| ዐውደ ርዕይና ሽያጭ 2000 |
|
|
| Wednesday, 12 March 2008 | |
|
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ዝግጅት ተቋም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የታተሙ በዓይነታቸው የተለያዩ መጻሕፍት ለዐውደ ርዕይና ሽያጭ የቀረበበት መሰናዶ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ የተቋሙ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ (6 ኪሎ) በተዘጋጀው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዐውደ ርዕዩና ሽያጭ ላይ ከ30 በላይ የመጻሕፍት አሳታሚ ድርጅቶች፣ አታሚ ድርጅቶች፣ የምርምር ተቋማትና ደራስያንም ጭምር የኅትመት ውጤቶችን ለአንባብያን ለሽያጭ መቅረቡን፣ እስከ 50 ከመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽና የግዢ ማበረታቻ እንደተደረገበት ገልጸዋል፡፡ ለንባብ ባህል ዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ በሚታሰበው መሰናዶ ላይ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ደራስያን ከራሳቸው መጻሕፍት የሚያነቡበት፣ አንጋፋ ደራስያን የሕይወት ገጠመኞቻቸውን ለኅብረተሰቡ የሚያጋሩበት፣ ስለሀገሪቱ የመጻሕፍት ኅትመትና ሥርጭት ውይይት የሚደረግባቸው መድረኮች መዘጋጀታቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ የዐውደ ርዕይና ሽያጩ ዋና ዓላማ የታተሙ መጻሕፍትን በአንድ ቦታ ላይ ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ለዕይታና ለግብይት ለማቅረብና የመጻሕፍት አሳታሚ ድርጅቶች፣ አከፋፋዮች፣ ደራስያን፣ የቤተመጻሕፍት ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና አንባቢው ኅብረተሰብ የሚገናኙበት መድረክ ለመፍጠር መሆኑ ታውቋል፡፡ በሔኖክ ያሬድ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |