| ዲያስፖራዎችን በማሳተፍ የኤምባሲዎች ሚና |
|
|
| Sunday, 09 March 2008 | |
|
ለአፍሪካ እድገት የአፍሪካ መንግሥታት በውጭ አገር የሚገኙ ዲያስፖራዎቻቸው ተሳትፎ ላይ ትኩረት እያደረጉ እንደ መሆናቸው የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎችን ተሳትፎ ለማሳደግም ኤንባሲዎች ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
በተለያዩ አለማት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ለትውልድ አገራቸው እድገት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ በተለያዩ ደረጃዎች ድጋፍ ሰጪ ፖሊሲዎች ወጥተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ዲያስፖራዎቻቸውን በምን መንገድ ለመሳብ እንደሚችሉ ጥያቄ ሆኖባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የአፍሪካ መንግሥታት ዲያስፖራዎቻቸውን ለመሳብ በሚነድፏቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እርስ በርስ ሊማማሩ ይገባል፡፡ እያንዳንዳቸው የአፍሪካ አገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች የተለያዩ ቢሆንም በተወሰነ መልኩ ሊጋሯቸው የሚችሉ አካሄዶች ይኖራሉ፡፡ ከሁሉም በላይ በውጭ ካሉ ዲያስፖራዎቻቸው ጋር ጠንካራ የሆነ ግንኙነት መመስረት ሁሉም የአፍሪካ አገሮች የሚጋሩት ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ዲያስፖራዎች በአገራቸው የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ እንዳይሆኑ እንቅፋት የሚሆነው በእንደዚህ ያለ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ እንደሚችሉ የሚጠቁም መረጃ ባለመኖሩ ነው፡፡ በአገራቸው ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና ለዲያስፖራው ስለሚደረገው የማበረታቻ ድጋፍ መረጃ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ቢመቻች ወደ የአገራቸው የመመለስና ኢንቨስት የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ የዲያስፖራዎችን መረጃ የማግኘት ችግር ለመቅረፍ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች በተለያየ አገር ለሚገኙ ዜጎቻቸው መረጃ ለመስጠት ኤምባሲዎቻቸውን መጠቀም ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ የአፍሪካ አገራት ኤምባሲዎችና ማህበረሰብ ድርጅቶች የአፍሪካ መንግሥታት ከዲያስፖዎቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር አይነተኛ መፍትሄ ሆነዋል፡፡ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ አገራት የማህበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ከዜጎቻቸው ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ረድተዋል፡፡ በዚህም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በአገራቸው የልማት እንቅስቃሴ ተሳታፊ ለመሆን ችለዋል፡፡ ዲያስፖራዎች በአገር ልማት የተሻለ ነገር እንዲያበረክቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ካለው ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የተለያዩ እቅዶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የልማት እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ በአገር ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉት ያሉትን የተመቻቹ ሁኔታዎችን ማሳወቅና በተለያየ መንገድ በአገሪቱ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ለመሳተፍ ለሚፈልጉት ያሉት ማበረታቻዎች ድጋፎች ማሳወቅን ያካትታል፡፡ ቢሮው ቀጣይነት ባለው መልኩ የዲያስፖራውን ጥያቄ በማዳመጥ በአገራቸው ልማት የተሻለ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበትን መንገድ መፍጠር አለበት፡፡ ባለፈው ጊዜ በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ለቅድመ ጥናት የሚያገለግሉ መረጃዎችን በመጠየቅ ለኤምባሲው አቅርቧል፡፡ የጥያቄዎቹ ምላሽ በአገር ልማት ላይ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት አስፈላጊ ነው፡፡ በካናዳ ቶርንቶና ኦቶዋ ግዛቶች ለዲያስፖራ አባላት መረጃ የሚሰጡ በርካታ ስብሰባዎች ተካሄደዋል፡፡ ስብሰባዎቹ የዲያስፖራ አባላት፣ ድርጅቶች፣ ማህበረሰብ መሪዎችና የኤምባሲ ሰራተኞችና አምባሳደሮች ተከፋይ ነበሩ፡፡ ኤምባሲው ተመሳሳይ ስብሰባዎችን ዲያስፖራውና በርካታ የአካባቢ ባለሥልጣናትን ተካፋይ በማድረግ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በተወሰኑ አካባቢዎች ያሉትን የልማት ፍላጎቶችና የኢንቨስትመንት አማራጮችን አሳይተዋል፡፡ በስብሰባዎቹ ከሐረሪ፣ አፋር፣ ሶማሌና ኦሮሚያ አካባቢ ተወካዮች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ መልክ ዲያስፖራዎችን ተሳታፊ የሚያደርጉ አቅጣጫዎችን በማስተዋወቅ በኩል የመንግሥት ድረገፆች፣ ኤምባሲዎች መረጃዎችን በኢንተርኔት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባል፡፡ በመረጃዎቹ ዲያስፖራዎችን የሚመለከቱ ጽሁፎች፣ ከዲያስፖራው ጉዳይ ጋር የተያያዙ የመንግሥት ቢሮዎች መረጃ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፍላጎትን ማካተት የተሻለ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አገልግሎት ለመስጠት ከሚገጥማቸው ችግሮች የገንዘብና የሰው ሃይል እጥረት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ካናዳ ሰፊና ከዲያስፖራዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎች የሚካሄድባት ሃገር ናት፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴም ሃገሪቱ ውስጥ ከፍ ያለ ገንዘብ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም ካናዳ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች በተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ለማድረግ የበጀት እጥረት ያጋጥማቸዋል፡፡ የሰው ሃይል እጥረትም አንዱ ችግር ነው፡፡ ሌላው ችግር ደግሞ ዲያስፖራው በአመለካከት አንድ አለመሆኑ ነው፡፡ በፖለቲካ የተለያየ አመለካከት የሚያራምዱና እርስ በርሳቸው የተበታተኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም ኤምባሲው የሚያደርጋቸው የስራ ክንውኖች አይዋጥላቸውም፡፡ የሚፀፈመው ስራ ሁሉ ከመንግሥት የፖለቲካ ጥቅም አኳያ ብቻ እንደሚደረግ ይጠረጥራሉ፡፡ ኤምባሲው በበኩሉ ምንም አይነት አመለካከት ያለው ዲያስፖራ ቢሆን ኤምባሲው በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እንዲካፈሉና በስብሰባዎች ላይ በመገኘት መረጃዎችን እንዲያገኙ ይመክራል፡፡ ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ይህንን የሚፈፅሙ ሰዎች በቀሪው ዲያስፖራ ዘንድ ማህበራዊ መገለልና የመንግሥት ደጋፊ ነው ተብሎ የመፈረጅ አደጋ ይገጥማቸዋል፡፡ በኤምባሲዎችና በዲያስፖራ ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት አስቸጋሪና ትዕግስት የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር አምባሳደሮች የማህበረሰብ ድርጅቶችን ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ ለሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ኤምባሲዎች ክፍት ሊሆኑና በጋራ ሊሰሩ ይገባል፡፡ የተለያየ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በአገሪቷ እድገት የበኩላቸውን ማበርከት የሚጋሩት ሊሆን ይገባል፡፡ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ኤምባሲዎች በዚህ ረገድ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩበት ሁኔታም አለ፡፡ የዚህ አይነቱን የኤምባሲዎች እንቅስቃሴ መንግስት የዲያስፖራዎችን ሁኔታ ለመቆጣጠር እንደቀየሰው መንገድ የሚመለከቱበት ጊዜው አለ፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |