Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow በአዲሱ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ...
በአዲሱ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ... Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
በአዲሱ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ ለመሳተፍ አንድ የአሜሪካ ኩባንያ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

ኢትዮጵያ አምስት ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የባቡር ሃዲድ ለመዘርጋት ማቀድዋንና ለዚህ ኢንቨስትመንትም አንድ የአሜሪካው ሎጂስቲክ የተባለው ኩባንያ ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁን የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡
 
እንደዘገባው ከሆነ አዲስ የሚሰራው የባቡር ሐዲስ መስመር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች ጋር የሚያገናኝና እምቅ የሃይልና የማዕድን ሃብትን ለመጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

የባቡር ሃዲድ መስመሩ ግንባታ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር የተናገሩት ሚኒስትሩ ከግንባታው መጀመር ቀደም ብሎ የባቡር መስመሩን የሚቆጣጠር ኤጀንሲ እንደሚቋቋም አመልክተዋል፡፡

አገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ለመጠቀም በተለይ በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የብረት ማዕድን ለማውጣት፣ በምሥራቅ በኩል ደግሞ የጋዝና የነዳጅ ዘይት ሃብቷን ለመጠቀም እንዲሁም ንግድና እርሻን ለማስፋፋት የሚገነባው የባቡር መስመር ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ሚኒስትሩ የባቡር መስመሩን ለመገንባት የሚያስፈልገውን ገንዘብ በተመለከተ ማብራሪያ ያልሰጡ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >