| ቻርለስ ቴለር ወታደሮቻቸውን... |
|
|
| Sunday, 16 March 2008 | |
|
ቻርለስ ቴለር ወታደሮቻቸውን የጠላት ሥጋ እንዲበሉ ማዘዛቸው ተገለፀ
የቀድሞው የላይቤሪያ ኘሬዚደንት ቻርለስ ቴለር ወታደሮቻቸው የጠላትን ሥጋ እንዲመገቡ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የቀድሞ የሀገሪቱ የጦር ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣን ማጋለጣቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ጆሴፍ ማርዛ በሄግ በመደመጥ ላይ ባለው የጦር ወንጀለኝነት ክስ ችሎት ላይ በሰጡት የምስክርነት ቃል፤ ቻርለስ ቴለር ወታደሮቻቸው የጠላት ወታደሮችን ሥጋ እንዲመገቡ ትዕዛዝ መስጠታቸውን አሳውቀዋል፡፡ ጆሴፍ እንደገለፁት ቴለር በውጊያው ወቅት ወታደሮች ፍርሀት እንዳይሰማቸው በሚል የሰው /የጠላት/ ሥጋ እንዲመገቡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ “ጠላቶቻችንን መመገብ አለብን፤ የተመድ ወታደሮችንም መመገብ አለብን” በማለት ወታደሮቻቸው አዘዋል በማለት ጆሴፍ ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል፡፡ ቻርለስ ቴለር በሥልጣን ዘመናቸው ወቅት የሴራሊዮን አማፅያንን በማስታጠቅ ለአሥራ አንድ ዓመታት ጦርነት እንዲካሄድ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች እንዲገደሉ በማድረጋቸው የጦር ወንጀለኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ቡድን የአውስትራሊያ ታጋቾችን ለመግደል ዛተ በሰሜን አፍሪካ የሚንቀሳቀሰው የአልቃይዳ ቡድን በሰሜን አውስትራሊያ ሰሞኑን ያገታቸውን ሁለት የአውስትራሊያ ቱሪስቶችን እንደሚገድል ዛተ፡፡ ቡድኑ በአልጄሪያና በቱኒዚያ የታሰሩ አባላቱ ካልተለቀቁ በሦስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ታጋቾቹን እንደሚገድል አስጠንቅቋል ሲል አሶሲየትድ ኘሬስ ዘግቧል፡፡ በዘገባው መሠረት ቡድኑ ባሰራጨው የኢንተርኔት መልዕክት ቱሪስቶቹን በሶስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ለመግደል ዝቷል፡፡ የአውስትራሊያ መንግሥት ታጋቾቹ እንዳይገደሉ በአልጄሪያና በቱኒዚያ የታሰሩ የቡድኑ አባላትን እንዲያስለቅቅ ቡድኑ አማራጭ አቅርቧል፡፡ ቡድኑ የአውስትራሊያ መንግሥት እንዲሁም የአልጄሪያና የቱኒዚያ መንግሥታት የቀረበውን አማራጭ የማይጠቀሙበት ከሆነ ታጋቾችን የሚገድል መሆኑን አሳውቋል፡፡ በኢራን የፓርላመንታዊ ምርጫ ውድድር እየተካሄደ ነው በኢራን የኘሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር በመካሄድ ላይ ሲሆን በውድድሩ የሀገሪቱ የወግ አጥባቂው ፓርቲ እንደሚያሸንፍ መግለፁን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡ የኢራን መንግሥት ባለሥልጣናት ምርጫውን በማሸነፍ ጠላቶቻቸውን የሚያሳፍሩ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል የሀገሪቱ ህዝብ በምርጫው ለመሳተፍ ያሳየው ተነሳሽነት አነስተኛ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ይህም በምርጫው ውድድር የተሳተፉት የፓርቲዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የፓርላመንታዊ ምርጫው ውጤት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ኘሬዚደንታዊ ውድድር ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡ በውድድሩ አራት ሺ አምስት መቶ እጩዎች ፓርላማ ውስጥ ያለውን ሁለት መቶ ዘጠና መቀመጫ ለመያዝ እየተወዳደሩ ነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት አባላት የአየር ብክለትን ለመቀነስ ተስማሙ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በብራሰልስ ባካሄዱት ስብሰባ የአየር ብክለትን ለመቀነስ መስማማታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ በዘገባው መሠረት አባል ሀገራቱ ከኢንዱስትሪ ተቋሞች የሚለቀቀውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ለመቀነስ ተስማምተዋል፡፡ የቅነሳውን አተገባበር በተመለከተ በቅርቡ በሚያካሂዱት ስብሰባ እንደሚወሰን ተገልጿል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |