Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow የሕያዋን አቁዋመ ማኅበር
የሕያዋን አቁዋመ ማኅበር E-mail
Sunday, 06 January 2008
የማህበራችን አቁዋም የተሰራበት ስራት ልማዱ፣ ወጉ ሕጉ እንደ ሕይወታዊ ስራተ ማህበር ሳይሆን ሕይወት እንደሌለው የድንጋይ ካብ አንዱ ባንዱ ላይ ተደራርቦ የላይኛው የታችኛውን ተጭኖ የታችኛው የላይኛውን ተሸክሞ እንዲኖር ሆኖ የተሰራ በመሆኑ ከጊዜ ብዛት የታችኛው ማፈንገጡ ስለማይቀርና ይህ ሲሆን ህንጻው በሙሉ እንዳይፈርስ እንደገና ተሻሽሎ ሰውን ከድንጋይ በተሻለ መልክ የሚያሳይ የህያዋን አቁዋመ ማህበር እንዲሰራ ያስፈልጋል፡፡

ገበሬ ይዘራል፣ የዘራውም ዘር አበቃቀሉን አሳምሮ ይወጣል፣ ያድጋል፣ ይለመልማል፣ ያብባል፣ ያምራል፣ ዘሪውም ከቡቃያው እስካበባው ድረስ ደስታው ካዝመራው ጋር አብሮ ያድጋል፡፡ ከዚያ ፍሬውን ለማየት በናፍቆት ሲጠባበቅ በመሀከሉ ድንገት አንድ የመርዶ ነቢይ ይመጣና ..የዘራኸው ፍሬ አያፈራም ባበባው ደርቆ፣ ገለባ ትቢያ ሆኖ ይቀራል ያንተም ደስታ ከቡቃያ እስካበባው በማየት ብቻ ይወሰናል.. ብሎ ቢያረዳው ያ ገበሬ ምን ያክል ይሰቀቅ? ምን ያህል አንጀቱ ይቆረጥ ይሆን?

/ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ፍቅር እስከ መቃብር፣ 1958/

የሸረሪት ፈትል

የሰው ልጅ የሽመናን ጥበብ ከሸረሪት እንደተማረ ይነገራል፡፡ ሆኖም ሰውና ሸረሪት ተጣጥመው የኖሩበት ጊዜ እስካሁን እምብዛም አልታየም፡፡ ሸረሪትም ይህን ሁሉ የሰው ልጅ በትር ችላና ከዘመን ዘመን ትውልዷን በየሥርቻው ስትራባ ኖራ ዛሬ ደግሞ የሰውን ልጅ እንክብካቤ ለማግኘት ታድላለች፡፡

የሸረሪትን ጥቅም አበክረው የተረዱት ቻይናውያን ገበሬዎች ናቸው፡፡ በቻይና ሰፋፊ የሩዝና የጥጥ እርሻዎች ውስጥ አነስተኛ የሳር ክምሮች በብዛት ይታያሉ፡፡ በእነዚህ የሳር ጠለላዎች ተገንነት በሺህ የሚቆጠሩ ሸረሪቶች ተራብተው በየማሳው ውስጥ ለአደን ተግባር ይንከላወሳሉ፡፡ እነዚህ ሸረሪቶች አድነው ለምግባቸው የሚያውሏቸው ፀረ ሰብል ተባዮችን ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ዘዴ የቻይና ገበሬዎች ከፀረ ተባይ መድሃኒት ይልቅ የሸረሪት ድጋፍ የተሻለ ምርት እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡

/አባይነህ አበራ፣ ካዘና፣ 1982/

ሁለቱም እንዳይቀየሙ

በአብዮት ፍንዳታ ማግሥት ሁለት ድርጅቶች ላብ አደሩ፣ ወዝ አደሩ ያቸንፋል ያሸንፋል እየተባባሉ በጥይት በሚጋደሉበት ወቅት አንድ ዘፈን በሬዲዮ ይቀርባል፡፡ ወዝአደሩ ያሸንፋል ላብ አደሩ ያቸንፋል፣ አፈር ገፊው ያቸንፋል፣ አርሶ አደሩ ያሸንፋል... የሚለው የሰማ ምን ለማለት ነው ብሎ ቢጠይቅ፣ ሁለቱም እንዳይቀየሙ ነው የሚል መልስ አገኘ፡፡

ወርቅ ይተከልለታል

በገጠር ያደግሁ ነኝ ባይ አንድ ሰው ለገና በዓል ጓደኛውን በግ ሊያጋዛ ወደ ሾላ  ሄደ፡፡ በብዙ በጎች ላይ አቃቂር እያወጣ ሲያማርጥ ቆየ፡፡ ኋላም የአንዱን በግ አፍ አላቆ አየና ..ይኸስ የሸረፈ ነው.... ቢል፣ በትችቱ ያልተደሰተው በግ ሻጭ ..ይተውት ጌታው ወርቅ ይተከልለታል.. ብሎ መለሰለት፡፡

ማየቴ


ማየቴ ማየት እንዲሆንልህ እንዴት ብዬ ልንገርህ? እንዴትስ ብዬ ላስረዳህ? የባሕሩ አንቀሳቀስ ደስታዎች በሰውነትህ እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋቸዋል፡፡ የማዕበሉ አዘላለል እረድፍ አዎበጀ ሲገነፍልና ፈረሰኛውን ፈረሰኛ የተከታተለው ባሕሩን እየለቀቀ በተፈጥሮ ሳይሆነ በገዛ ኃይሉ ባበቀለው ክንፍ አግድም ሲንቻረር የእግዚአብሄር መንፈስ በውሃዎች ላይ ይሰፍ ነበር የተባለውን ቃለ ኦሪት ሲተረጎም ታየዋለህ፡፡ ማዕበሉ እንደ ሰጎን አንገቱን አስግጎ በኋላ እግሩ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንደገና በፊት እግሩ ደፋ ሲል በስግደት ላይ የሚገኝ ባህታዊ ይመስላል፡፡

/ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ፣ አግአዚ፣ 1958/

የታሪክ ነገር

ዘነበ የአጼ ቴዎድሮስን ታሪክ ጻፈ፡፡ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የአጼ ዮሐንስንና የአጼ ምኒልክን ዘመነ መዋዕል ባጭሩ ተርከው ነበር፡፡ ጸሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ የአጸ ምኒልክን ዘመነ መንግሥት ታሪክ አቅርበዋል፡፡ የብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ..ዝክረ ነገርም.. ከታሪክ ጽሁፎች ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ በአቀራረባቸው ተመሣሣይነት አላቸው፡፡ ደራሲዎቹ ለቤተ መንግሥት አቅራብ ናቸው፡፡ ታሪካቸውም በአብዛኛው በቤተ መንግሥቱና በንጉሠ ነገሥታቱ ዙሪያ የተገነባ ነው፡፡ ስለዚህም አንዳንድ የታሪክ ሊቃውንት ..የኢትዮጵያ ታሪክ በቁመትና /ማለት ከላይ ወደታች/ በጥብቅ እንጅ በስፋት እስከ አሁን አልተጻፈም.. ይላሉ፡፡ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝም ይህንን ይዞታ ነቅፈዋል፡፡ አስተያየቱ እውነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ደግሞም ምክንያት አለው፡፡

ሀገሬው የሚቀበለው ወይም እንዲቀበለው የሚደረገው ማዕረጉ፣ ሥርዓቱ ባሕሉ የሚመነጨው ከቤተመንግሥት ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ወግ ወደፊት ጦረኛና ጦር አዝማች አስተዳዳሪ፣ ዳኛ የሚሆነው ..የጨዋ ልጅ.. በቤተመንግሥት ወግና ሥርዓት ተቃኝቶ ያድጋል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ የጦር መሪ፣ የሀገር መሪ የመንግሥት መሪ፣ አስተዳዳሪ የበላይ ጠባቂ ነው፡፡ ስለዚህ የሚሰራው ሥራ ሁሉ በደግም ሆነ በክፉ የኢትዮጵያን ታሪክ የኢትዮጵያን ሕዝብ አኗኗር የሚነካ ሊሆን መቻሉ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ነው የቤተ መንግሥቱና የነገሥታቱ ታሪክ የኢትዮጵያ ታሪክ ሆኖ የኖረው፡፡

/ብርሃኑ ዘርይሁን፣ መነን መጽሔት፣ 1962/

አባቶቻችን

አባቶቻችን በሰማይ አልበረሩም፣ በምድር አልተሽከረከሩም፡፡ ብዙ አገር አላቋረጡም፡፡ ብዙ መጽሀፍ አላነበቡም፡፡ መሬት ባለመልቀቃቸው ግን መሬታቸውን አስከብረዋል፡፡ ቀስ እያሉ በመሄዳቸው ብዙ ተመልክተዋል፡፡ ወረቀት አይሁን እንጅ የተፈጥሮን ገፅ አገላብጠዋል፡፡ ብዙም አይራቁ እንጂ የሚሻላቸውን አገር መርጠዋል፡፡ ለምርጫቸውም መስዋዕት ሲሆኑ ኖረዋል፡፡

/ዳኛቸው ወርቁ፣ የጽሁፍ ጥበብ መመሪያ፣ 1988/

ገራገር

በፖሊስ ቲሸርት አፍንጫዋን ያፀዳች ክስ ተመሰረተባት

በፖሊስ መኮንኑ ቲሸርት አፍንጫዋን የጠረገችው አሜሪካዊት ክስ ተመሰረተባት፡፡ በምዕራብ ቨርጂኒያ በቻርሌስቶን አቅራቢያ በምትገኘው ዱንባር አካባቢ ፖሊሱ ከሕግ ውጪ የተፈጠረውን ቀላል ግጭት ለማረጋጋት በሄደበት አጋጣሚ ሲሆን ወ/ሮዋ ድርጊቱን የፈፀመችው የተጣላችውን ሰው እንዳትመታው እንቅፋት ስለሆነባት እንደሆነ ተገል..ል፡፡

የ36 ዓመቷ ጓርጂያ ኔውማን ከእሷ ጋር ግጭት የፈጠረውን ሰው በጥፊ ለመማታት ሙከራ ስታደርግ ሰውየው መንከሷን ፊቱን መሞነጫጨሯ ተገል..ል፡፡

በዚህ ድርጊቷ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ የተጓዘችው ወ/ሮ ነገሩን ለማስረዳት በማስመሰል የፖሊስ መኮንኑን ትከሻ በመደገፍ በቲሸርቱ አፍንጫዋን በመጥረጓ ድጋሚ ክስ ተመስርቶባታል፡፡

ታራሚዎች የሌሊት ልብሳቸው እንዲቀየር ጠየቁ

በጃፓን እስር ቤት ያሉ እስረኞች ስታይል የሌለውን የሌሊት ልብሳቸውን ጠልተዋል፡፡ የሚመገቡት ምግብም አቅም ስላሳጣቸው እንዲቀየርላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የጎን መስመር ያለው ግራጫ ፒጃማቸው ፋሽን አልባ በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እስረኞች ቀለሙ ግራጫ በመሆኑ፣ 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ዲዛይኑ አስቀያሚ በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ይፈልጋሉ፡፡

የአገሪቱ የክስ አይነቶች በመብዛታቸው የእስረኞች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ መምጣቱ ተገል..ል፡፡

የጃፓን አለም አቀፍ የወንጀለኞች ምህረት አድራጊ ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ማኮቶ ቴራናካ እስር ቤቶች ከማህበረሰቡ የተከለሉ በመሆናቸው እስረኞች ሰብዓዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው አመልክተዋል፡፡ ለጠየቁት ጥያቄ መልስ የሚሰጥና በእስር ቤቶች ያሉትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለመቀየር የሚያስችል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሟቹ ስጦታ

በአሜሪካ ኦሪጎን ውስጥ ከሞተ ሁለት ወራት የሆነው ሰው ለ34 ሰዎች የገና ካርዶች መላኩ ተገለፀ፡፡ በሚ/ር ቼት ፊች የእጅ ጽሁፍና ፊርማ የተላኩት ካርዶች ከእግዚአብሄር የተላኩ መሆናቸውና በካርዱ ላይም በ1995 ከሞተችው ሚስቱ ጋር ሲደንስ የሚያሳይ ምስል እንዳለበት ተገል..ል፡፡

የሚስተር ፊች ጓደኞችና ዘመድ ወዳጆች በድርጊቱ የተገረሙ ሲሆን፣ አሌክሳንደር የተባለችው የፊች ሴት ልጅ በካርዱ የተሰራውን ተንኮል አስቂኝና አስደሳች ሆኖ እንዳገኘችው ተናግራለች፡፡

በካርዱ የመጨረሻ መልዕክት ..መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ ባላሰባችሁት በቅርብ ጊዜ እታያችኋለሁ.. ብሏል፡፡ ሚ/ር ፊች ይህን ተንኮል ፀጉሩን ታስተካክለት ከነበረችው ደንበኛው ፒቲዲን ጋር በመተባበር ያደረገው መሆኑም ተገል..ል፡፡

ለ11 ወራት የቆየ ስርቅታ

አንድ ሰው ለ11 ወራት ያህል ያለማቋረጥ በስርቅታ መሰቃየቱ ተገለፀ፡፡ ክሪስ ሰንድኮ የተባለው የ24 ዓመት ወጣት ካለፈው የፈረንጆች መጋቢት ወር ጀምሮ ለሚያሰቃየው ስርቅታ፣ የአዕምሮ፣ የሆድ፣ የደረት አጠቃላይ ምርመራ ያደረገ ቢሆንም ለስቅታው ምክንያት የሆነው ችግር አልታወቀም፡፡

ዶክተሮች በህክምና ችግሩን ማግኘት ስላልቻሉ ስርቅታን ልምድ ከማድረግ የመጣ ሊሆን ይችላል በሚል ህመምተኛውን ወደ ሥነ አዕምሮ ባለሙያዎች ልከውታል፡፡

ክሪስ ለችግሩ እርዳታና መድሃኒት ለማግኘት የሚያስችሉ ሰዎችን ፍለጋ ማይስፔስ በተሰኘ ድረገፅ ላይ ብሎግ መክፈቱም ተገል..ል፡፡

በአለማችን በስርቅታ ሪከርዱን የያዘው በአየዋ አንቶን አካባቢ የነበረው ቻርለስ አስቦርን ሲሆን ለ68 ዓመታት ያህል ተሰቃይቷል፡፡

እግዚኦ

የመረጡትን መርጦ፣
የረሱትን ረስቶ፣
     ትቶ፣
ጠላን ያሉትን ጠልቶ፣
ሆን ያሉትን ሆኖ
   መስሎ፣
    ተመስሎ፣
አለሁ ብሎ፣
    ተቀብሎ፣
እርሱ ተበድሎ
ለመኖር ሲል ግን አታሎ፣
አታሎ ይባል ይሆን? ተታሎ?
ብቻ ለመኖር ሲል መስሎ
 እግዚኦ..
ህይወት ለምን እንዲህ ጣፈጠ?
   መኖር ምነው ዋጋው በዛ?
የልብን ውሳኔ እስኪጥስ
   ህልውናን እስኪገዛ፡፡

/አምሀ አስፋው፣ ይላላ ደነቦ፣ 1995/

 
< Prev