Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ሥነ ተዋልዶ ጤና የገጠር ሴቶች ራስ ምታት
ሥነ ተዋልዶ ጤና የገጠር ሴቶች ራስ ምታት E-mail
Sunday, 06 January 2008
በሴቶች ጤና ላይ የሚከሰቱ ችግሮች በአብዛኛው ከሥነ ተዋልዶ ጤና ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ›”Ç”É የጤና ምርመራዎች በተወሰኑ አካባቢያዋች ብቻ መገኘታቸው ችግር ነው፡፡ በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቅድመ ካንሰር ምርመራ ሲሆን የሚገኘው በአዲስ አበባ በሚገኙ ጥቂት የጤና ማዕከላት ነው፡፡

ንፅህናው ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥን ጨምሮ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር የተያያዙ ችግሮች በሴቶች ጤና ላይ የተጋረጡ እንቅፋቶች ናቸው፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት አለመስፋፋት ሴቶች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በዚህም ሳቢያ ለተደራራቢ ወሊድ፣ ለጤና ቀውስና ለሞት ይዳረጋለ፡፡

የኢትዮጽያ ፅንስና ማህፀን ሐኪሞች ማኀበር በቅርቡ ያወጣው ጥናት እንደሚያስረዳው ንፅህናው ያልተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አሁንም /በተለይ በአዲስ አበባ/ ለኢትዮጵያ እናቶች ሞት በቀዳሚ ምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡

ይኸው ጥናት እንደሚለው በዘጠኝ የሀገሪቱ ክልሎች በተደረገ ዳሰሳ ከተመዘገቡ የፅንስ ማቋረጥ ድርጊቶች 58 በመቶው የተፈፀሙት ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 29 ባሉ ሴቶች ነው፡፡ ከእነኝህ ሴቶች 26 በመቶው ያልተማሩ ሲሆኑ 27 በመቶው የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ከእነኝህ ሴቶች 87 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ስለወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ቢያውቁም ለአንድ ጊዜም ቢሆን ተጠቅመው የሚያውቁት ግማሹ ብቻ ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት የወሊድ መከላከያ ዘዴ ተጠቅሞ አለማወቅ ከሚፈጠሩ እርግዝናዎች 78 በመቶው ምክንያት ነው፡፡

ሀገራችን በዓለም ፈጣን የህዝብ ቁጥር ዕድገት ካላቸው ጥቂት ሀገሮች አንዷ ብትሆንም የወሊድ መቆጣጠሪያ አቅርቦት አጠቃላይ ሽፋን አሁንም ከ1ዐ በመቶ በታች ነው፡፡ ከሴቶች ጤና ጋር ተያይዞ በተለይ በገጠር ሴቶች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው የሥነ ተዋልዶ ጤና ጉዳይ በመሆኑ ነው ይህንን ያህል መረጃዎችን ማጣቀሳችን፡፡ የገጠር ሴቶች ጤና ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ የሚያሻው መሆኑንም ለመጠቆም ጭምር፡፡

የህብረተሰቡ ጤና ሲቃወስ ቀዳሚ ተጐጂዎች ሴቶች መሆናቸው ስለሚታወቅ ብቻ ሳይሆን የጤና አገልግሎት ሽፋን ባለመዳረሱ ምክንያት በእናቶች ሞት በቀዳሚነት መሰለፋችን ትኩረት ለሴቶች ጤና እንድንል ያስገድደናል፡፡ አብዛኛው ሕዝብ በገጠር እየኖረ፣ የጤና አገልግሎት ሽፋናችን በሀገሪቱ ካለው የጤና ባለሙያ እጥረት የተነሳ አጥጋቢ ሳይሆን መቆየቱ ደግሞ ይህ ጉዳይ መነሳት እንዳለበት ያሳያል፡፡

መንግሥት በሚከተለው በሽታን የመከላከል ፖሊሲ መሠረታዊ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶች አቅርቦትን ለማሻሻል ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በተለይ ከሴቶች ጋር በቀጥታ የሚያያዙት የእናቶችና የህፃናት ጤና ጉዳዮች አሁንም የበለጠ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ከዚህ ጋር አብረው የሚመጡት የቤተሰብ ምጣኔ፣ የክትባት፣ የወጣቶች ሥነ ተዋልዶ ጤናም የህብረተሰቡን ብሎም የሴቶችን የአኗኗር ሁኔታ የተሻለ ለማድረግ ወሳኝ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ሽፋን ከታዳጊ ሀገሮች ጋር እንኳን ሲነፃፀር በጣም አናሳ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ፅንስና ማህፀን ሀኪሞች ማህበር በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት ይጠቁማል፡፡

የዚህ ሽፋን አናሳ መሆን የሚባባስበት አንዱ ምክንያት ደግሞ ከፍተኛ ዓመታዊ የህዝብ ቁጥር ዕድገት /2.7 ሚሊዮን በየዓመቱ/ መኖሩ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የጤና አገልግሎቶች በጣም ውሱንና በከተማ አካባቢ ብቻ ተከማችተው የሚገኙ ናቸው፡፡ 85 በመቶ ይሆናል የምንለው የገጠሩ ህዝብም የዘመናዊ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚ አይደለም፡፡ የሀገሪቱ ታሪክም ከአጠቃላይ ህዝቡ ፍላጐት ጋር የተመጣጠነ አገልግሎት ለመስጠት የቻለችበት ጊዜ እንደሌለ ያሳያል፡፡ የገጠር ነዋሪዎች በጣም አስፈላጊ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶችን ሳይቀር ማግኘት አለመቻላቸውን ከላይ የተጠቀሰው ጥናት አመልክቷል፡፡ በዚህ ረገድ በተለይ ከሥነ ተዋልዶ ጤና ጋር የተያያዙና እንደ ወሊድ ያሉ አጣዳፊ ችግሮች የሚመለከቷቸው ሴቶች የዚህ ችግር ተጠቂ መሆናቸው እሙን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬም በእናቶች ሞት ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገሮች በመሪነት ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ከ1ዐዐ ሺህ ወሊዶች 673 እናቶች ይሞታሉ፡፡

እነኝህና ሌሎች ምክንያቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በገጠር ያለውን የጤና አገልግሎት ፍላጐት ለማሟላት የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ለመጀመርና ከዚህ በፊት የነበሩትን የጤና ፖሊሲዎች እንዲመረምር አድርጐታል፡፡ የጤና ኤክስቴሽን ኘሮግራም መጀመር የገጠር ሴቶች ፈተና የሆነውን የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃና አገልግሎት አቅርቦት አለመኖር ችግር ለመፍታት ተስፋ ሊጣልበት የሚችል አንድ ክስተት ነው፡፡

ጥናቱ እንደሚለው በገጠር የሚኖሩ የኀብረተሰብ ክፍሎች የማፈልጓቸውን የጤና አገልግሎት ዘርፎች የሚጠየቁበት አሠራር ያልነበረ በመሆኑም የሚከናወኑት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የህብረተሰቡን ፍላጐት ያልያዙ አልያም ከፍላጐቱ ጋር የማይመጣጠኑ ነበሩ፡፡

የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ዓላማ በመከላከል ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎት ማስፋፋት፣ ዘላቂ የመከላከል ሂደቶችን ማበረታታትና ስለጤና ያለውን አጠቃላይ ግንዛቤ በመለወጥ ጤናማ አካባቢን መፍጠር ናቸው፡፡

ከኘሮግራሙ ዝርዝር አላማዎች አንዱ ደግሞ ለሴቶች /ለእናቶች ስለቤተሰብ ጤና እንክብካቤ እንዲሁም ቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት መሠረታዊ መረጃዎችን መስጠት ነው፡፡ ህፃናትን ለሞት የሚዳርጉና በመከላከል ብቻ ሊወገዱ የሚችሉ በሽታዎችን በተመለከተም በመውለድ ክልል ላሉ እናቶች መረጃ ይሰጣል፡፡ ስለ ስነ ተዋልዶ ጤና፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች፣ ፅንስ ማቋረጥ፣ ያልተፈለገ እርግዝናና ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በተመለከተም በተለይ ወጣት ሴቶችን ያሳውቃሉ፡፡

መንግሥት እስካሁን 17..500 የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ሠራተኞች አሰልጥኖ በማስመረቅ 9 ሺህ የሚሆኑትን በጤና ጣቢያዎች /በመንደሮች/ አሠማርቷል፡፡ ይህም እስከ 2ዐዐ8 ለማሰልጠን ካቀደው 60 በመቶ ያህሉ ነወ፡፡

የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራሙ ተግባራዊ እንዲሆን በአግባቡ የሠለጠኑ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ያስፈልጉታል፡፡ እነኝህ ሠራተኞች በየመንደሩ ያሉትን ያልሰለጠኑ አዋላጆች በመተካት አዲስ አገልግሎት የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡ የመሠረተ ልማት መሟላት ሌላው ለኘሮግራሙ መሳካት አንዱ ሲሆን የጤና ማዕከላትን መገንባትና ቁሳቁስ ማሟላት የግድ ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ኘሮግራሙ በሁሉም ደረጃዎች ብቃት ያለው አስተዳደር ያስፈልገዋል፡፡ በገጠር የጤና አገልግሎት መስፋፋት የሚጠቅመው ሴቶችን በመሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም መስፋፋት ጠቀሜታው ለሴቶች ነው፡፡

በቤተልሔም ነጋሽ

 
< Prev   Next >