Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow መለስ ከግል ከፍተኛ...
መለስ ከግል ከፍተኛ... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
መለስ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር መከሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ረቡዕ የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም ውይይት አደረጉ፡፡
 
25 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በትምህርት አሰጣጥ ላይ ያጋጠማቸውን ችግር በማስመልከት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በተነጋገሩበት በዚሁ ዕለት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊመልሳቸው የሚገቡ አምስት ጥያቄዎችን ለአቶ መለስ ማቅረባቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

የግሉ ዘርፍ ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንዳለበት የሚያመለክት መሪ እቅድ እንደሌለው የገለፁት ተወካዮች የመንግሥት እና የግል ተቋማት አብረው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ለግሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግሥት የሚሰጠው ድጋፍ አነስተኛ መሆኑን የጠቆሙት ተወካዮቹ ለመስኩ የሚያስፈልጉ ግብአቶች በተገቢው መንገድ አለመቅረባቸውን አመልክተዋል፡፡ እንደምሳሌም የግንባታ መሬትንና የኮንስትራክሽን ቁሳቁሶችን ጠቅሰዋል፡፡

ከምንጮቻችን መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮቹ የረጅም ጊዜ አገልግሎት ለዘርፉ ሊሰጥ ይገባል የሚል ሃሳባቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የግልና የመንግሥት ተቋማት የሚወዳደሩበት መስክም እኩል እንደማይቃኝ ለአቶ መለስ ተናግረዋል፡፡ የመመሪያዎቹ ግብታዊነትና የተዘበራረቀ መሆንም በዘርፉ ላይ ችግር መፍጠሩ ተገልጿል፡፡ በመመሪያ አፈፃፀም ላይ የሚታየውም ችግር የግል ተቋማቱ መስራት የሚጠበቅባቸውን ያህል እንዳላሰራቸው ተወካዮቹ ገልፀዋል፡፡

የተወካዮቹን ጥያቄ ያዳመጡት አቶ መለስ በበኩላቸው እስከ አሁን ድረስ መንግሥት በበቂ ሁኔታ ያልሰራቸው ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመው ከአሁን በኋላ ግን መንግሥት ከግል ተቋማቱ ጋር በመተባበር ለመስራት እንደሚሞክር መናገራቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

የግል ተቋማቱ ጥያቄ ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ የሆነ ሥራ እየሰራን ነው በብቃታችን እየተለየን እንለካ፣ ዘርፉም ውጤት አልባ እንዳይሆን በጋራ እንስራ የሚል አንድምታ እንዳለው የተረዱ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት በቁጥጥሩ ላይ ያለውን አቅም በማሻሻል እንደሚሰራና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱንም እንደሚያበረታታና እንደሚደግፍ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ አሰራሩም ተቋማዊ በሆነ መንገድ እንደሚመቻች አመልክተዋል፡፡  

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >