Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow የአይ.ኤስ.ኦ ሰርተፊኬት በማግኘት...
የአይ.ኤስ.ኦ ሰርተፊኬት በማግኘት... Print E-mail
Sunday, 09 March 2008
Imageየአይ.ኤስ.ኦ ሰርተፊኬት በማግኘት የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ቀዳሚ ሆነ

በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና የአገልግሎታቸውን የጥራት ደረጃ ያረጋግጣል ተብሎ የሚታመንበትን የአይ.ኤስ.ኦ 9001 2000 ሰርተፊኬት ያገኙ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ቁጥር ወደ 16 አደገ፡፡ የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ሰርተፊኬቱን በማግኘት ቀዳሚ ሆነ፡፡
 
በጀርመንና በኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ በተቋቋመው የምህንድስና አቅም ግንባታ ፕሮግራም (ኢሲ.ቢፒ) እገዛ ስልጠና ተሰጥቷቸው የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬታቸውን የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም የተቀበሉት ኩባንያዎች ኤቢቢኤ አርክቴክስ፣ ኢኳቶር ኢንጂነሪግ ኃ.የተ.የግ.ማ፣ ላይፍ ኮንሰልት፣ ኤም.ኤጆ ኢንጅነሪንግ ኦርቢት ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማ፣ ቴዎድሮስ አበራ በቡልዲንግ ኮንስትራክተር ናቸው፡፡

ሰርተፊኬቱ በተሰጠበት ወቅት የኢ.ሲ.ቢፒ ዳይሬክተር ፒተር ካሮለር እንደገለፁት፣ ኩባንያዎቹ ከኢትዮጵያ ውጪ በተሠማሩበት የሥራ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ በሌሎች አገሮች የሚደረጉ ሥራዎችን ለማግኘት  እንደ አንድ የመወዳደሪያ መስፈርት የሚወሰደው ይህ ሰርተፊኬት ስለነበር ሥራውን ለመስራት ብቃት እንኳን ቢኖራቸው እድሉን ያጡ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የአይ.ኤስ.ኦ ሰርተፊኬት ካገኙት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ተክለ ብርሃን አምባዬ የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት አቶ ተክለ ብርሃን አምባዬ እንደገለፁት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ቢያንስ በአካባቢያችን ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ለመስራት ያስችለናል" ብለዋል፡፡

የአይ.ኤስ.ኦ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ የምህንድስና አቅም ግንባታ 16 ለሚሆኑ ኩባንያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት ለሠርተፊኬቱ ብቁ እንደሆኑ ጥረት ያደረገ ሲሆን ከእዚህ ስምንቱ ሰርተፊኬቱን ለማግኘት ችለዋል፡፡

ሰርተፊኬቱ በተሰጠበት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአቅም ግንባታ ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ዋልዋ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማሳደግ የዚህ አይነት የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቶችን የአገራችን ኩባንያዎች ማግኘታቸው ትልቅ ነገር እንደሆነና ለኮንስትራክሽን ግንባታው ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡

በሰርተፊኬቱ አሰጣጥ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ለዝግጅት ክፍላችን በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የእሴት ሰንሰለት ልማት አለም አቀፍ ገበያን መሰረት በማድረግ ምርትና ምርታማነትን፣ የምርት ሂደት፣ የምርት ጥራት፣ የቴክኖሎጂ ሁኔታና መሰል ወሳኝ ጉዳዮች አሰራር በመለወጥና በማሻሻል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎችን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ መሆኑን ያትታል፡፡

የእሴት ሰንሰለት ልማት ማዕከል በማድረግ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በ13 ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ እየተሳተፉ ካሉት 3 የኮንስትራክሽን አስተዳደር ድርጅቶች 13 የዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅቶች 13 የሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች ውስጥ ስምንቱ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የአይ.ኤስ.ኦ 9001 ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን መግለጫው አስታውሶ በተጨማሪም አራት ድርጅቶች ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ሲሆን አስራ ሦስት ድርጅቶች ደግሞ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በቀጣይ የሚካተቱ እንደሚሆኑ አመልክቷል፡፡

በቆዳ ዘርፍ 12 ኩባንያዎች ቀጥተኛ የቴክኒክ፣ የአስተዳደርና አለም አቀፍ ገበያ ትስስር ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሁለት ጫማ አምራች ኩባንያዎች (ራስ ዳሽንና ካንጋሮ"፣ ሁለት ቆዳ ፋብሪካዎች (ብሉ ናይልና ባቱ) ከአንድ የጀርመን ኩባንያ ጋር በገበያና በቴክኖሎጂ እንዲተሳሰሩ በመደረጋቸው የኤክስፖርት ሽያጫቸው እድገት በማሳየት ላይ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡
 
ከዚህም ሌላ በፋርማስቲካል ዘርፍ ስምንት ኩባንያዎች የጂኤምፒ ሰርተፊኬት ለማግኘት እንዲችሉ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከስምንቱ ኩባንያዎች ስድስት የጂኤምፒ ሰርተፊኬት ደረጃ ሊያሟሉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >