Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home
በሕግ ከነገዱ ቀና ነው መንገዱ! Print E-mail
Sunday, 16 March 2008
Image
ማጭበርበር ከወደዱ ጥልቅ ነው ጉድጓዱ!

በርዕሱ ላይ የተቀመጡት ሁለት ነጥቦች ተግባራዊ ሆነው የሚታዩ ናቸው? እውነት ሕግን ተከትሎ፣ ሃቀኛ ሆኖ፣ አገርንና ሕዝብን ወድዶና አክብሮ የሚነግድ ሰው መንገዱ ቀና ይሆንለታል? እውነት አጭበርብሮ ሰርቆና አታሎ የሚነግድ ነጋዴ እየተያዘ ችግር ውስጥ የሚገባ፣ ሥራውም ገደላማና ጥልቅ ጉድጓድ የሞላበት ነው?

ሰሞኑን እየታየ ባለው መንገድ መንግሥት ጥብቅ መሆን ከቀጠለ እውነትም በሕግ ከነገዱ ቀና ነው መንገዱ ያሰኝ ይሆናል፡፡ ማጭበርበር ሲወዱ ጥልቅ ነው ጉድጓዱ የሚባልበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም፡፡

በሕግ ለመስራት የሚንቀሳቀስ፣ የሚነግድ እየተጎዳና እየተገፋ የሚሄድበት፣ አጭበርብሮና አታሎ ሰርቆ የሚሄደው ነጋዴ ግን ሲካስ፣ ሲጠቀም፣ ሲያተርፍና አይዞህ ሲባል የታየበት ሁኔታ ነው የተስተዋለው፡፡

ሰሞኑን እየታየ ያለው የወርቅ ማጭበርበርና የሃሰት ብር የማሳተም ወንጀል የሚያረጋግጠው ተሰርቶና ተለፍቶ የተገኘ ሃብት አለመሆኑን ነው፡፡ ንጹህ ነጋዴ የለም ማለት ነው? የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው፡፡ ባለሥልጣናት በዚህ ተግባር ተባባሪ አልሆኑም? የሚል አጀንዳም እየተከፈተ ነው፡፡ የሚሰማን አጥተን ነው እንጂ ብለን ነበር የሚሉም ብዙ ናቸው፡፡

ሃቀኛው የሚጨነቅበት፣ አጭበርባሪው የሚፈነጥዝበት መድረክ ለመኖሩ ጥናትና ምርምር አያስፈልገውም፡፡ ገሃድ የወጣና ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነውና፡፡ አንዱ እቁብ ገብቶ፣ አራጣ ተበድሮ፣ የቤተሰቡና የጓደኛው ንብረት አስይዞ፣ ተፍጨርጭሮ ቢዝነሱን ለማሳካት መከራውን ያያል፡፡ ሌላው ትንሽዬ ኪዮስክ ከፍቶ በጥቁር ገበያ ዶላርና ዩሮ እየመነዘረ ሕጋዊ ፍቃድ ሳይዝና ግብር ሳይከፍል ሚሊየነር ሆኖ ፎቅ ሲሰራ ይታያል፡፡

አንዱ በሪል ስቴት ሥራ ውስጥ ገብቶ ቤት ለመግዛት ከወሰኑት ቅድሚያ ክፍያ ተቀብሎ ለራሱ ምንም ሳይዝ በቅድሚያ ክፍያ ሃያ ሰላሳ ሚሊዮን ብር ግብር ለመንግሥት በሃቀኝነት አስረክቦ ሥራ ይጀምራል፡፡ በመሃልም ዓያሌ መንገላታት ያጋጥመዋል፡፡ ትቼው ልውጣ ወይ ብሎ እስከማወላወል ይደርሳል፡፡ ሌላኛው ብልጣ ብልጥ ደግሞ ለሪል ስቴት ብሎ በወሰደው ቦታ ላይ ከአሥር ካሬ ሜትር ያልበለጠ ..ሰርቪስ.. ሰርቶ መሬቱን ይሸጠዋል፡፡ ቤት ሳይሆን መሬት ሽያጭ ውስጥ ይገባል፡፡ ሚሊየነር ይሆናል፡፡ ሃቀኛው ይጎዳል አጭበርባሪው ይጠቀማል፡፡

አንዱ ያመጣው ባሌስትራ ወርቅ ነው ተብሎ ይታመንለታል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት እምነት አይባል “ተባባሪነት”፣ አገር ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ይከስራል፣ መሳቂያ መሣለቂያም ይሆናል፡፡ አንዱ ደግሞ ያመረተውን ምርት ብቻ ሳይሆን ምርቱን ለማምረት የተሰማራው ሠራተኛ ታስሮ የማያውቅ፣ እብድ አለመሆኑን ማስረጃ አምጣ ተብሎ ይወጠራል፡፡

አንዱ መከራውን አይቶ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ያቋቁማል፡፡ ሌላው በኮንትሮባንድ ልብስ ያመጣል፡፡ አምራች ተብሎ ፋብሪካ አቋቁሞ ገዥ ያጣል፡፡ ዋጋው ውድ ነው ተብሎ ይቀራል፡፡ በኮንትሮባንድ የሚያመጣው ቀረጥ ስለማይከፍል በርካሽ ይሸጣል፡፡ ግብር ከፋይ ይጎዳል፤ ኮንትሮባንዲስቱ ይጠቀማል፡፡

አንዱ በስንት መከራ የመድሃኒት ፋብሪካ ያቋቁማል፡፡ ሌላው መድሃኒቱን በኮንትሮባንድ ያመጣዋል፡፡ በርካሽ የሚሸጠው ኮንትሮባንዲስቱ ነው፡፡ ቀኑ ያለፈበት፣ በረሃ ዱርና ገደል አቋርጦ የመጣ የተበላሸ መድሃኒት ይሸጣል፡፡ አጭበርባሪው ይጠቀማል፣ ሃቀኛው ይጎዳል፡፡

ብዙ ምሣሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ገሃድ የሆነ ሃቅ ስለሆነ ይህ ይብቃንና እንደዚህ ሆኖ መቀጠል አለበት ወይ? የሚለውን ጥያቄ እናንሳ፡፡

አጭበርባሪን የሚክስና ሃቀኛን የሚጎዳ አሰራር በአስቸኳይ መቆም አለበት፡፡ መንግሥት ሰሞኑን በጨው ነጋዴዎች፣ በወርቅ አጭበርባሪዎችና በሕገወጥ ዶላር መንዛሪዎች ላይ የወሰዳቸው እርምጃዎች ዓይነት በተጠናከረ መልኩ መቀጠል አለባቸው፡፡

አጭበርባሪና ሕገወጥ ነጋዴዎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለአደጋና ለውርደት የሚዳርጉ መሆናቸውን በሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል፡፡ መቀመቅ የሚወርዱበት ጥልቅ ጉድጓድ እንደሚጠብቃቸው ሊታያቸውና ሊነገራቸው ይገባል፡፡

በሃቅ የሚሰራው ወገን ደግሞ ሊበረታታና የመንግሥትን ድጋፍ ሊያገኝ ይገባል፡፡ በሃቅ የሰራ ይጠቀማል፣ አጭበርባሪ ይጎዳል የሚል ግልፅ መልዕክት በማያሻማ መንገድ መተግበር አለበት፡፡ የመንግሥት እርምጃም ጊዜያዊና እያደር የሚጠፋ እንቅስቃሴ መሆን የለበትም፡፡ ምንጊዜም በአጭበርባሪዎች ላይ ምህረት እንደሌለው ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡ ምንጊዜም ከሃቀኞች ጋር እንደሚቆም በተግባር ማረጋገጥ አለበት፡፡

ሃቀኛን የማበረታታትና አጭበርባሪን የመቅጣት እርምጃ ከመንግሥት ብቻ ሳይሆን ከሕዝብም ሊመጣ ይገባል፡፡ ሕዝብ ከአጭበርባሪ ጋር አልሰራም ብሎ መነሳት አለበት፡፡ የሸማቾች ማኅበርን እያቋቋመ ሊታገል ይገባል ብቻ ሳይሆን አጭበርባሪዎችን ማጋለጥና መጠቆም አለበት፡፡ መንግሥትም ወንጀለኛን ለሚጠቁሙ የማበረታቻ ከፍያ ሊከፍል ይገባል፡፡ ይህ ማበረታቻ ወንጀለኞችና አጭበርባሪዎች በሕዝብ እንዲታደኑ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ሕዝቡም፣ መንግሥትም፣ ሃቀኛ ነጋዴዎችም በጋራ ቃል ይግቡ፡፡ በሕግ ከነገዱ ቀና ነው መንገዱ የሚል መልዕክትና አሠራር በግልጽ ይስፈን፡፡ ማጭበርበርን ከወደዱ ጥልቅ ነው ጉድጓዱ የሚል ተግባራዊ መፈክርም ይስተጋባ፡፡ ያኔ ነው “አገር እንዴት ነው?” ስንባል በልበ ሙሉነት “ሰላም ነው” የምንለው፡፡
 
< Prev   Next >
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
በፕሬስ ሕጉ ላይ የሚወያይ ስብሰባ ተጠርቷል
በጋዜጣው ሪፖርተር

በትናንትናው ዕለት በፓርላማ በፀደቀው የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት ሕግ ላይ የሚወያይ ወርክሾፕ በዛሬው እለት በጊዮን ሆቴል መጠራቱን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

Read more...
 
Zena
Image አወዛጋቢው የፕሬስ ህግ ፀደቀ
"የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚገድል አዋጅ ነው" አቶ ተመስገን ዘውዴ
"እኔና እንደኔ የሚያስቡ ሰዎች ይህን ቀን በሀዘን ነው የሚያዩት" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

Editorial
Image ከፕሬስ ነፃነት ሽሽት
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቅርቡ ከኒውስዊክ መፅሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሚፀድቀው የፕሬስ ሕግ ኢትዮጵያን በፕሬስ ነፃነት መስፈርት በዓለም አሉ ከተባሉት በግንባር ቀደምትነት የሚያሰልፋት ይሆናል ብለው ቃል ገብተውልን ነበር፡፡ ትናንት የፀደቀው ግን ኢትዮጵያን በፕሬስ ነፃነት ግንባር ቀደም የሚያደርጋት ሳይሆን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባት ነው፡፡ ቃል የተገባልን ሌላ የፀደቀው ሌላ!

 
Politics
የአዲሱ የተቃዋሚ ፓርቲ ዳዴ
በሰለሞን ጎሹ

ባለፈው እሁድ ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በኢየሩሳሌም ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዷል፡፡ ፓርቲው በእለቱ የቀድሞውን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ምክትል ኘሬዚዳንት አቶ ሙላቱ ጣሰውን ኘሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

Briefs
ከ3ሺ 400 በላይ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች ተመደቡ
በደቡብ ክልል በቀበሌ ደረጃ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ሕዝቡ ቀልጣፋና ፈጣን የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ከ3.ሺ 400 በላይ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች መመደባቸውን የክልሉ አቅም ግንባታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

 
Business & Economy
Image የብሔራዊባንክ ረቂቅአዋጅ አሁንም እያነጋገረ ነው
በዳዊት ታዬ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተዘጋጁት የባንክ ሥራና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጆች ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሸጋግረዋል፡፡

Shemach
የከርሞ ገበያን ለማረጋጋት
በናታን ዳዊት

በርካታ የአገራችን አርሶ አደሮች ዓመታዊ ምርታቸውን ለማምረት ማዳበሪያ መጠቀም ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ያለ ማዳበሪያ መሬቱ አልሰጥ ብሏል፡፡ በዚህም የተነሳ አርሶ አደሮቻችን ማዳበሪያን እንደዋና የምርት ግብዓታቸው አድርገው ይወስዳሉ፡፡ በየዓመቱ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የማዳበሪያ መጠን እየጨመረ መምጣቱም የተጠቃሚዎች ቁጥር እየበረከተ መሆኑን ያሳየናል፡፡

 
Interview
"እንደ እንጉዳይ በአጭር ጊዜ ውስጥ...
"እንደ እንጉዳይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደርስ የሚችል የምግብ ዘር የለም"
ዶ/ር ዳዊት አባተ

እንጉዳይ በውስጡ ፕሮቲን፣ አሚኖ አሲዶች፣ ሚኒራሎች0ቫይታሚኖች፣ የያዘ ሲሆን እንዲሁም በምግብ አጣፋጭነቱና በመድሃኒትነቱ ይታወቃል፡፡ እንጉዳይን በጥናት በተደገፈ መልኩ ለማምረትና ለምግብነት ለማዋል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጂ ዲፓርትመንት አነሳሽነት ጥናት ማድረግ የተጀመረው ከ10 ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጥናቱ ውጤታማ ሆኖ ኦይስተር፣ ሽታኪ፣ በተን እና ናሜኩ የተባሉትን አራት ዓይነት ለምግብነት የሚውሉ የእንጉዳይ ዓይነቶች በኢትዮጵያ በመጠኑ ማምረት ተጀምሯል፡፡

Fermata
የመጀመሪያዎቹ
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በ1896 ዓ.ም የመንገድ መዳመጫ ሩሎ እና ሰረገላ አስመጥተው የመንገድ ሥራ አስጀመሩ፡፡ የመጀመሪያውም መንገድ 56 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከአዲስ አበባ እስከ አዲስ ዓለም ድረስ የተሰራው ነው፡፡

 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር
(ሥራ አስኪያጁ፣ በሚኒስትሮች የሚታዘዙ ሳይሆኑ ሚኒስትሮችን የሚያዙና በሚኒስትሮች የሚፈሩ ናቸው)

Life & Art
Image ሰንደቅ ዓላማችን
በሔኖክ ያሬድ

"በባንዲራ"" በባንዲራ"" በባንዲራችን"" በሕግ ቁም ብዬሃለሁ!!" ትለዋለች፤ እየተከተለች፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ፣ ወደ ቀጨኔ መድኃኔዓለም በሚወስደው መንገድ፣ ድልድዩ አጠገብ፣ ከአባ ሀብቴ ቤት አጠገብ ነው፡፡ ሴትየዋ ጠላ ሻጭ ናት፡፡

 
Social
Image “ኮትቻ የዋለ ምሳና ራቱን አያጣም”
በምሕረት ሞገስ

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቀድሞው የባንክ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎች አብዛኞቹ ግንባታቸው ተቋርጧል፡፡ አካባቢው ጭር ብሎ የሚታየው መሠረታቸው ወጥተው የቆሙ ጅምር ግንባታዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግንባታዎች መጀመሪያና ሁለተኛ ፎቅ ድረስ ደርሰው ቆመዋል፡፡

Science & Technology
የሚበር መኪና እውን ሊሆን ነው
የቤት ውስጥ ኮምፒውተርና በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና በመስራት የሚታወቁት ክሊቭ ሲን ክላር ለቢቢሲ ሬድዮ እንዳስታወቁት ለረዥም ዓመታት ሲያልሙት የቆዩት በአየር ላይ መብረር የሚችል መኪና እውን ሊሆን ነው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት “በአየር ላይ የሚበር መኪና ለመስራት በኢኮኖሚም ሆነ በቴክኒክ የሚቻል ነው”

 
Diaspora
Image የዲያስፖራውን መረጃ የማሰባሰብ...
የዲያስፖራውን መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ ነው

በምሕረት ሞገስ

በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው የውጭ አገሮች ዲያስፖራውን አስመልክቶ መረጃ የማሰባሰቡ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Youth
Image “ስለ ምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች...

“ስለ ምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች አለማወቅ አስገራሚ ነው”

በምሕረት አስቻለው

“ወጣቶች የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉባቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች በተለያየ መልኩ ለመፍታት ወጣቶቹ ተደራጅተው በመንቀሳቀስ፣ መንግሥትና ሌሎች አካላት ደግሞ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

 

 
Opinion
ራዲዮ አክቲቭ ቃላት የሚተፉ ፕሬስማ!!

(አ.አ.)

መጀመሪያ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ቻርተር ተረጋገጠ ተባለ፡፡ በግንቦት 1983 ዓ.ም እና ያንኑ ያህል አሁን ታሪካዊ እየሆነ በመጣው በጥቅምት 11 ቀን 1985 ዓ.ም መካከል የነበሩት 512 ቀናት (17 ወራት ወይም 73 ሳምንታት) ለሁለት የተከፈለ የተለያዩ አስተያየቶችና አቋሞች የተስተናገዱባቸው ነበሩ፡፡ በአንድ በኩል የፕሬስ ነጻነት ህግን አስፈላጊነትን፤ አምንበታለሁ የሚለው ወገን የፕሬስ ህጉ ዘገየ፣ መሥራት አልቻልንም እያለ ጮኸ ተቃውሞውን ስጋቱን አስተጋባ፡፡

 

Letter to Reporter
ክትትል ይደረግ
የሕክምና ሙያ ከሰው ሕይወት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ጥንቃቄና ትኩረት የማድረጉ ሥራ ደግሞ ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ ባለድርሻ አካላትና ኅብረተሰቡም ጭምር ሊሳተፉበት ይገባል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድና ሙያው ከሚፈቅደው ውጪ የሚንቀሳቀሱ የሕክምና ተቋማትን በመጠቆም ረገድ ኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተውም መንግስታዊ አካል በየወቅቱ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

 
Women
Image ከፈተና ወደ ፈተና
በትዕግሥት ዘሪሁን

እናቷን በሞት ያጣችው ገና በ11 ዓመቷ ነው፡፡ እናቷ ከሞተች በኋላ በእግሯ መራመድ የማትችለውን የሁለት ዓመት እህቷን የእንጀራ አባቷን የመንከባከብ ኃላፊነት ወደቀባት፡፡ እሷ እንደምትለው እቤት ውስጥ የሚያስፈልገውን ስራ ሁሉ የምትሰራው ብቻዋን ነበር፡፡ ቤት ማፅዳት፣ ልብሳቸውን ማጠብ፣ ምግብ ማብሰልና አስፈላጊ የምግብ እህሎችን መግዛት ይጠበቅባታል፡፡

Temuaget
ጓዳችን፣ ማጀታችን፣ በጀታችን፣
"እንዲህ ያለ ነገር የጠፋ ለመላ"?

አብነት ገመቹ

"በጀቱ ለፓርላማው በወቅቱ አልቀረበም፣ የቀረበውም በዝርዝር አይደለም" የሚል አይነት ጥያቄና እንቅፋት ምራቃቸውን የዋጡ ጠያፋቸውን የከተቱ፣ ለበጀት ዲሲኘሊን እና ለሕግ የበላይነት የተገዙ አገሮች ችግር በጭራሽ አይደለም፡፡

 
Law
የዳኞች መርሀ ችሎት
አካለ መጠን ያልደረሱ ወጣቶች የሚፈፅመት ወንጀል
ሥርዓቱን በተመለከተ


1.    ዕድሜው ከ9 እስከ 15 ዓመት የሆነ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ከአዋቂዎች ጋር በተከሰሰበት የወንጀል ነገር አብሮ ሊታይ አይችልም (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5)
Zennk
ሳይቤሪያ
ሳይቤሪያ /በሩሲያንኛ ሲቢር ይባላል/ ከኡራል ተራራዎች በስተምሥራቅ የሚገኝ የእስያን ክፍለ ዓለም መላው ሰሜናዊ ክፍል የሚይዝ በጣም ሰፊ የሆነ ግዛት ነው፡፡

 
Delalaw
እህህ. . .
ከመሬቱ በላይ ትውላለች እሷ
ደግሞም ከእሷ በላይ ይውላል ሰማይ
አልሙት አልጥፋ የእሷን ልክ ሳላይ

Teles
የሕይወት አቅጣጫ ሲቀየር
በትዕግሥት ዘሪሁን

የስምንተኛ ክፍል ትምህርቷን እስከምታጠናቅቅ ድረስ የወላጆቿን ፍቅርና እንክብካቤ እያገኘች በቤተሰቦቿ ቤት ትማር ነበር፡፡ ተወልዳ ባደገችበት ጎንደር ከተማ ከጓደኞቿ ጋር ለዋና ወደ ወንዝ የወረደችበት እለት ግን የህይወቷን አቅጣጫ ቀየረው፡፡ እሷ እንደምትለወ ውሃው ላይ አርፎ የተንፀባረቀው የፀሃይ ጨረር የአይን ብርሃኗን አሳጥቷታል፡፡ ወይንሸት ሙሉሰው ህይወቷ አስቸጋሪ የሆነው ከዚህ አጋጣሚ በኋላ መሆኑን ትናገራለች፡፡

 
Sport
አትሌት አምበሴ ሞርፊን የተሰኘ...
አትሌት አምበሴ ሞርፊን የተሰኘ መድሃኒት ወስዶ ስለተገኘ ሁለት ዓመት ተቀጣ
 
በደረጀ ጠገናው

ኢትዮጵያዊው የማራቶን አትሌት አምበሴ ቶሎሳ ሞርፊን የተሰኘ የፔንኪለር ተመሳሳይ መድሃኒት ወስዷል በሚል አለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኅበራት ፌዴሬሽን (አይ.ኤ.ኤ.ኤፍ) አትሌቱን ለሁለት ዓመት ከማንኛውም ውድድር አግዶታል፡፡ አትሌት አምበሴ በበኩሉ በወቅቱ ወስዷል ስለተባለው መድሃኒት ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልጿል፡፡

Taxi
የተለመዱ፣ ያልተፈቱ
ለመሳፈር ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቅቀን ታክሲ ተራ ተገኘን፡፡ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ እንደመሆኑ፣ አገልግሎት ለመስጠት በቀላሉ አይሆንለትም፡፡ ተራ ይጠብቃል፡፡ የተራ አስከባሪው ፍቃድ ሲገኝ ነው ጭኖ መውጣት የሚቻለው፡፡

 
World
Image "ምዕራባዊያን - ሊሰቀሉ ይችላሉ"
የሙጋቤ ቃል አቀባይ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሁለት ቀኑን ጉባኤ ሲፈፅም በዚምባብዌ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት እንዲቋቋም አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ በስብሰባው ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የሰጡት ምላሽ አልነበረም፡፡ ምናልባትም ቀደም ሲል "የአፍሪካ ሕብረት ምን አገባው? የሚለውን አቋማቸውን ፀንተውበት ሊሆን ይችላል፡፡"

 
  • Do You Know ?
    How To Increase Font Size
    You can increase the font size of the website if it appears smaller than normal. Just click the member area link at the top right of this page and the page will slide down. At the top left corner of the page, look for three small buttons. To increase font size, click the button with "+" sign and "-" sign to decrease font size.
  • Tips !
    Tips for Amharic Version
    • Use Internet Explorer version 6 or better
    • Adjust your screen resolution to 1024 X 768
    • Use the font resizer to increase font size if needed
    • Though it is not strictly needed having power geez unicode font could enhance the font rendering in your browser
 

Important Links

Visit Ethiopian Yellow PagesA forum on Dialogue, Democracy & Development