| በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጪ የሚወጡ... |
|
|
| Wednesday, 12 March 2008 | |
|
በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጪ የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ለአደጋ እየተጋለጡ ነው
በሕጋዊ መንገድ ሥራ ፈልጎ ወደ ውጭ መውጣት እየተቻለ በደላላዎች ተታለው በሕገወጥ መንገድ በጅቡቲ በኩል ለመውጣት የሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን ለአሰቃቂ አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸውን አምባሳደር ሸምሰዲን አህመድ አስታወቁ፡፡ አንዳንድ ሕገወጦች ለገንዘብ ሲሉ ወደ ሌሎች አገሮች ለመሸጋገር የተመቸ ሁኔታ እንዳለ በማስመሰል ዜጎችን አታለው ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ እንደሚወሰዱ፣ የሚሄዱት ወጣቶች በማያውቁት አካባቢና ውሃ በማይገኝበት በረሃ ስለሚጓዙ በድካምና በውሃ ጥም ጭምር እስከሞት እየደረሱ የአውሬ እራት እየሆኑ ነው በማለት አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡ (ኢዜአ) ሦስት ሺ 200 የጤና ሱፐርቫይዘሮች ሊሰለጥኑ ነው በመላው አገሪቱ ለጤና ኤክስቴንሺን ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ 3ሺ 200 ሱፐርቫይዘሮችን እንደሚያሰለጥን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሱፐርቫይዘሮቹ በጤና ኤክስቴንሺን አገልግሎት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ አንድ ወር ስልጠና ከተከታተሉ በኋላ በየጤና ጣቢያው ይመደባሉ፡፡ በአገሪቱ በተቋቋሙ 30ሺ የጤና ኬላዎች ውስጥ የሚሰሩ የኤክስቴንሺን ባለሙያዎችን የዕለት ተዕለት ሥራ የመከታተልና ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንደሚጣልባቸው፣ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ 700 የጤና ጣቢያዎች በአገሪቱ እንደሚገኙ፣ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተጨማሪ 500 የጤና ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገል..ል፡፡ (አዲስ ዘመን መጋቢት 2 ቀን 2000 ዓ.ም) የልማት አማካሪዎች መድረክ ተቋቋመ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በነቀምቴ ከተማና በአካባቢዋ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ልማትንና ዕድገትን ለማፋጠን የተለያዩ አካላትን ያካተተ የልማት አማካሪዎች መድረክ ተቋቋመ፡፡ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሪነት የተቋቋመው የልማት አማካሪዎች መድረክ ዩኒቨርሲቲውን ጨምሮ ከባንኮችና ፋይናንስ ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤት፣ ከግብርናና ገጠር ልማት፣ ከኢንቨስትመንት፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ፣ ከከተማ ልማት ጽሕፈት ቤት የተውጣጡ አባላትን ያካተተ ነው፡፡ (ዋኢማ) የሙስና ወንጀል የፈፀሙ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ በአሰላ ማዘጋጃ ቤት በተለያዩ ኃላፊነት ላይ በቆዩበት ወቅት የተለያዩ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ ስድስት ሠራተኞች ላይ ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት መወሰኑን በአሰላ ዞን ከፍተና ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የበየነው በሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት የያዙትን ኃላፊነት መከታ በማድረግ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል፣ ከተለያዩ ባለጉዳዮች ጉቦ በመቀበል፣ መሬት ሸንሽኖ በመስጠት በተመሰረተባቸው የሙስና ክስ ጥፋተኞች መሆናቸውን ከቀረበው ማስረጃ በመረጋገጡ ነው፡፡ (ዋኢማ) በሕገወጥ ጨው ነጋዴዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌሎችም ላይ ይቀጥላል አግባብ ባልሆነ መንገድ በምግብ ጨው ምርት ላይ የተከሰተውን ቅፅበታዊ የዋጋ ጭማሪን ለመግታት የተወሰደው እርምጃ በሌሎች ምርቶችም ላይ እንደሚቀጥል አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |