Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow የሕንድና የአፍሪካ የንግድ ልውውጥ...
የሕንድና የአፍሪካ የንግድ ልውውጥ... Print E-mail
Wednesday, 12 March 2008
የሕንድና የአፍሪካ የንግድ ልውውጥ 20 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ

ሕንድ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ያጠናክራል የተባለውና በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊኖር ስለሚገባው የሥራ መርሃ ግብር (Action plan) ለማፅደቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ 17 አገሮች የሚገኙበትን የሦስት ቀን ጉባኤ ልታካሂድ ነው፡፡ የንግድ ልውውጡ 20 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡
 
በመጪው ሚያዚያ ሕንድ ውስጥ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ የጋራ ጉባኤን (India-Africa Forum Summit) አስመልክቶ የሕንድ የአገር ውስጥ ሚኒስትር አድርጊድ ሻርማ እንደገለፁት ጉባኤው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ የሚያደርስ ነው፡፡

በጉባኤው ላይ የሁለቱ ወገኖች የስነ ምግባር ደንብ ረቂቅ ማፅደቅ ከዋነኛ አጀንዳዎቹ አንዱ ሲሆን ደንቡ ከመፅደቁ በፊትም በረቂቁ ላይ የአፍሪካ አገሮች ሃሳብ እንዲሰጡበት የተላከላቸው መሆኑንም አይ.ኤ.ኤን.ኤስ የተባለ የሕንድ ጋዜጣ አመልክቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ሕንድ ከአፍሪካ ጋር ባላት ግንኙነት የቴክኖሎጂና የትምህርት እገዛ ትሰጥ እንደነበር ጋዜጣው ጠቁሞ፣ በሕንድ የተጠራው ይህ ጉባኤ ሕንድ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ግንኙነት የበለጠ ከፍ እንዲል የሚደረግበት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

ከጉባኤው መክፈቻ ቀደም ባሉት ቀናት የሁለቱን ወገኖች ግንኙነት የሚያመለክቱ ፌስቲቫሎችና የሙዚቃ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

የ17 አገራት መሪዎች ይገኙበታል በተባለው በዚህ ጉባኤ ላይ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (....፣ ኮሜሳና ኢኮዋስ ተወካዮች ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሕንድና በአፍሪካ አገሮች መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 20 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ዋነኛ የንግድ ሸሪኮች ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱት  ውስጥም ኢትዮጵያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያና ኡጋንዳ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
 
< Prev   Next >