| የኢኮኖሚ ጭንቅላት ናቸውና... |
|
|
| Sunday, 09 March 2008 | |
የኢኮኖሚ ጭንቅላት ናቸውና ልዩ ትኩረት ለፋይናንስ ተቋማት!የተዛባና የተነካ ጭንቅላት ያለው ሰው አይ ቁመት፣ አይ መልክ፣ አይ ጥርስ፣ አይ ጠጉር፣ አይ እግር፣ አይ ዳሌ እያሉ ቢያደንቁት ትርጉም የለውም፡፡ እንደ ስሙ ሊያንቀሳቅሰውና ሊያኖረው የሚያስችለው ወሳኙ የሆነው ጭንቅላቱ ተዛብቷልና፡፡ ኢኮኖሚም እንደዚያ ነው፡፡ የኢኮኖሚው ጭንቅላት የሆኑት የፋይናንስ ድርጅቶችና ተቋሞች ከቀወሱ ልማትም፣ እድገትም፣ መሠረተ ልማትም፣ ንግድም፣ ኮንስትራክሽንም፣ አገልግሎቱም ይበላሻሉ፡፡ እነዚህ ከተበላሹ ደግሞ አይ የአየር ጠባይ፣ አይ ተራራ፣ አይ ሸንተረር፣ አይ ዘፈን፣ አይ መዝሙር፣ አይ ባህል፣ አይ ታሪክ". እያልን ብናደንቅና ብናወድስ ትርጉም የለውም፡፡ አጉል ማስተዛዘኛ ነው የሚሆነው፡፡ የፋይናንስ ድርጅቶች ስንል ብሔራዊ ባንክ፣ ሌሎች ባንኮችና ኢንሹራንሶች ማለታችን ነው፡፡ የመንግሥትም ይሁኑ የግል የፋይናንስ ተቋሞች በጋራ የኢኮኖሚው ጭንቅላት ናቸው፡፡ የመንግሥትም ሆነ የግል ገንዘብና ንብረት፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ኢምፖርትና ኤክስፖርት፣ ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት የሚንቀሳቀሰው በእነዚህ ተቋማት ዙሪያ ነው፡፡ እነሱ ከቀወሱና ከተናጉ ጠቅላላ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ይናጋል፣ ይቃወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያሉት የፋይናንስ ድርጅቶች፡- እጅግ ከፍተኛ ትኩረት፣ ዳግም መደራጀት፣ አዲስ አወቃቀር አዲስ ፖሊሲ፣ አዲስ ራዕይና እምነት ያለው የሰው ኃይል ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህን እውን ለማድረግ መንግሥት ቆራጥና አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ እርምጃውን ለመውሰድ የሚያስችለው በቂ መረጃም በእጁ ይገኛል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ብቃት ያለው አመራር እንደሌለው ገሃድ ወጥቷል፡፡ የአገር ሃብትና መጠባበቂያ የሆነው ወርቅ መሣቂያና መቀለጃ ሲሆን ብሔራዊ ባንክ ተባባሪ ሆኗል ወይም ተጭበርብሯል፡፡ በሁለቱም በኩል ሲታይ ብቃት የሌለው ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡ ልማት ባንክ ከሰረ ብሎ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው ሪፖርትም የልማት ባንኩን ደካማነት ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን የብሔራዊ ባንክንም ደካማነት ያረጋግጣል፡፡ ምክንያቱም ይህ ኪሳራ የአንድ ዓመት ሳይሆን ቢያንስ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲከማች የመጣ ስለሆነ ብሔራዊ ባንክ በጊዜው ለምን አልገለፀም? አልተቆጣጠረም? የሚያሰኝ ነው፡፡ ለአበባ የተሰጠው ብድር ከስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተገኘው ገቢ ግን ሰባ ሚሊዮን ብር ብቻ በነበረበት ወቅትም ብሔራዊ ባንኩ እንኳን ሊቆጣጠርና መፍትሔ ሊሰጥ "እንዴት ነው ነገሩ?" የሚል መገረምም አላሳየም፡፡ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል ብር ሲቃጠል የሚታይበት ብሔራዊ ባንክ ብሔራዊ ባንክ ሊባል አይገባውም፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዢና ምክትል ገዢ ብቻ ሳይሆኑ ብሔራዊ ባንኩን የሚቆጣጠረው ባለሥልጣንም የሚጠየቅበት ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክ የራሱን ሥራ ማካሄድ አቅቶት የበላይ አካል ሥራውን እንዲሠራለት ሲጠብቅና ሲማጠን የበላይ አካልም የባንኩን ችግር አይቶ ከመፍታት ይልቅ የባንኩን ሥራ "በአደራነት" እያካሄደ መቆየቱ ያስጠይቀዋል እንጂ አያስመሰግነውም፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኤጄንሲ ኃላፊ አጥቶ ለሦስት ዓመታት ተዘግቶ መክረሙም ተገቢ አልነበረም፡፡ ብዙ መሥራትና ማስተካከል ይችል የነበረ አካል ኃላፊ አጥቶ ሥራ ፈት ሆኖ መቆየቱ ሌላው የፋይናንስ ድርጅቶች ትኩረት የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኤጄንሲው እያደረገው ያለው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ቀደም ብሎ ቢጀምር ኖሮ ብዙ ችግር ማስወገድ በተቻለ ነበር፡፡ የልማት ባንክ ችግር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ችግር ነው፡፡ ኃላፊዎች ተብለው የተቀመጡ ሰዎች በሚያበድሩት ድርጅት ቦርድ አባላት ሆነው ሲሰሩና ያበደሩት ድርጅት ሊሸጡና ሊለውጡ እንደሚችሉ ውክልና እንዲሰጣቸው ሲጠየቁ እየተስተዋለና እየተነገረ፣ በመገናኛ ብዙሃን እየተላለፈ እያለ ሥራ ጠፍቶ አሁን ልማት ባንክ ችግር ውስጥ ገብቶ ቢገኝ የሚገረም ሰው ካለ ራሱ የሚያስገርም ሰው ነው፡፡ አምስት ቢልዮን ብር አበድሮ ከአምስቱ አራቱ ቢልዮን መሰብሰብ አቅቶት ቢገኝ ችግር ለመኖሩ የሚሰጠው ተጨማሪ መረጃ አይኖርም፡፡ የታወቀ ነውና፡፡ ስለአሟሟቱ የሬሳ ምርመራ ዘዴው እውቀት ይሰጥ እንደሆነ እንጂ፡፡ የባንኮችና ኢንሹራንሶች ፖሊሲ ምን ይመስላል? ኤንትሬና አሮጌ ቪላ አለህ እያሉ ዋስትና (ኮላትራል) ማፈላለግ የዘመናዊ ባንክ አሰራር ነው ወይ? ባንኮች በሃራጅ በሚሸጡት ንብረት ላይ ነው ማተኮር ያለባቸው ወይስ ቢዝነሱ የተሳካ ሆኖ በሚከፈለው ወለድና ብድር? ባንኮች በሚሸጥ ንብረት ላይ እያተኮሩ የሚያበድሩ መሆናቸው ራሱ አሳዛኝ ነው፡፡ በሚሸጠው ንብረት ላይ ያለው ፖሊሲ ምን ይመስላል? መኪኖች (ትናንሽ የቤትና የቢሮ እንዲሁም የጭነት መኪኖች) በባንኮችና በኢንሹራንሶች ተወርሰው ከአዲስ አበባ እስከ አቃቂ ባለው ዋና መንገድ ዳር ተጥለው ዝገው፣ ሣር በቅሎባቸው ይታያሉ፡፡ የፎርክሎዣር ሕግ ውጤቱ ይህ ነው ወይ? ንብረት ወርሶ መጣል፤ ንብረቱም ለኪሳራ፣ ገንዘቡም ለኪሳራ ማድረግ መዳረግ? ከመውረስና ከመጣል ይልቅ ጤናማ ገንዘብ ሰጥቶ በሽተኛውን ገንዘብ ማዳን አይሻልም? የግል ባንኮች የሚመረቱት አትራፊ ሆነው መስራቾች ከትርፉ እንዲጠቀሙ ሳይሆን ለመበደር እንዲመቻቸው ብለው በመስራቾች ሲመሰረቱ ምን ይባላል? ከእድርና ከእቁብ ያነሰ አደረጃጀትና አመኔታ ያላቸው የግል ባንኮችስ ባንኮች ናቸው? ልማት ላይ ከማተኮር ይልቅ "ገልባጭ" መኪና መግዣ ለማበደር የሚቋቋሙ ባንኮችን ባንኮች እንበላቸው? ጥሩና በልማት ላይ የሚንቀሳቀሱ የሚባሉ ጥቂት የግል ባንኮች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ግን ለስርቆትና ለዝርፊያ እንዲመቻቹ የሚቋቋሙ ባንኮች አሉ፡፡ ይህም የፋይናንስ ድርጅቶችን ችግር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ብዙ ለማለት የማስረጃ ችግር የለም፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በወርቅም፣ በባሌስትራም፣ በኪሳራውም፣ በትርፉም፣ በገንዘብ እጥረቱም፣ ባልተሰበሰበ ገንዘብ ብዛቱም አንፃር ሲታይ በፋይናንስ ድርጅቶች ዙሪያ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ሆኗል፡፡ አሳሳቢ ነው፡፡ በተለይም ከአሁኑ አሳፋሪ አካሄዳቸው አንፃር ሲታይ እነዚህን ባንኮች ይዞ ልማት አይታሰብም፡፡ ይህ ችግሩን በግልፅ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ያመቻቸ ስለሆነ መንግሥት ይህ ሁኔታ ሳያመልጥ በአስቸኳይ እርምጃ ይውሰድ፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ደመወዝ ለመጨመር ኤጀንሲው የቦርድ አባላትም ማኔጅመንቱም እየተነጋገሩ ሠርተዋል፡፡ ይህ ከተቻለ፣ እየተነጋገሩ ብዙ ችግር መፍታት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ይህ አካሄድ ተሳክቶ ብሔራዊ ባንክን የማስተካከል ሥራ ካልተሰካ ግን ታጥቦ ጭቃ ነው፡፡ ስለዚህ፣ መንግሥት ለፋይናንስ ድርጅቶች ጥንካሬና መሻሻል ልዩ ትኩረት ይስጥ፡፡ አሁኑኑ!! |
| < Prev | Next > |
|---|
የሃቀኛ ተፎካካሪ ቤት ተዘግቶ ያድራል!
በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ኃያልነት ፈተና
ደቡብ አፍሪካ ለሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ ልትሰጥ ነው
የደቡብ አፍሪካ መንግስት በአቢይ ክልል ለሚገኙ ሱዳናውያኖች 40 ቶን የሚመዝን ድንኳን፣ ብርድልብስ፣ የወባ መከላከያ አጎበር፣ ፍራሽ፣ ምግብና ልብሶች እርዳታ ሊሰጥ ነው፡፡
የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ጉዳቱና ጥቅሙ
"በእኛ አገር እውቀት እንደ...
"በእኛ አገር እውቀት እንደ ገንዘብ እየተቆጠረ አይደለም"
ካፒቴን መኮንን ሃብት ይመር
ካፒቴን መኮንን ሃብት ይመር ኢኮ የሁሉነሽ የጋዝ ምድጃዎችና የእርሻ መሣሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ኢኮ የሁሉነሽ የነጭ ጋዝ ምድጃን በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡
የሚቆጠብ ባይኖርም ይቆጠባል
በምሕረት አስቻለው
ለረዥም ዓመታት ከክፍለ ሀገር ቅቤ፣ አይብና እህል እያመጡ ይነግዱ ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እቃዎች ስለተወደዱባቸው ወደ ጉሊት ችርቻሮ ንግድ መግባታቸውን ይናገራሉ ወ/ሮ ፋንቱ ብዙነህ፡
የተራቀቁ ሌቦች ለቤጂንግ...
የተራቀቁ ሌቦች ለቤጂንግ ኦሊምፒክ አስግተዋል
የቤጂንግ ኦሊምፒክ በኤሌክትሮኒክስ ወንጀል ለሚፈጽሙ ሰዎች የተጋለጠ መሆኑን የደህንነት ድርጅቶች ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዲያስፖራው በአገሩ ልማት...
የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ
በምሕረት አስቻለው
"ማጥናት ለእኔ እንደመዝናናት ነው፡፡ እለት በዕለት የተማርኩትን አጠናለሁ፡፡ ደብተሬ ጠርዝ ላይ ዋና ዋና ነጥቡን እጽፋለሁ፡፡ ቋሚ ጓደኛዬ የምለው በግቢ ውስጥ የለኝም፡፡ በአጋጣሚ ካገኘሁት ተማሪ ጋር እሆናለሁ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት በትምህርትና በጥናት ሁኔታ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ የዚያ ዓይነት ግንኙነት የለኝም፡፡ ይህ ለውጤቴ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል" ያለችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ነጥብ በማምጣት ከሥነ ኤዱኬሽን ኮሌጅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ወጣት ማስተዋል መኮንን ነች፡፡
ኦሊምፒክን በቲቪ፣ ኢ ቲቪን በኦሊምፒክ
ከበደ አስቻለው
የኦሎምፒክ ጨዋታዎችና ውድድሮች በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን መሰራጨት እስኪጀመር ድረስ የኦሊምፒክ ንቅናቄ ከአርባ ዓመት በላይ እድሜ አስቆጥሯል፡፡ የመጀመሪያው የ1896 የአቴንስ የኦሊምፒክስ ጨዋታዎች የተዘገቡትና ዜናቸው የተሰማው በጋዜጣና በጋዜጦች ብቻ ነበር፡፡ የወቅቱ ሪከርዶች እንደሚያመላክቱት ለአቴንስ ውድድር እውቅና ያገኙት (አክሬዲት የተደረጉት) ጋዜጠኞች በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ነበሩ፡፡
ፍርድ ቤት ምን ያህል ይናገራል? ያናግራልስ?
የመንግሥት መሠረታዊና ዋና ዋና ሥልጣኖች የህግ አውጭነት፣ የህግ አስፈጻሚነት እና የዳኝነት ስልጣኖች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ አንዱን የመንግሥት ዓይነት ከሌላው የመንግሥት ዓይነት የሚለየው የተጠቀሱት መሠረታዊ ስልጣኖች ተጠቅልለው፣ ጨርሰውና አካተው በአንድ ሉዓላዊ የሥልጣን አካል እጅ መግባታቸው ወይም መውደቃቸው፣ አለዚያም እነዚህ የመንግሥት መሰረታዊ ሥልጣኖች ሊለያዩና ለየቅልና እኩል ለሆኑ ሦስት የሥልጣን አካላት መደላደላቸው ነው፡፡ እንደ አሜሪካ ባለ ኘሬዚዳንታዊ የመንግሥት ሥርዓት የመንግሥት የህግ አውጭዎች፣ የህግ አስፈጻሚነት የዳኝነት ሥልጣን እንደቅደም ተከተላቸው ለፓርላማ፣ ለኘሬዚዳንቱ (እና ለካቢኔው) እንዲሁም ለፍርድ በት የተሰጡ በመሆናቸው ከዚህ በመነጨ አሰራር በተለይም የዳኝነቱ አካል ሦስተኛው ዘርፍ (ዘ ሰርድ ብራንች) ይባላል፡፡
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ከወረቀት ዘሏልን?
በሠለሞን ጎሹ
በድምቀት እየተካሄደ ቆይቶ ዛሬ የሚጠናቀቀው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ከመጀመሩ በፊት ቻይና ለአካባቢ ጥበቃ የምትሰጠው ትኩረት የላላ መሆኑን በማንሳት ምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙሀን ውርጅብኝ ሲያወርዱባት ነበር፡፡ ቻይና በቅርብ ዓመታት በኢኮኖሚው ረገድ ያደረገችው እምርታ ዜጎቿ በንፁህና ጤናማ አካባቢ ለመኖር እንዲችሉ ባለማድረጉ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱባት ይገኛሉ፡፡ የቻይና በቴክኖሎጂ መራቀቅ ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና የሚሰጥበት ስርዓት እስካልዘረጋ ድረስ ጥያቄዎቹ ወደፊትም ይቀጥላሉ፡፡
በምሕረት ሞገስ
ዛሬ እንደቀድሞው በተበላሹ መኪኖች ሥር እየተንከባለለ አይሠራም፡፡ የመካኒክነት ሥራውን ተወት አድርጐ ሞባይሉንና መፅሐፍ ቅዱሱን በጥቁር ቦርሳው አዝሎ በየመንገዱ ይዘዋወራል፡፡
29ኛው ኦሊምፒያድ በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ነው፡፡ በቤጂንግ ሲካሄድ ለሰነበተው የቤጂንግ ኦሊምፒክ ቻይናውያን ልዩ ድምቀትን የሰጡት በዝግጅቱ ብቻ ሳይሆን በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የበላይነታቸውን ጭምር ማረጋገጣቸው ስለስኬታቸው እንድናስብ እንገደዳለን፡፡
ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት እንደምትፈጽም አስታወቀች
የዩናይትድ ስቴትስና የፖላንድ የፀረ ሚሳኤል ግንባታ ስምምነት አዲስ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እንደሚፈጥር ያስጠነቀቀችው ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል አስታውቃለች፡፡
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.