Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ...
ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ... Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
Imageከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የታገዱት የንግድ ድርጅቶች ይፋ ሆኑ

በወርቅ ማጭበርበር ተጠርጥረው ከተያዙት መካከል ንብረታቸውና የንግድ ቤታቸው የታገደባቸውን የፌዴራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡ ጥያቄ ቀርቦ ለጊዜው እግድ ያልፀናበት ገላን የልብስ ስፌት ፋብሪካ ብቻ ነው፡፡
 
በኮሚሽኑ ጥያቄ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ባስተላለፈው ትዕዛዝ ንግድ ቤትና መጋዘኖቻቸው የታገዱባቸው ሙደሲር መሐመድ፣ አብዲሽኩር መሀመድ፣ ሱልጣን መሀመድ ሶፋምና ሃሺም፣ አማን ሁሴን ናቸው፡፡

ንብረትነቱ የሙደሲር መሀመድ የሆነው (ሶፋም) ኢንተርፕራይዝ ኃላፊቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚል የሚታወቀው ቀድሞ ወረዳ 3 ቀበሌ 52 የሚገኝ የመኪና እቃ መለዋወጫ ሱቅ፣ በወረዳ 23 ቀበሌ 03 የሚገኝ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኝ የመኪና መለዋወጫ እቃ መጋዘን፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 12 የሚገኝ የቤት ቁጥሩ 774/ሀ/ የሆነ የተዘጋጁ ልብሶች መሸጪያ መደብር፣

ንብረትነቱ የአብዲሽኩር መሀመድ (ሶፋም) በአራዳ ክፍለ ከተማ 04/05 የቤት ቁጥር 14820 የሆነ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02/03 የቤት ቁጥር 334/01 የንግድ ቤቶች፣

ንብረትነቱ የሱልጣን መሀመድ (ሶፋም) የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 12 ቤት ቁጥር 964/5/ሩህ በሚል የሚታወቅ የተዘጋጁ ልብሶች መሸጪያ መደብር፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/19 የቤት ቁጥር 305 ዴይ ኤንድ ናይት የንግድ መደብር፣

ንብረትነቱ የሃሺም አማን ሁሴን የሆነ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02 የቤት ቁጥሩ የማይታወቅ የተዘጋጁ ልብሶች መሸጪያ መደብር፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 18 በመኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ግምጃ ቤት የተከማቹ የተለያዩ ሸቀጦች በከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታሸጉ (የእግድ ትዕዛዝ) ሰጥቷል፡፡

ንብረትነታቸው የፉዐድ የሆኑ የዋው ፋሽን የንግድ ቤቶቹ ላፓሬዚያን አጠገብና ፍሬንድ ሺፕ ሕንፃ ያሉትን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የንግድ ቤቶች ታሽገዋል፡፡

የፌዴራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የእግድ ትዕዛዝ እንዲስጥለት የጠየቀው ንብረትነቱ የአብዱል ሽኩር መሀመድ የሆነው ገላን ከተማ የሚገኘው ገላን የልብስ ስፌት ፋብሪካ ለጊዜው በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >