| በነዳጅ ምርቶች ላይ 3ዐ በመቶ... |
|
|
| Wednesday, 12 March 2008 | |
|
በነዳጅ ምርቶች ላይ 3ዐ በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ሊጣል ነው
ጭማሪው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብሰው ተሠግቷል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ትላንት በቀረበ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከኬሮሲን ውጪ ባሉ የነዳጅ ምርቶች ላይ የ30 በመቶ ታክስ እንዲጣል ደነገገ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁኔታው የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ ያባብሰዋል በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው ኬሮሲን (ለቤት ውስጥ ፍጆታ የሚውል ጋዝ) በስተቀር ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ ሱፐር ቤንዚን፣ የአውሮኘላን ነዳጅ እና ተሽከርካሪ ዘይቶች ላይ የ3ዐ በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጥላል፡፡ በተጨማሪ የአልኮል መጠጦች ላይ በአሁኑ ሰዓት ያለውን 5ዐ በመቶ ታክስ ወደ 75 በመቶ ከፍ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገ ውሀ 2ዐ በመቶ ታክስ መጣሉን ረቂቁ ያስረዳል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ለመኪና መገጣጠሚያ የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች እና የተዘጋጁ ልብሶች ከታክሱ ነፃ የተደረጉ ሲሆን የለስላሳ መጠጦች አሁን ካለበት 4ዐ በመቶ ታክስ ወደ 3ዐ በመቶ ዝቅ ተደርጓል፡፡ በነዳጅ ምርቶች ላይ ኤክሳይዝ ታክሱ የተጣለው መንግሥት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚያወጣውን ወጪ ለመከላከል ታስቦ ነው ተብሏል፡፡ የታክስ ማሻሻያው ዋንኛ ዓላማም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ኢዴአፓ መድህንን ፓርቲ ጨምሮ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በተለይ በነዳጅ ምርቶች ላይ ረቂቅ አዋጁ ያሰፈረው የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ እንዳያባብሰው እና ተደራራቢ ታክስ እንዳያስከትል ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለሚመለከተው ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል፡፡ በፍሬው አበበ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |