| የከበደ ሚካኤል ግጥም በሥዕል ቀረበ |
|
|
| Sunday, 09 March 2008 | |
|
የደራሲ ከበደ ሚካኤል አንዱ የግጥም ሥራ ለልጆች በሚመች መልኩ በሥዕል ተቀናጅቶ ለሕትመት በቃ፡፡
“የዕንቁላሉ ተረት በግጥምና በሥዕል” በሚል ርእስ የቀረበው መጽሐፍ ቀደም ሲል “ብርሃነ ኅሊና” ከተሰኘው የግጥም መድበል ደራሲው “ምስጢርና ወሬ” በሚል ርእስ የጻፉት ነው፡፡ በዋሸራ አሳታሚዎች በቅርቡ ስለታተመው መጽሐፍ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ኃይሉ ሃብቱ እንደገለጹት መጽሐፉ የአሁን መልኩን ከመያዙ በፊት ቀድሞ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተሰራጭቶ የአማርኛ ንባብ መልመጃ እንደነበረና ብዙ የዘመኑ ተማሪዎች ሊገለገሉበት፣ እውቀትን ሊገበዩበት፣ የሥነ ምግባር እሴቶችን ሊቀስሙበት እንዲሁም ግጥሞቹን በቃላቸው አጥንተው ሊዝናኑበት በቅተዋል፡፡ በ1994 ዓ.ም. በደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ “ተረት ተረት የመሠረት” መጽሐፍ፣ “የወለደውን የማያከብር፣ የሚያከብረው ልጅ አያገኝም” የሚለውን አንዱን ተረት በሥዕል ተደግፎ በዛምራ አሳታሚ መታተሙ ይታወቃል፡፡ በሔኖክ ያሬድ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |