከአዲስ አበባ አስራ ዘጠኝ አባላት ከድሬዳዋ አስራ አንድ በጥቅሉ ሠላሳ አባላት ለዕርቅ ሐረር ከተማ ተገኝተው የብሔረሰቡ የአገር ሽማግሌዎችም የማስታረቅ ሥራ እየሰሩ መሆኑን አባላቱ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡ የፓርቲው አንዳንድ አባላት "በፓርቲው ውስጥ የተነሳው ውዝግብ በፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ በሽምግልና አይፈታም" የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ በሌላ ዜና በሐረሪ ክልል ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች በግዴታ ከወርሃዊ ደመወዛቸው ከአስር በመቶ ጀምሮ በተለያየ መጠን ከሦስት እስከ አራት ወር ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ለፓርቲው ማጠናከሪያ እንዲሁም በሚያዚያ ወር ለሚካሄደው ምርጫ እገዛ የሚውል መዋጮ እንዲያዋጡ መጠየቃቸው ታውቋል፡ መዋጮው የፓርቲው አባላትና አባል ያልሆኑትንም ያጠቃልላል፡፡ በዚህም በርካታ የክልሉ ሠራተኞች ከፍላጎታቸው ውጪ መሆኑን በመጥቀስ አማርረዋል፡፡ መዋጮውን አስመልክቶ ለክልሉ አስተዳደር ተቃውሞ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ የመጀመሪያ ዙር ክፍያ በጥር ወር መጀመራቸውን ሰራተኞቹ ለሪፖርተር ከስፍራው በስልክ ተናግረዋል፡፡ የክልሉ የአስተዳደር መዋጮው ግዴታ መሆኑንና የማያዋጣ ሰራተኛ ከስራ ገበታው እንደሚፈናቀል የተገለፀላቸው መሆኑን በመጥቀስ ሠራተኞቹ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ ርዕሰ ጉዳዮቹን አስመልክተን ለፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሙራድ አብዱላሂ በተደጋጋሚ በስልክ በማግኘት ብንጠይቃቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በሐረሪ ብሄራዊ ሊግ በተፈጠረ ልዩነት ከህግ ውጪ አባለት እንደሚታገዱ፣ የተለየ ሃሳብ የሚያራምዱ "ጥገኛ" እንደሚባሉ የፓርቲውን አባላት በመጠየቅ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
“ጦርነት የሚፈጠረው ተቃዋሚዎች...
ምክር ቤቱ ሕንፃውን ለመረከብ...
“ዋጋው ባይረጋጋ እንኳን ነጋዴው...
“ዋጋው ባይረጋጋ እንኳን ነጋዴውመረጋጋት ይኖርበታል”
ወጣቱ ዲን
ራስን ለገበያ ማመቻቸት
"ከረጅም ርቀት ውጭ...
በዚምባብዌ ድጋሚ ምርጫ ይካሄድ ይሆን?
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.