| በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች... |
|
|
| Wednesday, 12 March 2008 | |
|
በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል
በኢትዮጵያ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚስፈልግ የአሜሪካ የጥናት ቡድን ትላንት ማስታወቁን ሮይተርስ ዘገበ፡፡ በዘገባው መሰረት በኢትዮጵያ የአርብቶ አደሩ አካባቢ ለሚገኙ ዘጠኝ ሚሊዮን ነዋሪዎች የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋል፡፡ ከነዚሁ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ ስምንት ሚሊዮኑ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በዘንድሮው የምርት ዘመን ከአስራ ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ቶን በላይ ምርት እንደሚገኝ የምርት ትንበያ ጥናትን በመጥቀስ አስታውቋል፡፡ የአሜሪካ የጥናት ቡድን በሶማሊያ፣ በኦሮሚያና በጋምቤላ ክልሎች የሚገኙ የአርብቶ አደሮች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በቦረናና በሶማሊያ አካባቢ የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአካባቢው በተከሰተው የድርቅ ችግር እንደተጠቁ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |