Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Monday
May 12th
Home
የወጥ አብዮት?! Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
Imageአንድ ብር ከአምሣ ሳንቲም ሲሽጥ የነበረው ጨው በሰዓታት ውስጥ በኪሎ አስር ብር መሆኑ ባለፈው ዓርብ በአዲስ አበባ ድንጋጤና ንዴት ፈጥሮ ነበር፡፡ መንግሥት ፈጣን እርምጃ በመውሰዱ ምክንያት እንደገና በሰዓታት ውስጥ ወደ ነበረበት መመለሱ ደግሞ ሕዝብ ደስ ቢለውም ከዚሁ ጋር ሌላ ስሜትና ጥያቄ ተፈጥሯል፡፡ ችግሩ የገንዘብ ስግብግብነት ወይስ የስልጣን ስግብግብነት? የሚል ጥያቄን እያስከተለ ነው፡፡
 
የብረት ዋጋ ጨመረ ሲባል በአንድ ጊዜ ኅብረተሰቡን አያናጋም፡፡ በቀጥታ ከብረት ጋር ሕዝቡ በዕለታዊ ኑሮው አይገናኝምና፡፡ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ ሲባልም በትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ሁሉም የሚነካ ቢሆንም ደረጃው ውሱንነት አለው፡፡ ወደ ምግብ  ብንገባም የጤፍ፣ የፓስታና የሞኮሮኒ ዋጋ ጨመረ ቢባልም ጤፍና ፓስታ ሳይበላ የሚኖር አለና በሕብረተሰቡ ዘንድ መናጋት ጎልቶ አይታይም፡፡ የጨውና የበርበሬ ጉዳይ ግን ምቱና የመልስ ምቱ ወዲያው ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ቋንቋ አላቸው፡፡ ጨውና በርበሬንም በተለያየ መልኩና አቀራረብ ይጠቀማሉ፡፡ ሃብታም ጨውን የዶሮ ወጥ ለመስራት ይጠቀምበት ይሆናል፡፡ ድሃው ግን በእንጀራ ላይ ነስንሶ ልጆቹን አብልቶ ወደ ትምህርት ቤት ይልካል፡፡ ሃብታም በርበሬን ለጥሬ ስጋ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ድሃው ግን እንዳለ በደረቁ እንደወጥ ተጠቅሞ ቤተሰቡን ያኖርበታል፡፡
ለዚህም ነው የበርበሬ፣ የጨው ዋጋ ናረ ሲባል ጩኸት የበረከተው፡፡ በቀጥታ ከዕለታዊ ኑሮና አመጋገብ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ሃብታሙንም ድሃውንም እንዴት ነው ነገሩ እንዲል አድርጎታል፡፡

ስግብግብ ነጋዴዎች በአንዴ አንድ ሺህ ፐርሰንት ለማትረፍ ፈልገው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጤት ነው ወይስ ጨውና በርበሬ የሕብረተሰቡ የወጥ ጉዳይ ስለሆነ ሕዝቡ የሚበላው አጥቶ ሆ ብሎ በመንግሥት ላይ እንዲነሳና መንግሥትን ገልብጦ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግ የስልጣን ጥመኞች እንቅስቃሴ?

የገንዘብ ወይስ የስልጣን ስግብግብነት ወይስ የስልጣን ጥመኝነት? በአቋራጭ ሚሊኒየር ለመሆን ወይስ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ቁጢጥ ለማለት? ወይስ የገንዘብ ስግብግብነትና የስልጣን ስግብግብነት የጋራ ግንባር?

የገንዘብ ስግብግብነት እንዳለ የተረጋገጠ ነው፡፡ ከበስተጀርባውስ የፖለቲካ ስግብግብነት የስልጣን ጥመኝነት ግፊት እያደረገ ነው ወይ ነው ጥያቄው እንጂ በአንድ ሰዓት ውስጥ በስልክም፣ በሌላም በሌላም የተሰራጨው የጨው መልዕክት በአንድ ጊዜ ከመደርደሪያ የተነሳው በነጋዴው ብቻ ሳይሆን ከበስተጀርባ ሌላ እንዳለ አሳማኝ ምልክት ነው፡፡

በሌላ የፖለቲካ ቅስቀሳ፣ ተደራጅቶና አደራጅቶ፣ በተለይም "ተቀናጅቶ" ለመታገል ወኔውም፣ አመለካከቱም አቅሙም ሲጠፋና ሕዝቡ አልገባም ሲል በወጥ በኩል ገብቶ ሕዝቡን ለማነሳሳት መሞከር ያለ ይመስላል፡፡ የወጥ አብዮት ያልነውም ለዚሁ ነው፡፡ ቀዩ አብዮትና ብርቱካናዊው አብዮት አልሳካ ሲሉ በጨውና በርበሬ በኩል የወጥ አብዮት እየተሞከረ ይመስላል፡፡ ሁሉም ልብ ሊለው ይገባል፡፡

በጨውና በበርበሬ ሕዝቡን ማስቆጣትና ማናደድ ሶስት አበይት መልዕክቶችን ያስተላልፋል፡፡ አንደኛው ለሕዝቡ፣ ሁለተኛው ለመንግሥትና ገዥ ፓርቲ፣ ሶስተኛው በጨውና በርበሬ ማለትም በወጥ በኩል ሕዝቡን ማነሳሳት ለሚሞክሩ፡፡

ለሕዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት ሁኔታውን በትኩረት እንዲከታተለው ነው፡፡ ከአንድ ብር ወደ አሥር ብር፣ ከአሥር ብር ተመልሶ ወደ አንድ ብር የሚመለስ ዋጋ ምክንያቱ እጥረት አልነበረም ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ሸማቹ ጠንካራ አቋምና ለመብቱ መከራከር አለበት፡፡ የሸማቾች ማኅበርን እየፈጠረ መቆጣጠርና መከላከል አለበት፡፡ በዚህና በዚህ ሕዝቡን መሳሪያ አድርጎ ሊያነሳሳ ለሚፈልገውም ቀይ መብራት ማሳየት ያስፈልጋል፡፡ ሕዝብ የስግብግቦች መሣሪያ እንደማይሆን በግልፅ ሊያሳይ ይገባል፡፡ ሕዝብን መናቅ የትም እንደማያደርስ ሕዝብ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡

ለመንግሥት የሚተላለፈው መልዕክትም ግልፅ ነው፡፡ ማንም ስግብግብ እየመጣ በሕዝብ ላይ ሲቀልድ መንግሥት ሊያድነኝ ይችላል ወይስ አይችልም? የሚል ጥያቄ በሕዝብ ዘንድ እየተነሳ ስለሆነ መንግሥትም ገዢው ፓርቲም ማገናዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨው ዋጋ ሲጨምር መንግሥት ያስተካክለዋል የሚል እምነት መኖር አለበት፡፡ ሕዝብ የማንም መጫዎቻ እንደማይሆን በተግባር የ"ያሳይና የ"ጠብቅ መንግሥት እንደሆነ ሊያስመሰክር ይገባል፡፡ በመግለጫ ሳይሆን በተግባር!

ለገንዘብና ለፖለቲካ ስግብግብነትም የሚያስተላልፈው መልዕክት አለ፡፡ እንዳሰቡት ሕዝብ መንግሥትን መገልበጥ ሳይሆን በስግብግብና በጥመኞች ላይ ቁጣውን ገል"ል፡፡ በወርቅ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ በጨው ጉዳይ በሕዝብ ዘንድ ያለው ስሜት ጥብቅ ነው፡፡ ሃይለኛ እርምጃ ይወሰድባቸው የሚል እንደሆነ መገንዘብ ይበጃል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥትም፣ ፖለቲከኛም፣ ነጋዴም፣ ቀይ መስመር እንዲያልፍ አይፈልግም፡፡ በዚህ አትምጣብኝ የሚል ሕዝብ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ውጊያ ነበር፡፡ የሶማሊያ ወራሪ ሲመጣ በግዛቴ ጉዳይ አትምጡብኝ ብሎ አንድ ሆኖ ተዋጋ፡፡ ደርግ አንድነት አንድነት ሲል ጥሩ አለ፡፡ ለአንድነት ብሎ እጨፈጭፋለሁ ሲል ግን በዚህ አትምጣብኝ አለ፡፡ ኢሕአዴግ ስልጣን ሲይዝ የደርግ ወታደሮችን አባሮ ነበር፡፡ የራሱን ታጋዮችም አፈናቅሎ ነበር፡፡ ቅሬታም ፈጥሮ ነበር፡፡ ሻዕቢያ ወረራ ሲያካሂድ ግን በአገር ጉዳይ አትምጡብኝ ብሎ አንድ ሆነ፡፡ ቅንጅት ሕዝብን አግኝቶ ነበር፡፡ የአዲስ አበባን ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ነበር፡፡ ቀብር አትሂዱ፣ ሠርግ አትሂዱ፣ እዚያ አትብሉ እዚያ ሻይ አትጠጡ የሚል በማህተም የተደገፈ መመሪያ ሲያወጣ ግን በዚህ አትምጣብኝ፣ በማህበራዊ ኑሮዬ ያንተ "ማንዋል" አያስፈልገኝም ነው ያለው፡፡

ስለሆነም የወጥ አብዮት ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲነሳ ያደርግልናል ብለው ተስፋ የሚያደርጉ ካሉ በዚህ አትምጡብኝ ብሎ በእነሱ ላይ ሊነሳ እንደሚችል ቢገነዘቡት ይበጃል፡፡ ስልጣን ይገባኛል የሚል ካለ ፕሮግራሙንና መርሃ ግብሩን አስተካክሎ በአደባባይ ታግሎ ይምጣ እንጂ በወጥ ቤት በኩል ሊሽሎከሎክ አይገባም፡፡ 
 
< Prev   Next >
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
Image ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ነገ ከነጋዴው...
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ነገ ከነጋዴው ኅብረተሰብ ጋር ይወያያሉ

በታምሩ ጽጌ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የንግዱን ኅብረተሰብ ነገ ግንቦት 4 ቀን 2000 ዓ.ም በጽሕፈት ቤታቸው የጉባኤ አዳራሽ ያወያያሉ፡፡
Read more...
 
Editorial
Image የተሳሳተ ጸሎት አዲስ የፖለቲካ ባህል አዳብረን ካልተጓዝን በስተቀር አሁን የያዝነው አሉታዊ ፖለቲካ ለምንመኘው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ልማታዊ ሥርዓት በእጅጉ እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ እየሆነብንም ነው፡፡
 
Politics
Image “ጦርነት የሚፈጠረው ተቃዋሚዎች...
“ጦርነት የሚፈጠረው ተቃዋሚዎች ሲሰንፉ ብቻ ነው”
አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ
የኤርትራ ፓርቲ ኮንግረስ ሊቀመንበር

በየማነ ናግሽ

አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ ይባላሉ፡፡ አባታቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ ፌዴሬሽን ወቅት በመጀመርያው የኤርትራ ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡
Briefs
ኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን...
ኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የልማት ድጋፍ ልታገኝ ነው

የእንግሊዝ የልማት መምሪያ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የድህነት ቅነሳ ኘሮግራም የሚውል የሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የልማት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
 
Business & Economy
Image ምክር ቤቱ ሕንፃውን ለመረከብ...
ምክር ቤቱ ሕንፃውን ለመረከብ የሚኒስትሮች ም/ቤትን ውሣኔ እየጠበቀ ነው

በዳዊት ታዬ

የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘውንና በስሙ ተመዝግቦ የቆየውን ባለሰባት ፎቅ ሕንፃ ለመረከብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሣኔ እየተጠበቀ መሆኑን አስታወቀ፡፡
Shemach
ከድጡ ወደ ማጡ
በናታን ዳዊት

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር ከድጡ ወደ ማጡ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉትና ከቻይና የመጡ መካከለኛ አውቶብሶች ሥራ መጀመር ትንሽ እፎይታን ይሰጣሉ ተብለው ተጠብቀው ነበር፡፡
 
Interview
Image “ዋጋው ባይረጋጋ እንኳን ነጋዴው... “ዋጋው ባይረጋጋ እንኳን ነጋዴውመረጋጋት ይኖርበታል”
አቶ ጌታቸው አየነው
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

አቶ ጌታቸው አየነው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡ ለ12 ዓመታት በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በመምህራን ማሰልጠኛ ተቋምና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ባለፉት አስር ዓመታት ደግሞ ወደ ንግድ ዓለም በመሸጋገር እየሠሩ ነው፡፡
Fermata
ጤና
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ መስጠት የተጀመረው በአፄ ልብነ ድንግል ዘመን ከፖርቱጊዝ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ጋር አብሮ በመጣውና ንጉሡን ከ1512-1527 ሲያገለግል በቆየ ሐኪም አማካኝነት ነበር፡፡ እስከ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በተመሳሳይ ሁኔታ የውጭ ሀገር ሐኪሞች እየመጡ ነገሥታቱን ሲያገለግሉ እንደነበር የተገኙት የጽሑፍ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር
(የታዳጊ አገሮች ኢኮኖሚን ማዳበር በሚመለከት በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለመሳተፍ ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ጄኔቭ እየተጓዙ ናቸው፡፡ አገራቸው ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የመጡት ኢትዮጵያዊው ዲያስፖራም ከጀርመን ማሽነሪ ለመግዛት እየተጓዙ ናቸው፡፡ እንዳጋጣሚ አውሮፕላን ውስጥ አብረው ተቀምጠዋል)
Life & Art
የጉራጌ ኪነ ሕንፃ
በምሕረት ሞገስ

የጉራጌ ባህላዊ ቤት በገጠራማው አካባቢ የሚሰራው የኅብረተሰቡን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ምሕዳራዊ ገፅታ በሚያሳይ መልኩ ነው፡፡ እንደየአካባቢው ሥነ ምሕዳራዊ ገፅታ በደጋውም ይሁን በወይናደጋው በአካባቢው የሚገኙ አስፈላጊ ተክሎች ለቤቱ ግንባታ ይውላሉ፡፡ ጽድ፣ ወይራ፣ የዘንባባ ቅጠልና ሳር መሠረታዊ የግንባታው አካሎች ሲሆኑ የእንሰት ውጤት የሆነውም ገመድም ለግንባታው ሚና አለው፡፡
 
Social
የአዲስ አበባ ውሃ!
በታደሰ ገብረማርያም

በአዲስ አበባ ከተማ በቧንቧ የሚሰራጨው የመጠጥ ውሃ ጥራት የጎደለው፣ በቆሻሻ ዝቃጭ የተበከለና ድፍርስ መሆኑን በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙ አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች ገለፁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ደግሞ ለመጠጥ የሚውለው ውሃ መቶ በመቶ ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን አስታወቁ፡፡
Science & Technology
የሚጥል በሽታን በምግብ መከላከል ይቻላል
ሕፃናት ላይ የሚከሰትን የሚጥል በሽታ የተለየና ከፍተኛ የቅባትነት ይዘት ያለው ምግብ በመመገብ መቀነስ እንደሚቻል የእንግሊዝ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

 
Diaspora
ዲያስፖራው ባለፉት ዘጠኝ ወራት
በጋዜጣው ሪፖርተር

ዲያስፖራው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተንቀሳቀሰባቸው ዘርፎች መካከል ኢንቨስትመንት ዋናው ሲሆን በእውቀትና በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአገር ገጽታ ግንባታና በቅስቀሳ ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡
Youth
Image ወጣቱ ዲን
በምሕረት አስቻለው

ምስጋናው ሙሉጌታ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ት/ቤት ዲን ነው፡፡ የሕግ ትምህርቱን በ1999 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ አጠናቋል፡፡ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መሥራት ከጀመረ ስምንት ወር ሆኖታል፡፡ የዛሬ ስምንት ወር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሲቀጠር አብዛኞቹ መምህራን ልክ እንደሱ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው መምህራን ለመሆን የተመደቡ ነበሩ፡፡ ስለነበሩና ዩኒቨርሲቲውም አዲስ ስለነበር በቢዝነስ ፋኩልቲ ሥር ለተቋቋመው ሕግ ዲፓርትመንት አስተባባሪ ሆኖ መመረጡን ነግሮናል፡፡
 
Opinion
አትሌቶቻችንን "ከአልባሽ መስሎ ገፋፊ" ይሰውራቸው
አፈወርቅ አባመርሳ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስተናጋጅ የሆነበትና በአዲስ አበባ የተካሄደው ዝግጅት የአፍሪካ አትሌቲክስ (16ኛው) ሻምፒዮን የተሳካ መሆኑ በይፋ ተነግሮለታል፡፡ እንደዚህ ያሉ አህጉራዊ ዝግጅቶችን በብቃት በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ እንዲያውም ከቀድሞዎች የተሻለ፣ የሚል ሙገሳ ማግኘት በራሱ የመልካም ምግባር ውጤት ነው፡፡
Letter to Reporter
ማስተካከያ
በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ሚያዚያ 29 ቀን 2000 ዓ.ም “ተመስገን ዘውዴ ካልተዘጉ ሒሳቦች የተገኘው ገንዘብ እንዲጣራ ጠየቁ” በሚለው ዜና ውስጥ “ቅንጅትን በመወከል” የሚለው ሐረግ ትክክል እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡
 
Women
Image ሳያስተውሉ ጉዞ
በትዕግስት ዘሪሁን

ተወልዳ ካደገችበት አሰላ ከተማ ውስጥ የምትኖረው ከአባቷ አክስቶች ጋር እንደነበር ትናገራለች፡፡ እናቷን ገና በልጅነቷ በሞት ስላጣች አታውቃትም፡፡ አባቷም ሌላ ትዳር መሥርቶ ሌላ አገር ይኖራል፡፡ የአባቷ አክስት እንደ ወላጅ እየተንከባከበች አሳድጋታለች፡፡
Temuaget
ዴሞክራሲ ጥሩ ነው ብሎ...
ዴሞክራሲ ጥሩ ነው ብሎ በሚቀበለው (ፕሬስን ጨምሮ) የማንፈታው መጥፎ ችግር የለም
በአስፋው ነፃነት

ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሻውና ሲመቸው እያስገመገመ አለዚያም እያዘገመ፣ እያስፈራራ፣ እያስደነገጠ፣ አንዳንዴ እሳት ለብሶ እሳት ጐርሶ በግልጽና በአደባባይ እየመጣ፣ አለዚያም "ጨለማን ተገን" አድርጐ ተደብቆ፣ ተቀላቅሎ፣ ተመሳስሎና ሰርጐ እየገባ፣ ራሱን የሀሳብ ሸመታ ገበያ ውስጥ ውሱን በግልጽና በአደባባይ "መሸጥ" እና "መለወጥ" ሲያቅተው ቀስ እያለ እያደገ ከፊል አካሉን ዋና ዋና "ብልቶች"ን በ"ችርቻሮ" እና በጥቁር ገበያና በማጣሪያ ሽያጭ ይህነው የሚባል አቢይ ይዘቱን ሸጦ ለውጦ፣ እንደ ሕግም በየቦታው፣ በየአዋጁና በየደንቡ "ፀድቆ" ያለቀው የፕሬስ ሕግ ረቂቅ እነሆ በስድስት ዓመት ረዥም ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ መደበኛ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት ውስጥ አጀንዳ ሆኖ ቀረበ፡፡
 
Law
የኘሬስ ውጤትን ማገት
በሰለሞን ጐሹ

፣ሁከት የሚያነሳሳ ጽሑፍ ልታሰራጩ አስባችኋል፣ ተብለው የ፣ዕንቁ፣ መፅሄት ምክትል ዋና አዘጋጅ እና ሌሎች ሦስት ግለሰቦች ከነ 1ዐ ሺህ እትም መፅሔቶቻቸው በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር፡፡ ሚያዚያ 24 ምሽት ላይ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ሚያዝያ 29 በዋስ መለቀቃቸውም ታውቋል፡፡ መፅሄቶቹ ግን አሁንም በፖሊስ ቁጥጥር እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡ የ፣ዕንቁ፣ መጽሔት 1ዐኛ ዕትም 1/4ኛው ስለ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ዘገባ እንደያዘም ለማወቅ ተችላል፡፡
Zennk
የጣሊያን ስያሜዎች
ፋሺስት ጣሊያን በአዲስ አበባ ከተማ ነባር ስያሜያቸውን ከቀየረባቸው ቦታዎች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡-
 
Delalaw
ድብብቆሽ - 2 ተስፋዎች እየመነመኑ፣ መርሃ ግብሮች እየተጠረጠሩ ነው፡፡ ለብዙ ዓመታት በሃብትነት ይቆያሉ ተብለው እምነት የተጣለባቸው ደኖችና ሐይቆች መጠናቸውን ቀንሰዋል፡፡ ከግምት በላይና በፊት ደርቀው አቧራ የሆኑም አሉ፡፡ የዓለማያን ሐይቅ እንዲሁም በየክልሉ የጠፉ ደኖችና ሐይቆች ምስክሮቻችን ናቸው፡፡
Teles
Image ራስን ለገበያ ማመቻቸት
በትዕግስት ዘሪሁን

የሆቴሎች መብዛትና የተስተናጋጆች መበራከት በሴተኛ አዳሪነት የሚሰማሩ ሴቶች በአብዛኛው እንዲኖሩ አስተዋፅኦ ያደረገ ይመስላል፡፡ መተሃራ ከተማ ውስጥ በርካታ ሴቶች በየሆቴሎቹ በሴተኛ አዳሪነት ሙያ ተሰማርተው ይታያሉ፡፡ ከናዝሬት እስከ ድሬዳዋ ድረስም አገር እያቀያየሩ እንደሚሰሩ ይነገራል፡፡ ይሄንን የሚያደርጉት ሁሌም ለገቡበት ቤት አዲስ እንዲሆኑ ነው፡፡ እገሌ ሆቴል አዳዲስ ልጆች መጥተዋል ተብሎ ገበያው ስለሚደራ፤ ቤት እየቀያየሩና ፊታቸው ሳይሰለች ገበያቸው ሳይቀዘቅዝ መሥራት ስለሚፈልጉ መሆኑን አንድ የሆቴል ባለቤት አጫውተውናል፡፡ ብዙዎቹ የከባድ መኪና ሹፌሮችም ደስተኛ ሆነው ሲስተናገዱ የሚያመሹት ሴቶቹ አዳዲስ ሲሆኑ መሆኑን ነግረውናል፡፡
 
Sport
Image "ከረጅም ርቀት ውጭ...
"ከረጅም ርቀት ውጭ ኢትዮጵያዊያን ውጤታማ አይሆኑም በሚለው አልስማማም"
አትሌት ዘምዘም አህመድ

ተወልዳ ያደገችው አርሲ አርጆ ወረዳ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ በ16ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለአገሯና ለራሷ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፡፡ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነው አያውቁም፡፡ አትሌት ዘምዘም አህመድ የመጀመሪያዋ ሆናለች፡፡ አነጋግረናታል፡፡
Taxi
ማረሻን ማረሻ ማለት
የትራንስፖርት ፈላጊው ቁጥር በጣም በዛብኝ፡፡ በታክሲ፣ በከተማ አውቶቡስ፣ በቤት መኪና፣ በእግር ወዘተ. የሚጓዘው መንገደኛን በመቶኛ ምን ያህል መሆኑን ማስቀመጥ ተሳነኝ፡፡ በርከት ያለው ቁጥር በታክሲና በአውቶቡስ የሚጓጓዘው መንገደኛ ነው፡፡

 
World
Image በዚምባብዌ ድጋሚ ምርጫ ይካሄድ ይሆን?
ባለው ወቅታዊ ሁኔታ በዚምባብዌ ድጋሚ ኘሬዚዳንታዊ ምርጫ ማድረግ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ታዛቢ ልዑክ መሪ ኪንግስሊ ማማቦሎ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ድብደባና እንግልት ደረሰብን የሚሉ በርካታ ሰዎች በሆስፒታሎች ይገኛሉ፡፡  የዙምባብዌ የምርጫ ኮሚሽን የድጋሚ ምርጫው እስከ አንድ ዓመት ሊዘገይ እንደሚችል የገለፀ ሲሆን በአገሪቱ ሕገ መንግሥት እንደተመለከተው የምርጫ ውጤት ይፋ ከሆነ ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ መካሄድ የነበረበት የድጋሚ ምርጫ በዚህ ቀን ይካሄዳል ተብሎ በምርጫ ኮሚሽኑ የተቀመጠ ነገር የለም፡፡
 
  • Do You Know ?
    How To Increase Font Size
    You can increase the font size of the website if it appears smaller than normal. Just click the member area link at the top right of this page and the page will slide down. At the top left corner of the page, look for three small buttons. To increase font size, click the button with "+" sign and "-" sign to decrease font size.
  • Tips !
    Tips for Amharic Version
    • Use Internet Explorer version 6 or better
    • Adjust your screen resolution to 1024 X 768
    • Use the font resizer to increase font size if needed
    • Though it is not strictly needed having power geez unicode font could enhance the font rendering in your browser
 

Important Links

Visit Ethiopian Yellow PagesA forum on Dialogue, Democracy & Development