| የፌደሬሽኑ የደመወዝ ማስተካከያ... |
|
|
| Sunday, 09 March 2008 | |
|
የፌደሬሽኑ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲፋጠን አሳሰበ
ለመንግሥት የልማት ድርጅት ሠራተኞች የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ የደመወዝ ማስተካከያ ለማድረግ በመካሄድ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ፈጠን ባለ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ እንዲሁም እያንዳንዱ የግል ድርጅት ባለቤቶች ሠራተኛው በማኀበር የመደራጀት መብቱን ከማደናቀፍ እንዲቆጠቡ በኢትዮጵያ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የቱሪዝምና ሆቴሎች ጠቅላላ አገልግሎት ሠራተኞች ማኀበራት እንዱስትሪ ፌደሬሽን ጉባኤ አሳሰበ፡፡ ከስድሳ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተውጣጡ ሠራተኞች ተሳታፊ የሆኑበትና የካቲት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በኢሠማኮ የስብሰባ አዳራሽ የተካሄደው ይኸው 25ኛ ጉባዔ እንዳመለከተው የደመወዝ ማስተካከያው የሚከናወነው መንግሥት ያወጣውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ነው፡፡ አንዳንድ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የቦርድ አባላትና ሥራ አስኪያጆች መንግሥት ያወጣውን መመሪያ በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ጉባዔው አመልክቶ መመሪያውንም በተዛባ መልኩ የሚተረጉሙት ማስተካከያ የሚደረግላቸው የወር ደመወዛቸው ከ325 ብር በታች ለሆኑ ሠራተኞች ብቻ እንጂ ከዚህ በላይ ያለት አይመለከታቸውም በማለት መሆኑን ጉባዔው አስረድቷል፡፡ ኢሠማኮና ኮንፌዴሬሽኑ በጋራ ሆነው ይህ ዓይነቱን የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ለሁሉም ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርጉ ጉባኤው አሳስቧል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |