Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ከውድቀትም መማር ይቻላል
ከውድቀትም መማር ይቻላል Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
በረቡዕ የካቲት 26 ቀን 2000 በፖለቲካ ገጽ ላይ ከአቶ ግርማይ ሃደራ ጋር ያደረጋችሁትን ቃለ መጠይቅ በደንብ አነበብኩትና የሚከተለውን ለማለት ፈለግኩ፡፡
 
አቶ ግርማይ እንዳሉት አራት ፓርቲዎች፤ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት እና የኦሮሞ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ ግንባር ፈጥረዋል፡፡ በእርግጥ ግንባር መፍጠሩ የሚበረታታ ሲሆን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ከተናጥል ይልቅ በጋራ ቢታገሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያስችላል፡፡ ነገር ግን ካለፉት ጥምረቶች በመነሳት ምን እናድርግ? እንዴት እንሂድ? ብለው ካለፉት ጥምረቶች ተገቢ ትምህርት መቅሰም አለባቸው፡፡ አቶ ግርማይ ግን ከዚህ በተቃራኒ ካለፉት ጥምረቶች ወይም ኅብረቶች ምንም አንማርም ማለታቸው ቅር አሰኝቶኛል፡፡ ምክንያቱም ከውድቀትም ብዙ መማር ይቻላልና፡፡ ለውድቀታቸው ምክንያት ምን ነበር ብሎ ያንን ላለመድገም ይበጃልና፡፡

(ጎሣዬ ዋቆ፣ ከቡራዩ)
 
< Prev   Next >