Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ዶ/ር አሸብር ተዘረፉ
ዶ/ር አሸብር ተዘረፉ Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
Image
ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህጋዊ ኘሬዚዳንት እንደሆኑ የሚገልፁት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ በድምሩ 51 ሺህ 600 ብር መዘረፋቸውን አስታወቁ፡፡ ባንኩ ዝርዝር መግለጫ አልሰጥም ብሏል፡፡
 
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ በቼክ ቁጥር እ.ኤአ CD4886661 በ10/03/08 27,500 ብር፣ በቼክ ቁጥር CD4886662 እ.ኤ.አ በ05/03/08 28,100 ብር በተመሳሳይ ቼክና ፊርማ መዘረፋቸውን ዶክተር አሸብር ገልፀዋል፡፡

"የተዘረፍኩበት ቼክ ሳይቆረጥ በእጄ ይገኛል፡፡ እንዴት ተመሳሳይ ቼክ ተሰራ? ማን ሰራው?" የሚለው ጥያቄ መልስ እስኪያገኝ ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሚሆንባቸው ዶክተር አሸብር ተናግረዋል፡፡

ባንኩ እ.ኤ.አ በ10/03/08 በድጋሚ 27"500 ብር ከሰጠ በ31 በበነጋታው ቼክ መስጠታቸውን መጠየቁን፣ እሳቸውም ምንም ዓይነት ቼክ አለመቁረጣቸውን ከገለፁ በኋላ መዘረፋቸውን እንዳወቁ ዶክተሩ አስታውቀዋል፡፡ "ያለምንም ወለድ ንግድ ባንክ የማስቀምጠው ለአስተማማኝነቱ ብዬ ነው" በማለት ባንኩን ያማረሩት ዶክተር አሸብር አጠቃላይ የባንክ ዝርዝር ሂሳብ መግለጫ ሲሰራ የተዘረፉትን ብር መጠን እንደሚያውቁት አመልክተዋል፡፡

የባንኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ደመቀ ከዶክተር አሸብር ሂሳብ ገንዘብ መዘረፉን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ በምርመራ ላይ ስለሆነ ባንኩ ዝርዝር መግለጫ ለመስጠት እንደሚቸገር ተናግረዋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >