| ለፖስታ ድርጅት ሰራተኞች... |
|
|
| Wednesday, 12 March 2008 | |
|
ለፖስታ ድርጅት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ተደረገ
ድርጅቱ ለማይሰሩ ሰራተኞች በወር ከ130ሺ ብር በላይ ይከፍላል የኢትዮጵያ የፖስታ ድርጅት የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ለድርጅቱ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ማስተካከያ አደረገ፡፡ ከድርጅቱ የተገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ወርሃዊ ጭማሪው የኑሮ ውድነትን በተመለከተ የተደረገ የደመወዝ ማሻሻያ ነው፡፡ በማሻሻያው መሠረት የወር ደመወዛቸው ከሦስት መቶ ሃምሳ በታች ለሆኑ ሠራተኞች የአምስት እርከን ጭማሪ ሲደረግ፤ ወርሃዊ ደመወዛቸው ከሦስት መቶ ሃምሳ በላይ ለሆኑ ሠራተኞች የሦስት እርከን ጭማሪ ተደርጓል፡፡ የጭማሪው ትግበራ ከትላንትና ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የጭማሪው እሳቤ ካለፈው ዓመት የሐምሌ ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ ነው፡፡ በድርጅቱ ሠራተኞች ጠያቂነት የሠራተኛ ማኅበሩና የድርጅቱ የአመራር አካላት ባደረጉት ስምምነት መሠረት የደመወዝ ማስተካከያው መካሄዱ ታውቋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪው በአገር አቀፍ ደረጃ ለመንግሥት ሠራተኞች የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪ መሰረት በማድረግ የተካሄደ ጭማሪ እንደሆነ ጭማሪ የተደረላቸው ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና የፖስታ ድርጅት ከሥራ ላገዳቸው አንድ መቶ አስራ ስምንት ሰራተኞች በየወሩ ከአንድ መቶ ሰላሳ ሺ ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ የደመወዝ ጭማሪው የታገዱ ሰራተኞችንም እንደሚያካትት ታውቋል፡፡ የታገዱ ሠራተኞች ከድርጅቱ ማግኘት የሚገባቸው የቦነስ፣ የቅምሻ፣ እንዲሁም ዓመታዊና የኑሮ ውድነት ማስተካከያ ጭማሪዎች የሚያገኙ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንዳንድ የታገዱ ሠራተኞች ድርጅቱ ከሥራ ለታገዱ ሠራተኞች ከፍተኛ ወጪ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ "ከአግባብ ውጪ ብክነት እየተካሄደ ነው" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በዚህም ድርጅቱ ወደ ሥራ ገበታቸው ቢመልሳቸው ለድርጅቱም ለአገሪቱም ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |