Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Sep 07th
Home
"ቅንጅት ዱሮም እንደ ድሪቶ የተሰፋ... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
"ቅንጅት ዱሮም እንደ ድሪቶ የተሰፋ ነው እንጂ የተደራጀ አልነበረም"
አቶ በድሩ አደም

አቶ በድሩ አደምን በቀድሞው ቅንጅትና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሰለሞን ጐሹ አነጋግሯቸዋል፡፡
 
ሪፖርተር፡- በግለሰብ ፖለቲከኛና በፓርቲ ፖለቲካ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

አቶ በድሩ፡-
ጥፋት ሲፈፀም ሁልጊዜ ከማልቀስ በጋራ የሕዝብ እንባ ላብስ በማለት ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ገብቻለሁ፡፡ በወቅቱ በኢህአዴግ የግል ተወዳዳሪዎችን ሞራል የሚነካ ሕግ ወጥቶ ነበር፡፡ ለፓርቲ አባላት በምርጫ ለመወዳደር 500 ድጋፍ ድምፅ ያስፈልግ ነበር፡፡ እሱ ቀርቶ ወደ ምንም አያስፈልገውም ሲቀየር ለግል ተወዳዳሪ ግን የነበረው 1"000 ድጋፍ ድምፅ አልተቀየረም፡፡ ወደ ፓርቲ ከገባሁ በኋላ በአጭር ጊዜ ነው ትክክለኛ ቦታ እንዳልገባሁ የተረዳሁት፡፡ በወቅቱ ጉድለቱን ለመናገር ምርጫ ደርሶ ስለነበር ተፅእኖ ነበረብኝ፡፡ ከፓርቲው አባላት ጋር በፓርቲውና በአመራሩ ጉድለት ዙሪያ ብዙ ተከራክሬያለሁ፡፡ የግለሰቦች የሥልጣን ጥመኝነት ነበር፡፡ የጋራ አመራር በወረቀት ላይ እንጂ በተግባር አልነበረም፡፡ በጋራ መደራጀቱ ለሀገርም ለሕዝብም ለእኛም ጠቃሚ ቢሆንም ተመሳሳይ አላማ እውነተኛ ሕዝባዊ ፍቅርና ስሜት ያላቸው በቂ ሰዎች በቅንጅት ስላልታቀፉ ፓርቲው አደጋ ላይ ወድቋል፡፡

ሪፖርተር፡- የእናንተ እናት ፓርቲ ቀስተ ደመና የመኢአድና የኢዴአፓ መድኀን ፓርቲዎችን ለማስታረቅ ብሎ የቀድሞውን ቅንጅትን በበላይነት ተቆጣጥሯል ተብሎ ይተቻል፤

አቶ በድሩ፡-
መኢአድንና ኢደአፓ መድህንን ለማስታረቅ ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡ አልተሳካም፡፡ የቀስተ ደመና መሪዎች የአስታራቂነት ሚና ሳይሆን የተጫወቱት አቋማቸውን መጫን ነበር፡፡ ይሄን ደግሞ ሀገሪቷ ላይም ደግመውታል፡፡ የአምባገነንነትና የገዢነት ስሜት ይንፀባረቅበት ነበር፡፡ ለዚህ በር የከፈተለት የመኢአድና የኢዴአፓ መድኀን እርስ በርስ አለመጣጣምና አለመስማማት ነው፡፡ የተወከለበት ቦታ ብቻ ሳይሆን ያልተወከለበትንም በበላይነት ይቆጣጠር ነበር፡፡ በሁሉም አይነት እንቅስቃሴዎች ሌሎቹን ፓርቲዎች ያገል ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- ከግለሰቦች የሥልጣን ፍላጎትና ሽኩቻ ባሻገር የቀድሞውን ቅንጅት የመሰረቱት አራት ፓርቲዎች ርዕዮተ አለማዊ ልዩነት ነበራቸው?

አቶ በድሩ፡-
ሊበራል ቡርዥዋ አመለካከት እናራምዳለን ብለን ነው የተነሳነው፡፡ እርግጥ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እኛ ሶሻል ዲሞክራቶች ነን ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን ከሥልጣን ጥመኝነት በዘለለ የርዕዮተ ዓለም ልዩነቱ ችግር አልነበረም፡፡

ሪፖርተር፡- መኢአድና ኢዴአፓ መድኀን ሕብረብሔራዊ ፓርቲዎች ከመሆናቸው በፊት አማራ ተኮር ፓርቲዎች ነበሩ፡፡ የቀድሞው ቅንጅት በርካታ አባላትም አማራዎች ናቸው፡፡ የዶ/ር ብርሃኑ እና የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ልዩነትንም ከብሔር ጋር የሚያያይዙት አሉ፤

አቶ በድሩ፡-
ይህን ያየሁት ከታሰርኩ በኋላ ነው፡፡ የዘር ልዩነት በእርግጥም አለ፡፡ ዶ/ር ብርሃኑም ሆነ ኢንጅነር ኃይሉ የብሔራቸውን ሰዎች ይፈልጉ ነበር፡፡ የዘር ብቻም ሳይሆን የሀይማኖትም ልዩነት አለ፡፡ ይህን ከእስር በፊት አላየሁም፡፡

ሪፖርተር፡- የታሰሩት በግለሰብ ደረጃ ነው በፓርቲው ስም?

አቶ በድሩ፡-
የታሰርኩት በቅንጅት ስም ነው፡፡ ነገር ግን እኔ በቅንጅት ምክር ቤት አባልነት ተመርጬ እውነቱ እስኪወጣ ድረስ አልቀበልም ብዬ ተቀምጫለሁ፡፡ ተቃውሞዬን በፅሁፍ ባለማስቀመጤ መንግሥት ያሰረኝ በቅንጅት አባልነት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በቅንጅት ክስ ከዳንኤል በቀለና ከነፃነት ደምሴ ጋር በመሆን ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ ለምን?

አቶ በድሩ፡-
እንደታሰርን እንከላከል አንከላከል በሚል ጭቅጭቅ ተነሳ፡፡ እኔ እከላከላለሁ አልኩ፡፡ ምክንያቱም ወደ ምርጫ ስገባ በዚህ ህገ መንግሥትና ባሉት ህጎች ወይም የፍትህ ስርዓት እዳኛለሁ ብዬ ነው የገባሁት፡፡ ከታሰርኩ በኋላ በፍትህ ስርዓቱ አላምንበትም በማለት አልዳኝም ማለት ራሴን መካድ ነው፡፡ የቀረበብኝን ፣ወያኔ ወደ በረሀ ይመለስ፣ የሚል ክስም አላልኩም፡፡ ተከራክሬ ከሰባት ክሶች ሁሉ ነፃ ሆኜ ነው የወጣሁት፡፡ "ኢሕአዴግ አንድ በፈጣሪ ሁለት በእናንተ ጡንቻ የዛሬ ሳምንት ወደ ነበረበት ይመለሳል" ነው ያልኩት፡፡ ዳኞቹም በእናንተ ጡንቻ የሚለው ስለሚያነሳሳ መብራራት ነበረበት አሉኝ፡፡ እርግጥ ሚያዚያ 3ዐ በአብዮት አደባባይ ያደረግኩት ንግግር ሕዝቡን ለግንቦት 7 ምርጫ ለማነሳሳት ነበር፡፡ የነበረው የሕዝብ ጡንቻ ካርድ ነበር፡፡ ከጥይትም ከዱላም የባሰ ገሎ የሚያነሳ የምርጫ ካርድ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 487 መሠረት የ6 ወር ቀላል እስራት ወይም 5ዐዐ ብር እንድታሰር ተፈረደብኝ፡፡ ነገር ግን ከዚያ በላይ በመታሰሬ በነፃ ተለቅቄአለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የዶ/ር ብርሃኑና የኢንጅነር ኃይሉ ልዩነት የቅንጅት ዓለም አቀፍ አመራርና የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤትን በመመስረት የበለጠ የተባባሰበት ሁኔታ እንዳለ ተነግሯል፡፡ በእስር ቤት የነበረው ሁኔታ ምን መልክ ነበረው?

አቶ በድሩ፡-
እስር ቤት በነበርንበት ወቅት ብዙ ችግር ይፈጥር የነበረው ዶ/ር ብርሃኑ ነው እንጂ ኢንጅነር ኃይሉ አልነበሩም፡፡ ብርሃኑ ለቅንጅት ዓለም አቀፍ አመራር ስድስት እጩዎችን በቀጥታ ያስተላልፋል . . .

ሪፖርተር፡- ኢንጅነር ኃይሉ በወቅቱ አልተሳተፉበትም?

አቶ በድሩ፡-
እንዲቋቋም ተስማምተዋል፡፡ ዝርዝሩ ላይ አልገቡም፡፡ እርግጥ ዶ/ር ብርሃኑ ነግሬው ተስማምተዋል ይላል፡፡ ኢንጅነሩ ግን አልሰማሁም ይላሉ፡፡ የተቋቋመው አመራር ከስድስት አባላት ውስጥ ሦስት ቀስተ ደመና ሁለት የመኢአድ ደጋፊ እና አንድ የኢዴአፓ መድኀን አባል ነው፡፡ ይህን ብዙዎቻችን ተቃውመናል፡፡ ከሦስቱም ድርጅቶች አራት አባላትን ያቀፈ (ኢዲሊ በውጭ ተወካይ አልነበረውም) የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት ተቋቋመ፡፡ ሥራ ሲጀምሩ እርስ በርስ መጋጨትና መጠላለፍ ጀመሩ፡፡ አንዱ አንዱን ገንዘብ አጠፋህ በማለት መካሰስ ጀመሩ፡፡ የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት ሲቋቋም ዶ/ር ብርሃኑ አይኑርበት እንጂ መነሻው ኢንጅነር ኃይሉ ብቻ አልነበሩም፡፡ መነሻ ሀሳቡን ያቀረቡት ሌሎች ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- የቅንጅት ዓለም አቀፍ አመራርና የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት ልዩነት የዲያስፖራውን ድምፅ በመክፈል ቅንጅቱን አላዳከመም? በአሁኑ ወቅትስ የዲያስፖራው ሚና ምንድነው?

አቶ በድሩ፡-
የዲያስፖራው ለሁለት መከፈል ቅንጅትን አላዳከመውም፡፡ የቅንጅቱ ለሁለት መከፈል ግን የዲያስፖራውን ሚና ከፍሎታል፡፡ የችግሩ ምንጭ ከዚህ ነው፡፡ ገንዘብ ጠፍቷል ተብሎ ኘሮፖጋንዳ ተጀመረ፡፡ አንዱ አጠፋህ ይባላል፡፡ ነገር ግን መልስ አይሰጥም፡፡ ከእስር ሳንፈታ ወደዚያው ለመሄድ ወሰንን፡፡ ሐምሌ 2ዐ በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል በተፃፈ ደብዳቤ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ደጋፊ የሆነው የቅንጅት ዓለም አቀፍ አመራር እና ኢንጅነር ኃይሉ ደጋፊ የነበረው የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት እንዲፈርሱ ተደርጎ በድጋፍ ሰጭነት እንዲቀጥሉ ተደረገ፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ወደ አሜሪካ አቀናን፡፡

ሪፖርተር፡- ከኢንጅነር ጋር አብረው በመጓዝ የዶ/ር ብርሃኑን ቡድን ይቃወሙ ነበር፡፡ ምክንያትዎ ምን ነበር?

አቶ በድሩ፡-
እነሱ ሐምሌ 13 እኔ ሐምሌ 3ዐ ቀን 1999 ዓ.ም. ነው የወጣነው፡፡ ልጆቻቸው የተጎዱባቸውን ቤተሰቦች እየዞርኩ እፈልግ ነበር፡፡ ለሚሌኒየሙ እና ለረመዳን ወር በዓል የሆነ ነገር ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ሲበዙብኝ ኢንጅነርን አማከርኳቸው፡፡ ተስማሙ፡፡ ለዚያ የሚሆን ብር ከመኢአድ ሒሳብ ላይ ለማውጣት አሰብን፡፡ ኢንጅነር ከፈረመ በኋላ ቀሪዎቹ ሁለት ፈራሚዎች አንዱ ውጭ ነበር ሀገር ውስጥ ያለው አልፈርምም ስላለ ተበድረን ሰጠን፡፡ ኢንጅነር ታመው ወደ አሜሪካ ሄዱ፡፡ ከዚያ ጠርተውኝ ሄድኩ፡፡ ዲያስፖራውን አብረን እንድናሳምን ነው፡፡ እኔም የተቻለኝን አድርጌአለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ዲያስፓራው የሁለቱን ቡድን ልዩነት እንዴት ነበር የተቀበለው?

አቶ በድሩ፡-
ሕዝቡ ቅንጅት ለሁለት በመከፈሉ በጣም አዝኗል፡፡ መጀመሪያ የዶ/ር ብርሃኑን ቡድን አምኖ ነበር፡፡ በኋላ እውነቱን ሳስቀምጥላቸው በብዛት ተመልሰዋል፡፡ ተፀፅተዋል፡፡ ሒሳቡም ኦዲት ተደርጓል፡፡ ከ700 ሺህ ዶላር እስከ 1.2 ሚሊዮን ዶላር እንደተሰረቀ ቢገለፅም በቅንጅት ሒሳብ ይህን ያህል ብር ኖሮ አያውቅም፡፡ ይህን የፈጠራ ክስ ያሰማው የዶ/ር ብርሃኑ ቡድን ነው፡፡ በአሜሪካ ሕግ መሠረት ሒሳቡ ሲጣራ የተጭበረበረ ብር አልነበረም፡፡ ይህን ክስ ያሰሙት ላይም ክስ መስርተናል፡፡ እስራኤላዊ የሆነ በአሜሪካ ሕግ መሠረት ቻርተርድ የሆነ አካውንታንት ነው ሒሳቡን ኦዲት ያደረገው፡፡ ክሱን አምኖ የነበረው ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልም በቅርቡ የኦዲት ሪፖርቱን ተከትሎ ድሮም ከስሼ አላውቅም ብሎ ክዷል፡፡ እንደውም ለአቶ አባይነህ ብርሃኑ በአቢሲኒያ ባንክ በኩል የተላከው 7500 ዶላር የት እንደደረሰ አልታወቀም፡፡

ሪፖርተር፡- ቡድኑ ወደ ተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተጨማሪ የልዩነት መንስኤዎች እንደተገኙ ይነገራል፤

አቶ በድሩ፡-
ለመንቀሳቀስ ግብረ ኃይል ሲመሰረት ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፡፡ ምክንያቱም ተጠሪነቱ ለፓርቲው ስላልነበር፡፡ ኢንጅነር ኃይሉ ግን የግብር ኃይሉን ሰብሳቢ ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያትን አደረገ፡፡ ዶ/ር ታዬ በመስሪያ ቤቱ የተሾመውን ሻለቃ ዮሴፍን ከቢሮው ያባረረ ነው፡፡ ሐምሌ 2ዐ የቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት ቢፈርስም የምክር ቤቱ ኘሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ታዬ በእንቅስቃሴአችን አሁንም ምክር ቤቱ እንዳለ ያወሩ ነበር፡፡ እኔ ይህንን አልቀበልም አልኩ፡፡ በዲያስፖራው የተመረጡ ሰዎችን እንደ ሌባ ተቆጥረው አብረው እንዳይሄዱ ተደርገው (ይህም ስንታሰር ለማስፈታት ብዙ የጣሩ፣ የኢንጅነሩን ዓይን ያሳከሙ መሆናቸው ተዘንግቶ) መካሄዱ ለእኔ  ክህደት ነበር፡፡ የቅንጅት አምስት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ሲታገዱ አላውቅም፡፡ ተጨባጭ ጥፋት ከተገኘ ተወያይተን አጥፊዎቹን ማገድ ነው ያለብን፡፡ ውክልናውም በሕጉ መሠረት መሆን ነው ያለበት፡፡ አቶ ገብረፃድቅ፣ ዶ/ር በዛብህ፣ ሻለቃ አድማሱና ወ/ሮ ንግሥትም አያውቁም፡፡ እኩልነት የተጠበቀበት የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረበት የዘርና የሃይማኖት ልዩነት የማይደረግበት ስርዓት ለመፍጠር የምታገል ሰው ነኝ እንጂ ፣አቤት ጓድ ሊቀመንበር፣ እያልኩ የማጎበድድ አይደለሁም፡፡ መጨረሻ ፌብሩዋሪ 3 ሎስ አንጀለስ ላይ ከህዝብ ጋር ስብሰባ ለማድረግ አዳራሽ ከተከራየን በኋላ ኢንጂነር ሞገስ ይቅርታ ካልጠየቀኝ መግቢያ ካርዱም በቅንጅት ዓለም አቀፍ ምክር ቤት ሥም ካልሆነ ጉባኤውም ላይ ዶ/ር ታዬ አብሮኝ ካልተቀመጠ በማለት ኢንጂነር ኃይሉ ስብሰባውን ሲሰርዘው ሁሉም ነገር በቃኝ፡፡ በቃኝ ብዬ ጥዬ ወደ ሀገር ቤት መጣሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ፓርላማ መግባት አለመግባት ከውይይት እስከ ውጤት አጨቃጫቂ ቢሆንም የኢንጅነሩ ውሳኔ የፓርቲውን የአሁኑን ሁኔታ ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው እየተነገረ ነው፡፡ የእርስዎ አቋም ምንድን ነው?

አቶ በድሩ፡-
ቅንጅት በፊትም ቢሆን አልነበረም፡፡ ህዝቡ ነው የተቀናጀው፡፡ የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት አመራረጥ ችግር ነበረበት፡፡ ወ/ት ብርቱካን ያለ ምንም ልምድ ነው የቅንጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆነችው . . . .

ሪፖርተር፡- ከላይ እንደገለፁልኝ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሥልጣን ጥም ካለበት ወ/ት ብርቱካን እንድትመረጥ እንዴት ሆነ?

አቶ በድሩ፡-
አንደኛ ኦሮሞ ነች፤ ሁለተኛ ሴት ነች፡፡ በዚህ ተጠቅሞ ልደቱን ከጣለ በኋላ እሷን አሻንጉሊት በማድረግ ለመጫወት አስቦ ነው፡፡ ፓርቲዎቹ ያላቸውን ድርሻ ካየን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መሆን የነበረበት አቶ ልደቱ አያሌው ነው . .

ሪፖርተር፡- ምንን ታሳቢ በማድረግ?

አቶ በድሩ፡-
በቁጥር ብዛት፡፡ ከመኢአድ በመቀጠል ብዙ አባላት ያሉት ፓርቲ ኢዴአፓ መድኀን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ኢድሊም ያቀረበው እጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አረዳን እንደነበር የሚናገሩ አሉ፤

አቶ በድሩ፡-
ልክ ነው፡፡ ዶ/ር አለማየሁን ጥለው ሙሉነህ እዩኤልን እንዲመረጥ ያደረጉት በተንኮል ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በወቅቱ ይህን ካወቁ ለምን አልተቃወሙም?

አቶ በድሩ፡-
ምርጫው ላይ አልተገኘሁም፡፡ በሌለሁበት ነው ቀስተ ደመናም ሆነ ቅንጅቱ የመረጠኝ፡፡ የቀረሁት ነገሩ ስላላማረኝ ነው፡፡
 
ሪፖርተር፡- ከአራቱ ፓርቲዎች ኢዴአፓ መድኀን ጥሎ ሲወጣ በወቅቱ ምን ተሰማዎት?

አቶ በድሩ፡-
ኢዴአፓ መድኀን ከሌሎቹ ፓርቲዎች የተለየ ዓላማና የፖሊሲ ልዩነት የለውም፡፡ በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ነው የለቀቀው፡፡ የኢዴአፓ መድኀን ፍፁም አብላጫ ድምፅ በወቅቱ ልደቱን ተከትሎ አልወጣም፡፡ አቶ አየለ ጫሚሶም ሆነ አቶ ተመስገን ዘውዴ የወጡት ከኢዴአፓ መድኀን ነው፡፡ ፓርቲው አሁንም በቅንጅት ውስጥ ነው፡፡ ልደቱን ግን እንዲወጣ ያደረጉት የሌሎች ፓርቲዎች በተለይም መኢአድና የቀስተ ደመና መሪዎች ናቸው፡፡ ግን እሱም የኢድሊውን ዶ/ር አለማየሁ አረዳን ገፍተው ከጣሉት አንዱ ነበር፡፡ ይሄ ያሳዝነኝ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- የነልደቱ ልዩነት ሚዲያ ላይ በመውጣታቸው እንጂ አመራሩ ላይ እናንተንም በወቅቱ ቅሬታ ነበራችሁ ማለት ነው?

አቶ በድሩ፡-
አዎ፡፡ ልዩነታችን በሚዲያ በመውጣትና ባለመውጣት መካከል ነው፡፡ ፓርቲው ውስጡ ባዶ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ኢህአዴግም ፓርቲው ውስጡ ባዶ እንደሆነ ቢያውቅ አያስረንም ነበር፡፡ ህዝቡም ይሕን አያውቅም ነበር፡፡ ወደ ሚዲያ እንዳልወጣ ንፁሀን ዜጎችን በሽምግልና ይልኩ ነበር፡፡ እነዚህ ንፁሃን ሰዎች ውስጣችን የተጠናከረና አንድነቱ የተጠበቀ ለሀገር ፍፁም የሆነ አቋም ያለው አድርገው ይወስዱናል፡፡ ሕዝቡ አሁንም እውነታውን የሚያውቀው አልመሰለኝም፡፡

ሪፖርተር፡- የታሰራችሁት ፓርላማ የገቡትን ፣ከሀዲ፣ አድርጋችሁ ትቆጥሩ ነበር ይባላል፤

አቶ በድሩ፡-
ይሄ የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ ፓርላማ ላለመግባት ሕዝብን በማነጋገር የተያዘ አቋም ነው፡፡ ማነጋገር የለብንም የሚል አቋም ነበረኝ፡፡ ፓርቲ የፖለቲካ መመሪያ ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ህዝብን መመሪያ መጠየቅ የለበትም፡፡ ምርጫው ስለተጭበረበረ ህዝብን መጠየቅ አለበት ቢባል እንኳን አዲስ አበባ ስላልተጭበረበረ ተገቢ ቦታ አይሆንም፡፡ አንዴ ህዝቡ ፣ፓርላማ አትግቡ፣ ካለ በኋላ ፓርላማ ገብቼ ልሰራ አልችልም፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የማቀርበውን ሪፖርት ህዝብ ሳላናግር ውክልናዬን ሳልፈፅም ማቅረብ አልችልም፡፡ በግሌ ፓርላማ የገባውን ፣ከሀዲ፣ ነው ብዬ አላምንም . . . .

ሪፖርተር፡- በቁጥር ምን ያህሉ ይህ እምነት ነበረው?

አቶ በድሩ፡-
ብዙዎቹ ይህ እምነት ነበራቸው፡፡

ሪፖርተር፡- እስር ላይ የነበረው አመራር የፓርላማ አባላትን የቅንጅቱ አካል አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር?

አቶ በድሩ፡-
እነሱን የመፈለግ ነገር ፈፅሞ አልነበረውም፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ ወልደማርያም ግን የተለየ አመለካከት ነበረው፡፡ ፓርላማ መግባታቸውን አይኮንንም ነበር፡፡ በተወሰነ መልኩ ኘሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተመሳሳይ ሀሳብ ነበረው፡፡

ሪፖርተር፡- ወ/ት ብርቱካን ከፓርላማው ቡድን ከአቶ ተመስገን ዘውዴ ጋር አብረው እየሰሩ ነው፡፡ በእስር ላይ የእሳቸው አመለካከትስ የተለየ አልነበረም?

አቶ በድሩ፡-
ወ/ት ብርቱካን ከእስር ሲፈቱ የፓርላማው ቡድን አይመለከተውም በማለት ነው ጥለዋቸው ወደ ውጭ የተጓዙት፡፡ እንደ ጠላት ነበር የምትቆጥራቸው፡፡ እኔ አቶ ተመስገን ዘውዴ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነ በፊትም እናገር ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- ስለመጭው ጊዜ ምን ያስባሉ?

አቶ በድሩ፡-
ቅንጅት ዱሮም እንደ ድሪቶ የተሰፋ ነው እንጂ የተደራጀ አልነበረም፡፡ የሦስት ወር ደቦ ነበር፡፡ ልዩነቱ ከአመራር ነው፡፡ በእኩልነት እምነት አልነበረውም፡፡ ህዝቡ በዚህ አዝኗል፡፡ ነገር ግን እንደገና ማደራጀትና መደራጀት ያስፈልጋል፡፡ ቺሊ የፒኖቼን ፓርቲ የጣለው የአራት ወር ፓርቲ ነበር፡፡ አርጀንቲና የዳንኤል ኦርቴጋ ፓርቲ የጣለው የስምንት ወር ፓርቲ ነበር፡፡ ለእኛም እድል ነበረን፡፡ አሁንም እርስ በርስ ከተጠናናንና ከተዋወቅን በቅርቡ በኬንያ የተገኘውን ዓይነት ድል ማስመዝገብ እንችላለን፡፡ ቅንጅት የጀመራቸውን ብዙ ነገሮች ኢህአዴግ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከኢንጅነር ቡድን ጋር ይቀጥላሉ?

አቶ በድሩ፡-
አልቀጥልም፡፡ አሰራሩ ሁሉ አላስደሰተኝም፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ አብሬ አልቀጥልም፡፡
 
< Prev   Next >
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
“የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ...
“የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ እና የተክለጻድቅ መኩሪያ ድርሰቶች ከዕውቅናችን ውጪ ታትመዋል”

ቤተሰቦቻቸው

“ለማሳተም ሕጉ ይፈቅድልኛል”

አቶ ዓይናለም መዋ - አሳታሚ

በሔኖክ ያሬድ

ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ የደረሱት “መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር” የተሰኘው መጽሐፋቸው ከቤተሰባቸው እውቅና ውጪ ተሰርቆ መታተሙንና በሕግም እንደሚጠይቁ የልጅ ልጃቸው ሲገልፁ፣ የአቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የታሪክ መጻሕፍት ያለፈቃዳችን ታተመ ሲሉ የደራሲው ልጅ አመለከቱ፡፡ አሳታሚው የዓይናለም መጻሕፍት መደብር ባለቤት መጽሐፉን እንደገና ለማሳተም ሕጉ ይፈቅድልኛል ብለዋል፡፡
Read more...
 
Zena
Image “ኢትዮጵያ በችጋር አደጋ ውስጥ ነች”
የተባበሩት መንግስታት ኃላፊ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ግልጋሎት ኃላፊ ጆን ሆልምስ በኢትዮጵያ ያለውን የረሃብና ድርቅ ሁኔታ ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አርባ ምርጭ ዙሪያን ከጎበኙ በኋላ “ኢትዮጵያ በችጋር አደጋ ወስጥ ነች” ሲሉ ተናገሩ፡፡
Editorial
Image እውነት የሕግ የበላይነት አለን?
ሰው ሰውን ገድሎ ይከሰሳል፡፡ ተናዶ ነው፤ ራስን ለመከላከል ነው፣ በድንገት ነው፤ በሚል በሕግ ፊት ክርክር ይደረጋል እንጂ፣ ሕግ ገደል ይግባ ብሎ ገዳዩን የሚተው የለም፡፡ የሕግ የበላይነት ለማስከበር ተብሎ ገዳይ ይከሰሳል፡፡ ሌባም እርቦት ነው የሰረቀው ተብሎ ከክስ አይድንም፡፡ የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ ተብሎ ሕግ ፊት ይቀርባል፡፡ ወዘተ.
 
Politics
Image ‘ሁሉንም ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች...
‘ሁሉንም ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች በኪራይ ሰብሳቢነት አልፈረጅንም’

አቶ በረከት ስምኦን

በፍሬው አበበ

ኢሕአዴግ 7ተኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ከመስከረም 5-9/2001 በሃዋሳ ከተማ ያካሂዳል፡፡ ድርጅቱ “ስኬታማ ተግባሮችን በማስፋፋት የኢትዮጵያን ህዳሴ በፅኑ መሠረት ላይ እንገነባለን” በሚል መሪ ቃል በሚያካሂደው በዚሁ ጉባዔ ላይ በአምስት አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይወያያል፡፡
Briefs
ሙገር ከ4ዐዐ ሚሊየን ብር በላይ አተረፈ
የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርኘራይዝ ዘንድሮ 75ዐ ሺ ቶን የሲሚንቶ ምርት ለገበያ በማቅረብ ከታክስ በፊት ከ4ዐዐ ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ፡፡

 
Business & Economy
Image መድን ድርጅት 440 ሚሊዮን ለመሰብሰብ...
መድን ድርጅት 440 ሚሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ 563.6 ሚሊዮን ሰበሰበ

ገንዘብ በመመሪያው መሠረት እንደማይሰበሰብ ተገለፀ


በጋዜጣው ሪፖርተር

በኢትዮጵያ የመድን ኩባንያዎች የተቋቋሙት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ እስከ 1968 ዓ.ም ድረስ በአገሪቱ ከ13 ያላነሱ ኩባንያዎች በሥራ ላይ ነበሩ፡፡ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ በኋላ የመድን ኩባንያዎቹ ተወርሰው በአንድ ተጠቃልለው የዛሬውን የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን አስገኝተዋል፡፡
Shemach
እንደተጠበቀው ያልተረጋጋው ገበያ
በናታን ዳዊት

መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየወሰድኩ ነው ካላቸው እርምጃዎች ውስጥ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው ስንዴ ከውጭ ገዝቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች ማቅረብ ነው፡፡
 
Interview
Image “ሰልጥነው የወጡ ስፖርተኞችን...
“ሰልጥነው የወጡ ስፖርተኞችን መከታተል የእኛ ኃላፊነት አይደለም”

አቶ ተሾመ ጫካ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ወጣቶችና

ስፖርት ቢሮ የስፖርትና ትምህርት ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ

አቶ ተሾመ ጫካ ከደብረ ብርሃን በመምህርነት ተመርቀው ጋሙ ጎፋ ተመድበው ሠርተዋል፡፡ ለሁለት ዓመታት በርዕሰ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በ1980 ዓ.ም መጨረሻ ወደ አዲስ አበባ በመዘዋወር ከመምህርነቱ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አስተዳደር ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በወረዳ ምክር ቤት ሰብሳቢነትም አገልግለዋል፡፡ በ1990 በዞን ደረጃ የፐርሶኔል ኃላፊ፣ ቀጥሎም በዚያው ዞን የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ሆነዋል፡፡
Fermata
ዋሽንግተን ፓስት
ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከሄድኩባቸው የጋዜጣ ክፍሎች ሁሉ የማረከኝ “ዋሺንግተን ፖስት” ጋዜጣ ቢሮ ነው፡፡ ቢሮ ስላችሁ እንደ እኛ አገር የጋዜጣ ቢሮዎች (የመንግሥትም የግልም ማለቴ ነው) በአይን የሚቆጠር ድምር ያለው ሠራተኛ የሚገኝበት አይደለም፡፡
 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር - ሃሎ! ክቡር ሚኒስትር፣
- እሺ፣ ምን አዲስ ነገር አለ? በዛ ጉዳይ ዙሪያ?
- ቶሎ ብለን አንድ እርምጃ መውሰዱ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡
- አንተ ሰውዬ እንዲህ ዓይነት ነገር በስልክ አትናገር አላልኩህም፡፡ በል አሁን በአስቸኳይ ወደዚያ ቦታ እለፍና እንገናኝ
Life & Art
“በሥዕል ጥበብ ኅሊናን የማብራት...
“በሥዕል ጥበብ ኅሊናን የማብራት ተግባር ነው ያለው”

-    ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ

በሔኖክ ያሬድ

ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ በሥዕል ጥበብ ሙያው ይታወቃል፡፡ ቅድመ አብዮት ከአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/ቤት (1966) በኪነ ቅብ ዲፕሎማውን፣ በ1970ዎቹ ከሩሲያ በማስትሬት ዲግሪ በከፍተኛ ማዕርግ ተመርቋል፡፡
 
Social
Image የሌሊቷ ሱቅ በደረቴ
በምሕረት አስቻለው

ምሽት ሦስትና አራት ሰዓት ላይ ከቤቷ በመውጣት እስኪነጋ ብዙ ቡና ቤቶች በሚገኙበት አራት ኪሎ አካባቢ፣ አራት ኪሎ ሆቴል ፊት ለፊት ጀብሎ (የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን) ትሰራለች፡፡ ዝናብና የሌሊት ቅዝቃዜን መቋቋም፣ በጨለማ መሥራትን በሌላ በኩል ደግሞ በመጠጥ የናወዙ ጠጪዎችን አስቸጋሪ ባህርይ መታገስ የአማረች አምባው የሕይወት ግዴታ ነው፡፡
Science & Technology
Image ሽቶ ላልተወለዱ ልጆች አደገኛ ነው
ወደፊት ለሚወለድ ልጅ የመጀመሪያዎቹ ሦስት የእርግዝና ወራት እጅግ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ በእነዚህ ወራት ሽቶ እና መሰል መዓዛ ያላቸውን ቅመሞች የሚጠቀሙ እርጉዝ ሴቶች ወደፊት የሚወልዱትን ወንድ ልጅ ለመሃንነት ሊዳርጉት እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
Diaspora
ሀገራቸው ገብተው በልማት ሥራ...

ሀገራቸው ገብተው በልማት ሥራ ላይ የተሰማሩ ቤተሰቦች
በታደሰ ገብረማርያም

ዶክተር አማረ ጌታሁን በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ (እርሻ ኮሌጅ) ዲንና ተባባሪ ሮፌሰር ሆነው ሠርተዋል፡፡ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ከባሕር ዳር እስከ ማይፀምሪ ድረስ ያሉት የዘመቻ ጣቢያዎች ኃላፊ ሆነውም አገልግለዋል፡፡ በሰበታና በግንደበረት ዘመቻ ጣቢያም አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ከብት ሀብት ልማት ማዕከል በአፍሪካ (ኢልካ) በተመራማሪነትና በልዩ ልዩ ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል፡፡

 

Youth
Image የሥነ ተዋልዶ ጤና በከፍተኛ...
የሥነ ተዋልዶ ጤና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት

በምህረት አስቻለው

የስነተዋልዶ ጤና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምን ይመስላል? ከሥነ ተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ያሉባቸው ችግሮች ምንድን ናቸው? የሚሉትና ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች "የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን የሥነ ተዋልዶ ፍላጐትና መብት መመልከት የሁለም ሰው ኃላፊነት ነው" በሚል ርዕስ ነሐሴ 22 ቀን 2000 በግዮን ሆቴል በተካሄደው ብሔራዊ የከፍተኛ ተቋማት የሥነ ተዋልዶ ጤና ሁኔታ ኮንፈረንስ ተዳስሰዋል፡፡

 
Opinion
ኢሕአዴግ ለውጥ ለአወቃቀሩ፣...
ኢሕአዴግ ለውጥ ለአወቃቀሩ፣ ለውጥ ለአሰራሩ፣ ለውጥ ሕግን ለማክበሩ. .  .

ሃብታሙ በቀለ

ኢህአዴግ 7ኛውን የድርጅት ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ ከመስከረም 5 ቀን 2001 ጀምሮ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ ለኢሕአዴግ የድርጅት ጉባኤ ማካሄድ የተለመደ ነገር ባይሆንም፣ የመሪው የፖለቲካ ድርጅት እንደመሆኑ በሕዝቡ ዘንድ ጉባኤው ቀልብ መሳቡ አይቀርም፡፡ ከጉባኤው የሚመነጭ ሃሳብና የማጠቃለያው ውሳኔ ዜጋውን በተናጠልም በቡድንም ከሕይወቱ ጋር የሚገናኝ እንደመሆኑ የሕዝቡን ባይሆን እንኳ የሚዲያዎችን ትኩረት መሳቡ አይቀርም፡፡

Letter to Reporter
ከዚህ በላይ ሙስና ምን አለ?
ከጅቡቲ ወደብ ለተወረሱት ንብረቶች ዋት ኢንተርናሽናል ውሃ ሃብት ሚኒስቴርን ተጠያቂ ማድረጉን የሚገልጽ ዜና በነሐሴ 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቷል፡
 
Women
Image "እጅጌና አንገት አውጥተን ጆንያ ለብሰናል"

በሶማሊያ-እናት እስረኞች
በምሕረት አስቻለው

"በሞላና በተደላደለ ቤት እንኳ እናት ለልጇ የምታደርገው በቂ ነው አትልም፡፡ እኔም ልጄ በእስር ቤት ውስጥ በረሀብ፣ በችግርና በግርፋት ሲሰቃይ ዘወትር ነፍስና ስጋዬ ይለያይ ነበር፡፡ ያለ ምግብ ያለ ውሀ ለሰባት ቀናት ተጉዘናል፡፡ ውሀ ማግኘት የቻልነው በስምንተኛው ቀን ነበር፡፡ የሰባት ዓመት ሴት ልጄን ለክርስትና እናቷ ሰጥቼ የያዝኩት የአስር ዓመት ወንድ ልጄን ነበር" ከዚያድባሬ መንግሥት ወረራ በኋላ ለአስራ አንድ ዓመታት በሶማሊያ ወህኒ ቤት ታስረው የኖሩ ወ/ሮ ወሰኔ ተሊላ፡፡

 

Temuaget
"ኪራይ ሰብሳቢ" ሚዲያ አለ?

ቢኒያም ለገሠ

ሀሳብን በነጻ የመግለጽ እና የኘሬስ ነጻነት መሠረታዊነት በየአንዳንዱ አገር፣ በእኛም አገር ውስጥ፣ እንዲሁም እያንዳንዱ በፈረማቸው ወይም አብዛኛው አገር ፈርሞ ባፀደቃቸውና የራሱም አገር ሕግ አካል ባደረጋቸው ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶች የታወቀ የተቋቋመ እንዲሁም የተረጋገጠ ነው፡፡ ጉዳዩ የህግ እውቅና ጥያቄ ላይሆን ይችላል፣ አይደለም ይሆናል፡፡ ጉዳዩ ባመዛኙና በእርግጠኛነት ለህጉ የመገዛት ህጉን የአገር ወግና ባህል የህብረተሰቡ በመላ እሴት ማድረጉ ማድረጉን ማገዝ መፍቀድ ወይም መከልከል ላይ ነው፡፡ የአገራችን ሰው ህግ ሌላ ተግባር ሌላ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የሚለው ከሌሎች መካከል ይህንኑ ጭምር ነው፡፡

 

 
Law
የክልልና የፌዴራል ሥልጣን ክፍፍል...

የክልልና የፌዴራል ሥልጣን ክፍፍል
ያልተመለሱ አንዳንድ ጥያቄዎች

በሰለሞን ጎሹ

"ማንኛውም የወንጀል ክስ ወይም ማንኛውም የክስ አቤቱታ ለፖሊስ ወይም ለዐቃቤ ሕግ ማቅረብ ይቻላል፡፡ . . . የወንጀሉ ክስ ወይም የክሱ አቤቱታ ለዐቃቤ ሕጉ ሲቀርብለት . . . የተባለው ወንጀል እንዲመረመር ዐቃቤ ሕግ ሥልጣን ላለው ፖሊስ ማስተላለፍ አለበት"፡፡ (የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-ሥዓርዓት ህግ ቁጥር 16/1954 ዓ.ም".

 

Zennk
አራሽ ሲወቃና ሲሰፍር የተሰራለት ደንብ
አራሽ እህሉን ሲወቃና ሲሰፍር እንደ ደንቡ አሥራት ተቀባዩን ወታደርና ጭቃ ሹሙን ጠርቶ ይወቃል፣ ይሰፍራል፡፡ ብቻውን ሊወቃና ሊሰፍር አልተፈቀደለትም፡፡ እነዚሀን ሳይጠራና ሳይዝ ወቅቶ አጥርቶ ቢገኝ ግን ባያሰፍርም ቅጣቱ እንደ ደንቡ ባላሥራት ወታደር የሚገባውን አሥራቱን ተቀብሎ የቀረው ያውድማ ምርት ለመንግሥት ውርስ ይገባል፡፡
 
Delalaw
ወርቃችንን ወስደው መዳባቸውን
በአራቱም አቅጣጫ ብንጓዝ ታሪክ መምዘዛችን አይቀርም፡፡ ማንነታችንን የሚገልፁ ቅርሣ ቅርሦች፣ ሐውልቶችና ባሕላዊ እሴቶችን እናገኛለን፡፡ የሚያስማሙንና የማያስማሙን ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ የታሪካችን ስፋትና ጥበት፣ ርቀትና ቅርበት ሊያነጋግረን ይችላል፡፡ መነጋገር፣ መወያየት፣ መከራከር. . .ይገባል፡፡ ሃሳብና ሃሳብ ተፋጭተውና ተጋጭተው ነው ወደ ቁም ነገር የሚደረሰው፡፡
Teles
Image የእግር ጉዞን ለማስተማሪያ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ከሁለት ጓደኞቹ ጋር በመሆን ከአክሱም በመነሳት በአድዋ፣ በአንትጮ፣ ብዘት፣ አዲግራት፣ መቀሌ፣ ማይጨው፣ ወልዲያ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ደብረብርሃን በእግር በመጓዝ እስከ አዲስ አበባ ስለ ኤች.አይ.ቪ አስተምረዋል፡፡ ወጣት ዳንኤል የማነ፣ አማኑኤል ኪዳነና ሐፍቶም ገብረ ጊዮርጊስ ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር በመሆን በተለያዩ ከተሞችና የገጠር ወረዳዎች በእግራቸው በመጓዝ ስለ ኤች.አይ.ቪ ለማስተማር ያነሳሳቸውን ሁኔታ እንዲህ ገልጾታል፡፡ "ለቤተሰባቸው ብሎም ለአገርና ለወገናቸው የተለያዩ አገልግሎቶችን ማበርከት የሚችሉ ሰዎች ሲረግፉ ተመልክተናል፡፡ ከቤቱና ከጎረቤቱ በኤች.አይ.ቪ ወገኑን ያላጣ የለም፡፡ እኔም እናትና አባቴን በተመሳሳይ ሁኔታ አጥቻለሁ፡፡ የእናትና የአባቴ ነገር ደግሞ ብዙ ችግሮችን አስከትሎብኝ ስለነበር እኔ የገጠመኝ ችግር እንደ እኔ አይነቶችንም እንደሚገጥም በመረዳት አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ ለጓደኞቼ አማከርኳቸውና ኤች.አይ.ቪ ምርመራ አደረጉ፡፡ ከዚያም ስለ ኤች.አይ.ቪ ለማስተማር ተስማማን፡፡"

 

 
Sport
Image የኢትዮጵያ መታገድና የጉባኤው ትርምስ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ተካሂዷል፡፡ ከ76 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት 67ቱ ተገኝተዋል፡፡

Taxi
ሳይደርቅ በእርጥቡ
በታክሲ ጉዞ ነጥብ በነጥብ ከተከታተሉ የሚመዘገብ ነገር ይበዛል፡፡ ለወሬና ለጽሑፍ የሚበቃ ርዕሰ ጉዳይ አይጠፋም፡፡ ነባር የታክሲ ደንበኞች ብንሆንም ብዙውን ጊዜ ከመመስገንና ከመከበር ይልቅ ብሽቀትን አትርፈን እንገባለን፡፡ በሌላው የሥራ ዘርፍ ደንበኝነት እንደሌሎች አገሮች ባያስከብርም “እንኳን ደህና መጣችሁ”፣ “የት ጠፋችሁ?” መባሉ አይጠፋም፡፡ በታክሲ አገልግሎት ግን ደንበኛ ንጉሥ ነው፤ ደንበኛ ቢሳሳትም ትክክል ነው የሚለውን የቢዝነስ መሳቢያ መርህ ተቀባይነት የለውም፡፡ “ይህ ሰው ዓመቱን በሙሉ በእኛ ታክሲ ነው የተጓጓዘው” ተብሎ የታሪፍ ቅናሽም ይሁን ጥሩ መስተንግዶ አይደረግለትም፡፡
 
World
Image በባንኮክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳማክ ሱንዳራቫጃ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ባንኮክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡