| ጦጣዎች የኬንያ አርሶ አደሮችን እየተተናኮሉ ነው< |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
የጦጣ መንጋ ኬንያውያን የመንደር ሴቶችን ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ ቀኑን ያለእረፍት እንዲያሳልፉ ከማድረጋቸው ባሻገር የእርሻ ማሳዎችን በማጥፋት የምግብ ቀውስ እንዲከሰት ምክንያት መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡
ባለፈው ወር የፖርላማ አባላት የኬንያ ዱር እንስሳት ጥበቃ አገልግሎት ጦጣዎችን ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታወሷል፡፡ በተለይ በኪኩዩ ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ባሉ መንደሮች 3ዐዐ የሚጠጉ ጦጣዎች የእርሻ ማሳዎች ላይ ወረራ በመፈፀም የመንደርተኞቹን በቆሎ፣ ድንች፣ ባቄላና ሌሎች ሰብሎችን በልተዋል፡፡ በአካባቢው ባህል የእርሻው ሥራና ጥበቃ በሴቶች ጫንቃ ላይ የወደቀ በመሆኑ የጦጣዎቹ ጥቃት ዋነኛ ሰለባ ሆነዋል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ጦጣዎቹ ለሴቶቹ ማስፈራሪያ የማይበገሩ እንዲያውም ድንጋይ መልሰው በመወርወር ጥቃት እስከመሰንዘር የሚደርሱ መሆናቸው ነው፡፡ የኬንያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ድርጅት አንድ የሥራ ኃላፊ ለቢቢሲ እንዳሉት፣ ጦጣዎቹ እያሳዩት ያለው ባህሪ ከዚህ ቀደም ጨርሶ ያልታየ ሲሆን ጉዳዩን በመመርመር ላይ ናቸው፡፡ መንደርተኞቹ በደረሰው ጥፋት ምክንያት ለተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ በጦጣዎቹ ላይ እርምጃ መውሰድ በህግ ያስጠይቃል እያለ ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |