Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 11th
Home arrow Sections arrow እርዳታው የተረጂነት ስሜት...
እርዳታው የተረጂነት ስሜት... Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
እርዳታው የተረጂነት ስሜት መፍጠር የለበትም

በእርዳታ ላይ ብቻ መተማመን ስንፍናንና ጥገኝነትን ይጋብዛል፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ የሥራ ክቡርነትን ይቀንሳል፡፡ ተነሳሽነትንና ፈጠራን ያዳክማል፡፡ ፈጣንና ተከታታይ እድገትን ለማስመዝገብ እንዲሁም ከድህነት ለመላቀቅና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ጎራ ለመሰለፍ አገሪቱ የተያያዘችውን እንቅስቃሴ ይጎትታል፡፡
 
ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 30 ቀን 2000 እትም ቆይታ ገጽ "ስንዴ እየጠበቁ እንዲኖሩ ሳይሆን (ተረጂዎች) ሕይወታቸውን እንዲለውጡ ነው የሚፈለገው" በሚል ርዕስ የቀረበው ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ተረጂዎች ለመስራት ብቁ መሆናቸው ከተረጋገጠ ከተረጂነት እንዲላቀቁ ማድረጉ ሁለት  ጠቀሜታዎች እንዳሉት መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ከጠቀሜታዎቹም መካከል አንደኛው መሥራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ ለሚገኙት ሌሎች ወገኖች ቦታ መልቀቅ ሲሆን ሁለተኛውና ዋነኛው ሰርቶ መብላት እርካታን እንደሚፈጥር፣ ሥራ ክቡር እንደሆነና በራስ መተማመንን እንደሚያጎናጽፍ፣ በአንፃሩ ደግሞ ዕርዳታ ጠብቆ መኖርና ጥገኝነት ምን ያህል አሳፋሪና አስነዋሪ እንደሆነ ለመገንዘብ ያስችላል፡፡ ስለሆነም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማንም ሆኑ ሌሎች ለተረጂነት የተዳረጉ ወገኖች መገንዘብ ያለባቸው  የሚሰጣቸው ዕርዳታ ሰርተው ለመብላት የሚያስችል አቅም እስከሚያገኙ ድረስ እንጂ የተረጂነት ስሜት እንዲፈጥርባቸው ለማድረግ አለመሆኑን ነው፡፡

ይህ አይነቱን መጥፎ ስሜት ኅብረተሰቡ በጋራ ሆኖ ሊዋጋው ይገባል፡፡ ኅብረተሰቡም በዚህ ላይ ያለውን ግንዛቤ ከፍ እንዲል መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡

(ዘላለም ወልዴ፣ ከሽሮ ሜዳ)
 
< Prev   Next >