Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow "በአየር ብክለት ሳቢያ በቤጂንግ...
"በአየር ብክለት ሳቢያ በቤጂንግ... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
Image"በአየር ብክለት ሳቢያ በቤጂንግ ኦሊምፒክ አልሳተፍም"
አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ

በመጪው ነሐሴ ወር በሚካሄደው የቤጂንግ ኦሊምፒክ በአየር ብክለት ሳቢያ እንደማይሳተፍ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ለሪፖርተር ጋዜጣ አስታወቀ፡፡
 
የመካከለኛና የረዥም ርቀት ጀግና ኃይሌ እንዳስታወቀው በቤጂንግ ኦሊምፒክ የማይሮጠው በቻይና ያለው የአየር ብክለት ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡

የከባቢ አየር እየጋለ መምጣት አሳሳቢ መሆኑን የገለፀው ኃይሌ ቻይናና አሜሪካ የኪዮቶን ፕሮቶኮል (የግሎባል ዋርሚንግ የዓለም ከባቢያዊ አየር እየጋለ መምጣትን) በተመለከተ የተደረገውን ስምምነት አለመፈረማቸው አግባብ አይደለም፡፡

42 ኪ.ሜ በተበከለ አየር መሮጥ አስቸጋሪ መሆኑን ያመለከተው ኃይሌ በቤጂንግ ኦሊምፒክ ተሳታፊ አለመሆኑ አላስደሰተውም፡፡

"የዓለም የከባቢ አየር እየጋለ መምጣት ሊያሳስበን ይገባል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት ከሚያባብሱ ድርጊቶች መታቀብ ደግሞ የዓለማችን የወቅቱ ጥያቄ ነው፡፡ እኔም ከኦሊምፒክ ጐን ለጐን ይህንን የዓለማችንን ስጋት ለመቀነስ የሚደረገው ትግል ድጋፌን እሰጣለሁ" በማለት ኃይሌ ተናግሯል፡፡

"አገር ጉዳይስ?" ተብሎ ለተጠየቀው "የአገር ጉዳይ የአገር ነው፡፡ ኢትዮጵያና ኦሊምፒክ በታሪክና በውድድር ደረጃ ያላቸውን ትስስር እወዳለሁ፡፡ ለኢትዮጵያዊያን ማራቶን የሚሰጠውን ትርጉምና ስሜትም አውቃለሁ፡፡" "በአገር ደረጃ የሚወሰነው ውሳኔ የአገር በመሆኑ የቤጂንግ ኦሊምፒክ ሲደርስ ይፋ አደርጋለሁ" ብሏል፡፡ አያይዞም "እኔም፣ ኦሊምፒክና ማራቶን እንፈላለጋለን፡፡ ወቅቱም አሁን ነው" ብሏል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >