Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow የብሔር ብሔረሰቦች መንደር...
የብሔር ብሔረሰቦች መንደር... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
Image
ዶ/ር ኃይሉ ወርቁ
Image
አቶ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ
የብሔር ብሔረሰቦች መንደር ግንባታ ቦታ አወዛገበ


በአዲስ አበባ "አድዋ ፓርክ" እየተባለ በሚታወቀው አካባቢ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መንደር ለመገንባት ስለመታቀዱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ፅህፈት ቤት እና ኢትዮጵያን ቪሌጅ አድቬንቸር በጋራ ዕቅዱን እንደሚያስፈፅሙ በመግለፅ ቦታውን ማስፈቀዳቸውን ገልፀዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ኃይሉ ወርቁ በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት አድዋ ፓርክ ባለቤትነት የመሥሪያ ቤታቸው መሆኑን በማስታወስ በዚሁ ጋዜጣ ላይ በቦታው ላይ የብሔር ብሔረሰቦች መንደር እንደሚገነባ አንብበናል፡፡ ባለቤት ሆነን ስለዚህ ጉዳይ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ የፈቀደው አካል የትኛው እንደሆነም አናውቅም፡፡

በአድዋ ፓርክ ላይ መሥሪያ ቤታቸው በዘንድሮ የበጀት ዓመት የማክሮ ኘላን እና ድንበሩን የመከለል ሥራዎች ለማከናወን ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዶ/ር ኃይሉ ጠቁመው ዕቅዳችንን በተፈለገው ፍጥነት እንዳይከናወን በክልሉ ያሉት ሕገወጥ ግንባታዎች እንቅፋት ሆነውብናል፡፡ ይኸንንም በአጭር ጊዜ ቀርፈን ወደ ተግባር እንገባለን ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ባለሥልጣኑ ያቀረበው ቅሬታ ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ስለግንባታው ለዋና ሥራ አስኪያጁ ተነግሮአቸው ቦታውን ለሌላ አካል ለማስተላለፍ መስሪያ ቤታቸው እንደማይችል፣ ሆኖም ከሚመለከተው አካል አስፈቅደው ቢመጡ ለሥራው አስፈላጊው እገዛ እንደሚያደርጉላቸው እንደገለፁላቸው አስታውሰዋል፡፡

አቶ ኪሮስ አያይዘውም ቦታውን ለመጠቀም ፈቃድ ተገኝቷል፣ ሆኖም ቦታውን እስካሁን አልተረከብንም በማለት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቪሌጅ አድቬንቸር ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሙራድ መሐመድ ግንባታውን አስመልክቶ ከክልሎቹ ጋር ለመመካከር ባለፈው ሐሙስ ዕለት በተጠራው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት መንደሩ በኢትዮጵያ ካርታ ቅርፅ በ160 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እንደሚገነባ፣ መንደሩም ባህልን፣ ማኀበራዊ እሴትን፣ ቋንቋን፣ ሥልጣኔን፣ ልማትን መሠረት በማድረግ እንደሚገነባ አስረድተዋል፡፡ ክልሎቹ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን ግንባታውን እንደሚያከናውኑ ገለፃ አድርገዋል፡፡

አቶ ኪሮስ ኅ/ሥላሴ የአዲስ አበባ ማሌኒየም ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ለፅህፈት ቤቱ ከቀረቡት በርካታ ኘሮጀክቶች መካከል እጅግ አስፈላጊ ናቸው ተብለው ከታመነባቸው መካከል የዚህ መንደር ግንባታ ኘሮጀክት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም የመንደሩን ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ለማግኘት ጊዜ መፍጀቱን፣ በመጨረሻም በአድዋ ፓርክ በጊዜያዊነት 16ዐ ሺ ካሬ ሜትር ቦታ መገኘቱን፣ ከግንቦት 2ዐ እስከ 2ዐዐ1 ዋዜማ ድረስ የሚቆይ የብሔር ብሔረሰቦች መንደር ለመገንባት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

የተለያዩ ክልል ተወካዮቹ በስብሰባው ላይ በሰጡት አስተያየት ኘሮጀክቱ ጥሩ መሆኑን በመግለፅ ነገር ግን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ክልሎቻቸውን አሳምነው፣ ግንባታው ላይ ተሳትፈው ለግንቦት 2ዐ ለማድረስ የጊዜ መጣበብ እንደሚኖር ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >