Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል...
ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል የተባለ ተጠርጣሪ ተያዘ

በደቡብ ክልል በአላባ ጠንባሮ ከተማ ባለቤቱን በቢላ አርዶ ገድሏል የተባለ ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
 
የአላባ ጠንባሮ ከተማ መርማሪ ፖሊስ መቶ አለቃ ኑርዬ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የዋለው የካቲት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በባለቤቱ ወ/ሮ ፀሀይን በቢላ አርዶ ከገደለ በኋላ ለማምለጥ ሲሞከር ነው፡፡

እንደ መቶ አለቃ ኑርዬ ገለፃ ግለሰቡ በሁለት ልጆቹ እናት ላይ ወንጀሉን የፈፀመው ሆን ብሎ ነው፡፡

ሟቿ የተገደለችው የልጇን አንደኛ ዓመት በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ በነበረችበት ወቅት መሆኑን የጠቆሙት መርማሪው ፖሊሱ ተጠርጣሪው ግለሰብ በባለቤቱ ላይ ወንጀሉን የፈፀመው ዝግጅቱን በማሰናዳት ሲያግዙ የነበሩ ጐረቤቶችን ምክንያት በመፍጠር ከቤት እንዲወጡ ካደረገ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ በቅናት ተገፋፍቶ ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑን የገለፁት መቶ አለቃ ኑርዬ ተጠርጣሪው ለፖሊስ ቃል በሰጠበት ጊዜ ትክክለኛ ያልሆነ የአባትና የአያት ስም አስመዝግቦ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የሟች ወንድም የሆነው ታምራት ከላይ በበኩሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፀው ተጠርጣሪው ግለሰብ በፖሊስ የተያዘው ወንጀሉን ፈፅሞ ከቤቱ ሲወጣ ልብሱ በደም ተጨማልቆ የተመለከተ ጐረቤት ለፖሊስ በማመልከቱ ነው፡፡

ከአላባ ጠንባሮ ከተማ ካገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው የከተማው ነዋሪ ህዝብ ወንጀሉ በተፈፀመ ማግስት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በወንጀል ፈፃሚው ላይ ትክክለኛ ፍርድ እንዲተላለፍበት ጠይቋል፡፡

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >