|
Sunday, 09 March 2008 |
|
የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ጽ/ቤት ከ2000 ዓ.ም ጋር በማያያዝ ብሔራዊና የመታሰቢያ በዓላት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲያከብርና ሲያስከብር መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ዓድዋን፣ የክርስቲያን፣ የሙስሊም በዓላት፣ የሴቶች ቀን የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ከ71 ዓመት በፊት በኢጣሊያ ፋሽስት የተጨፈጨፉትና የተፈጁት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የካቲት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ሲዘከር የሚሌኒየም ጽ/ቤቱ ከቁም ነገር አስገብቶ አለማክበሩና አለማስከበሩ ከምን የመጣ ችግር እንደሆነ አልተረዳኝም፡፡
ሪፖርተር ጋዜጣ በየካቲት 12 እትሙ እንደጻፈው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥትና በደርግ ዘመን የመጀመሪያ ዓመታት በብሔራዊ በዓልነት ይከበር የነበረው ወደ መታሰቢያነት እንዲወርድ የተደረገው ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል፡፡
(ዮሐንስ ተክሉ፣ ከሳሪስ) |