Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
May 09th
Home arrow Sections arrow ትልቁ የህዋ ካርጎ
ትልቁ የህዋ ካርጎ Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
ትልቅ የእቃ መጫኛ ካርጎ ወደ ህዋ ተላከ፡፡ አዲሱ አውሮፓ ሰራሽ የህዋ ላይ እቃ መጫኛ ካርጎ ከፈረንሳይ ጊኒ ወደ ህዋ የመጠቀ ሲሆን የተላከበት ዓላማም ለዓለም አቀፍ የህዋ ማዕከል አንዳንድ እቃዎችን ለማድረስ መሆኑ ታውቋል፡፡

ወደ ህዋ የተላከው ካርጎ እስካሁን ድረስ አውሮፓ ወደ ምህዋር ከላከቻቸው ሁሉ ትልቁና ውስብስብ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኤርያን-5 በተሰኘችው ሮኬት ተጭኖ ወደ ህዋ የተላከው ካርጎ 2ዐ ቶን ያህል የመያዝ አቅም አለው፡፡ በመጠቃው ወቅት ታላላቅ ሰዎች፣ የህዋ ማዕከሉ ባለ ሥልጣናትና ባለፉት አስራ አንድ ዓመታት ለካርጎ ሥራ ታላቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ቡድኖች የተወከሉ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡

ወደ ዓለም አቀፍ የህዋ ማዕከል የተላኩት እቃዎች ማዕከሉ በሃይል አቅርቦት በኩል እንዳይቸገር ለማድግ የሚረዱ ናቸው፡፡

ሰሞኑን በጊኒ ወደ ህዋ የተደረገው መጠቃ ለኤርያን-5ም ለየት ያለ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአውሮፓ ሮኬቶች ታሪክ እንደዚህ ከባድ እቃ ይዞ የመጠቀ እስካሁን አልነበረም፡፡ እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ እስካሁን በነበረው ተሞክሮ ሮኬቶች ይዘው የሚመጥቁት ከ10 ቶን በታች የሆነ ክብደት ይዘው ነበር፡፡ አዲሱ ካርጎ ግን እቃ መጫኛወ ብቻ 4.860 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆኝ ለጠፈርተኞቹ የሚሆን ኦክስጅንና ናይትሮጅን አየር 2ዐ ኪሎ ግራም እንዲሁም የተለያየ መጠንና ክብደት ያላቸውን እቃዎች ጭኗል፡፡

አውሮፓ አዲስ ያበረከተችውን ካርጎ በዓለም አቀፉ የህዋ ማዕከል ኘሮጀክት አባልነቷ ያበረከተችው መሆኑን ገልፃለች፡፡ ከዚህ በኋላ አራት ተሽከርካሪዎችን ወደ ማዕከሉ እንደምትልክም ጨምራ ገልፃለች፡፡

አልኮል ከልብ ህመም ለመታደግ

በመካከለኛ የዕድሜ ክልል የሚገኙ አልኮል የማይጠጡ ሠዎች የተወሰነ የአልኮል መጠጥ በምግባቸው ውስጥ በመቀላቀል ለልብ ህመም የመጋለጥ አደጋ መቀነስ ይችላሉ ይለናል ሠሞኑን ይፋ የሆነው የሳውዝ ካሮሊና ጥናት ለአራት ዓመታት ያህል በ7 ሺህ 500 ሰዎች ላይ በተደረገው ምርምር መካከለኛ የአልኮል መጠጥ የሚጠጡ ሰዎች ከማይጠጡት ጋር ሲነፃፀሩ በ38 በመቶ ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው የቀነሰ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡ በተለይ የወይን ጠጪዎች እጅጉን ተጠቃሚ እንደሆኑ ነው በአሜሪካ የሜዲካል መፅሄት ላይ የወጣው የምርምር ውጤት የገለፀው፡፡

የልብ ስፔሻሊስቶች ግን አልኮል ለልብ ህመም ዓይነተኛና ሙሉ መፍትሄ አይደለም ነው የሚሉት፡፡ የዚህ ምርምር መሪ የሆኑት ዶ/ር ዳና ኪንግ እንደሚሉን ደግሞ በጥንቃቄ በተመረጡ ሠዎች ላይ የተደረገው ምርምር የሚያሳየው ጤናማ የሆነ ልብ ያላቸው ሠዎች እነሱ ባያውቁትም በምግባቸው ውስጥ አልኮል ይኖር ይሆናል፡፡

ጥናቱ በተጨማሪም አልኮል የሚጠጡ ሰዎች የኮሌስትሮል መጠናቸው ከማይጠጡት ሰዎች አንፃር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል፡፡

ጥናቱ ይህን ይበል እንጂ ከዚህ በፊት አልኮል ጠጥተው የማያውቁ ሰዎች እንዳይጀምሩ የአሜሪካው የልብ ማህበር አስጠንቅቋል፡፡ ዶ/ር ዳናን ግን የአልኮል ውጤት ፈጣንና ከፍተኛ መሆኑ አስደንቋቸዋል፡፡

ህንድ ውስጥ የአእዋፍ ኢንፍሉዌንዛ ተከሰተ

በህንድ ምዕራባዊ ቤንጋል አካባቢ የአእዋፍ ኢንፍለዌንዛ በሽታ መከሰቱ ታወቀ፡፡ በአገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም በሽታውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በሽታው ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው የሚጠረጠሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዶሮዎችን ገድለዋል፡፡

በተጠቀሰው አካባቢ በሽታው የተከሰተው ከአንድ ወር በፊት ሲሆን ከዛ ወዲህ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች ታርደዋል፡፡ H5N1 ቫይረስ የተሰኘው የአእዋፍ በሽታ ወደ ሰው መተላለፍ የሚችል ሲሆን አንዴ ከተላለፈም ወረርሽኝ በመሆን በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን የመግደል አቅም አለው፡፡ ህንድ ውስጥ በበሽታው የታጠቃ ሰው እስካሁን ድረስ አልተገኘም፡፡

ከወር በፊት የተከሰተው የአእዋፍ ኢንፍሉዌንዛ 13 ከተማዎችንና 19 መንደሮችን የበከለ ሲሆን ወደ ዶሮ እርባታ ቦታዎችም ተዛምቷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በአገሪቱ አዲስ የአእዋፍ ኢንፍሉዌንዛ መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ በሃገሪቱ ከሦስት ሚሊዮን በላይ አእዋፍት ሞተዋል፡፡

የ2ዐዐ7 የጎርፍ አደጋ ከሙቀት መጨመር ጋር አይያያዝም

በእንግሊዝ ባለፈው ዓመት የደረሰው የጎርፍ አደጋ ከዓለም አቀፍ የሙቀት መጨመር ጋር እንደማይያያዝ ዘ ሴንተር ፎር ኢኮሎጂ ኤንድ ሲ.ኢ.ኤች ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ለጎርፍ አደጋው መከሰት ዋናው ምክንያት የክረምቱ ዝናብ የመራዘሙ ከአፈሩ ውሃ የመምጠጥ አቅም በላይ በመሆኑ ነው፡፡

በ2ዐዐ7 በተለይ በሰኔና ሃምሌ ወራት የዝናቡ መጠን ሃያ በመቶ ጨምሮ ነበር፡፡ በመሆኑም ወንዞቹ በፊት ከነበረው በባሰ ሞልተው ይፈሱ እንደነበር ታውቋል፡፡

በደረሰው አደጋም የሦስት ቢሊዮን ፓውንድ ያህል ውድመት ደርሷል፡፡ 55 ሺህ ያህል ቤተሰቦች እና ስድስት ሺህ ያህል የንግድ ቤተችም ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

ፔንታጐን ጉግልን አገደ

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስተር የዓለማችን ቁጥር አንድ የኢንተርኔት መረብ ኩባንያ በአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ውስጥ ምንም ዓይነት የፊልምና ሌላ ጥናት እንዳያካሂድ ከለከለ፡፡

የአሜሪካው የምድር ጦር ይህን ጉዳይ የፀጥታ ስጋት እንደሆነ ነው የሚገልፀው፡፡ ውሳኔው የተላለፈው በቅርቡ በቴክሳስ በሚገኘው ፎርት ሳም ሂውስተን በተባለ የጦር ሠፈር ምስል (ካርታ) በጉግል ከተለቀቀ በኋላ ነው፡፡

ይህን ተከትሎ የጉግል ቃል አቀባይ እንዳሉት ምስሉ ከጉግል ተነስቷል፡፡ ምስሉ 360 ዲግሪ እይታና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን፣ ፅህፈት ቤቶችን እና የተለያዩ ቦታዎችን ያካተተ እንደነበርም የመከላከያ ሚኒስቴር ለአጃንስ ፍራንስ ኘሬስ ተናግሯል፡፡

የጉግል ቃል አቀባይ ላዩ ጉግል የቴክሳስን የጦር ሰፈር ጥልቅ መረጃ መውሰዱ ስህተት ነው ብለዋል፡፡ ላሪዮ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የወታደራዊ መረቦችን ማየት የእኛ ፖሊሲ አይደለም፡፡ በወቅቱ የተፈፀመውም ስህተት ነበር፡፡ በመሆኑም ወዲያውኑ ምስሉን ከመረጃ መረባችን አንስተናል ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >